ያየሰው ሽመልስን አንድ በአንድ (ሙሉ ክፍል አንድና ሁለት)

ያየሰው ሽመልስን አንድ በአንድ (ሙሉ ክፍል አንድና ሁለት)

ያየሰው ሽመልስን አንድ በአንድ

ኤል ሲሲ > ዐቢይ አሕመድ = ሕዳሴ ግድብ

ያየሰው ሺመልስ፤ ማርች1 2020 በፌስ ቡክ ገጹ ላይ “ህዳሴ ግድብ ከለውጡ ወዲህ” ሲል፤ በፍትህ መጽሄት ለሰባት ወራት የጻፋቸውን (በግድቡ ዙሪያ) ሰብስቦ ፖስት አድርጎ ነበር። ጽሁፎቹን ብቻም ሳይሆን ያየሰውን በደንብ አነበብኩት።
ራሱ ባስቀመጠበት ቅደም ተከተል ለመቃኘት ሞከረኩ። ይመሳሰላሉ። ሁለቱን በተከታታይ ለማሳያነት ወስጄ እፈትሻቸዋለሁ። ከጽሁፉ ውስጥ ችግር አለበት ብዬ ያመንኩበትን ክፍል በቀይ፤ የኔን ምላሽ በሰማያዊ ለማሰቀመጥ ሞክሬያለሁ። ምላሾቸን እግር በእግር እየተከተልኩ ማሰቀመጤ የጽሁፉን ፍሰት ከረበሸባችሁ በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ።
*ቀዩ ስህተቱ፤
*ጥቁሩ ሰህተቱን ያጀበበት፤
*ሰማያዊው ደግሞ ሰህተቱን ያደመቀበት ነው።

(በስም የተቀሰውን ባለሶስት ድግሪ ፖለቲከኛ ትንታኔ ከመቀበላችን በፊት፤ እስቲ በስም የተጠቀሰውን አለምአቀፍ የሚዲያ ግሩፕ፤ ያውም ለዘገባው እንዲያገለግለው፤ ኢኮኖሚስቶችን የፓለቲካ ተንታኞችን፤ (እነ ያየሰውን) የሚያነጋግርረውን ኢንተርናሽናል የሚዲያ ግሩፕ እንፈልገው። ጉግል ላይ የለም። ጃፓን ውስጥ በዚህ ስም የሚሰራ ‘NIKKE GROUP’ የተባለ የንግድ ተቋም አለ። እንግዲህ የያሰውም ፖለቲካዊ ተንታኝኙን “ያገኘሁት ከአንድ ጃፓናዊ ወዳጁ ጋር ነው” ብሎን አልነበር? ያው ለንግድ መጥተው፤ ፖለቲካም ንግድ ነው በሚለው ካልኩሌት አድርጎለት ይሆናል። ቀላ ያለ ሁሉ ፈረንጅ፤ ፈረንጅ ሁሉ አዋቂ የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አውቃለሁ። (ከያየሰው ጋር ባልተያያዘ መልኩ ነው፤ ከተያያዘም ከግብጻዊው ተንታኝ የሚያንስ ኮሮሌሽን አይወጣውም) ወይ ኢንተርናሽናሉ የሚዲያ ግሩፕ ጎግል ላይ ያልሰፈረ ይሆን? ያ ከሆነ “በታሪክ የመጀመሪያው ጉግል ላይ ያልሰፈረ ኢንተርናሽናል መስሪያ ቤት” በሚለው ጉግል ላይ ይስፈርልና። በእርግጥ የሚዲያ ግሩፑ አሁንም የለም ብዬ ሙሉ በሙሉ ለመናገር ይሄ ብቻውን በቂ ማስረጃ ላይሆነኝ ይችላል። ለመጠራጠር ግን በቂ ነው። ከተጠራጠርኩ ደግሞ የያሰውን አይነት ጽሁፍ መጻፍ አይታሰብም። እንኩዋን ስለአባይ ግድብ፣ አባይ ስለሚባል ሰውዬ በዚህ ደረጃ ህልውናው ከሚያጠራጥር ምንጭ እየቀዱ ማውራት አግባብ አይደለም። እስቲ ደግማችሁ አንብቡት ስለምን እንዳወሩ፤ ምን ነግሮት ምን ያህል እንዳመነው የጻፈውን ደግማችሁ አንብቡልኝ እስቲ። ያላለው ነገር የለም። ይሄንን ሁሉ አምኖታል። ያየሰው የጋዜጠኝነት ኢቲክስ ላይ እንደማይደራደር ፔጁ ላይ ጽፎ አይቻለሁ። ጋዜጠኝነትን እንደሚያከብረውም ጭምር የተናገረውን እዚህ ውስጥ አጥቼዋለሁ።)

እሱ ለግብጽ የፖለቲከኞች ሰፈር የቀረበ ነው፡፡ሁለቱ ወንድሞቹ ከአሁኑ ፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ ጋር አብረው የሚሠሩ ናቸው፡፡አንዱ የፕሬዚዳንቱ ጠባቂ ሲሆን፣ሌላኛው ደግሞ እዚያው ፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት የሚሠራ ባለሙያ ነው፡፡ የሳቤር አባት በሙባረክ ዘመን የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡በ1987 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ከሱዳን የተላኩ ነፍሰ-ገዳዮች ሙባረክን ለመግደል በሞከሩ ወቅት የሳቤር አባት አብረው ነበሩ፡፡

ከግድያ አምልጠው ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ሙባረክ ‹‹ይህንን ጥቃት ያከናወነችብኝ ኢትዮጵያ ናት›› ሲሉ ወነጀሉ፡፡ የሳቤር አባት ግን ከድርጊቱ ጀርባ ያለችው ኢትዮጵያ ሳትሆን ሱዳን እንደሆነች ቢወተውቱም ሰሚ አጡ፡፡

ሙባረክም ከቤተመንግሥት እስከተወገዱበት 2003 ዓ.ም ድረስ በአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ ላይም ሆነ በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ሳያልፉ ኖሩ፡፡

(የተንታኙ ሰውዬ አባት በሙባረክ ዘመን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንደነበሩ ነግሮናል። ይሄ ንግግር ብቻውን ስህተት አለበት። ሲጀመር በሙባረክ ዘመን ብዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ነበሩ። የሁሉም ልጅ ነው? የግድያ ሙከራው እለት አብረው ነበሩ ብሎናል። እሳቸው ናቸው ብለን እንውሰድ? እሳቸው ከሆኑ ደግሞ አመር ሙሳ ናቸው ማለት ነው። (አመር ሙሳ ከግድያው ያምልጡ አያምልጡ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ የሚያውቀው ነገር የለም፤ በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሆናቸውን ብቻ ለማስታወስ ነው)። እሳቸው ከሆኑ፤ ሳቤር ራቢዬ የሚባል ልጅ የላቸውም። ኤልሲስን የሚጠብቅ ልጅ ይኖራቸዋል ብዬም አልገምትም። ማጣራት ያልፈለኩትም ለያዬሰው አዝኜ ነው። )

ሳቤር ‹‹ግብጽን ወደ አፍሪቃ የመለሰ ብልህ መሪ›› ሲል የሚገልፃቸው ኤል ሲሲ ደግሞ ምርጥ ዲፕሎማት ሆኑ፡፡ ‹‹ሙባረክ በዘመናዊ የግብጽ ታሪክ ምርጥ ወታደራዊ መሪ ነበር፡፡ የሙባረክን ብስለት የምታደንቀው ኤል ሲሲን ለመከላከያ ደኅንነት ኃላፊ አድርጎ መሾሙን ስትመለከት ነው፡፡ ሲሲን ሙባረክ የመረጠው ወታደራዊ ብስለቱንና ብቃቱን አይቶ ነው፡፡ኋላ ላይም ወደ ጦሩ ኤታማዦር ሹምነት ያደገው በዚሁ ብቃቱ ነው፡፡ ‹‹እናም ሲሲ ከሙባረክ ለግብፃዊያን የተበረከተ ስጦታ ነው፡፡ ሲሲ ቆራጥና አስተዋይ ዲፕሎማት ነው፡፡ ከእርሱ ጋር የሚሰሩት ወንድሞቼ እንደሚነግሩኝ

ሲሲ አንተን እርሱ ወደሚፈልገው አቅጣጫ ለመውሰድ መደራደር የሚችል፣ከፖለቲከኛነት ይልቅ ወታደራዊ ብልጠትና ዲፕሎማሲያዊ ብስለት ያለው ሰው ነው››

‹‹እንደመጣ ያደረገው ነገር ሁለት ነው፡፡አንደኛ ኢትዮጵያን መውጋት አይቻልም፤ ሁለተኛ ኢትዮጵያን የግድብ ግንባታውን እንድታቆም ማድረግ አይቻልም የሚል መርህ ተናገረ፡፡ ወረራ እንፈጽም ብንል መጀመሪያ ሱዳንን መውጋት አስፈላጊ ነው፡፡ምክንያቱም አንደኛ ሱዳን የግድቡ ግንባታ ደጋፊ ነች፡፡ ሁለተኛ ግድቡን ለማፍረስ በቅድሚያ የሱዳንን ግዛት ማለፍ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚሻለው ድርድር ብቻ ነው አለ፡፡ በዚህም ከኢትዮጵያ ጋር እርቅ ካወረደና ሰላም ከፈጠረ በኋላ በቀጥታ ሱዳን ገብቶ አል በሽርን ከሥልጣን አወረደው›› አለኝ፡፡

(ይሄ ሁሉ “ዐቢይና ኤልሲሲ ታርቀው ነው አልበሺርን ያወረዱት” ተብሎ አንዲታመንለት ፈልጎ የሚያቀርበው ቀደዳ ነው። ኤልሲሲ እኮ ከዐቢይ በፊትም አዲስ አበባ ይመጣ ነበር። ያላቸውን ልዩነት እንደዛሬው ሁሉ በድርድር (ይዘቱ ምንም ይሁን) ለመፍታት ሲሞክር ነበር። ከአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ጎን ለጎን ከሀይለማሪያም ጋርም አውርቶ ያውቃል። ኤልሲስ ከኢትዮጵያ ጋር የመጀመሪያውን የግንባር ውይይት ያደረገውም ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ አዲስ አበባ በመጣበት ወቅት ከሀይለማርያም ጋር ይመስለኛል። ከዐቢይ ጋር ያወረደው አዲስ ሰላምና እርቅ የለም። ኤልሲሲ ማለት ኢትየጵያ ፓርላማ ውስጥ ቁጭ ብሎ ሲያወራ የምናውቀው ሰው ነው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ ከአፈ ጉባኤዋ ጎን ቁጭ ብሎ በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ ከተሰቀለው የአረባዊት ሪፐብሊክ ግብጽ ባንዲራ ጎን ቁጭ ብሎ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የታየ ሰው ነው። Egypt's President arrives in Ethiopia ይህቺን አየት አድርጋት World Bulletin ላይ ታገኛታለህ። ኤልሲሲ አቡነ ማቲያስን ሳይቀር እንዳወራቸው ታጫውትሃለች። ያየሰው ያኔ ምናልባትም ማትሪክ እየተፈተነ ይሆናል። (ለዚህ ታሪክ ማጣፈጫ ሲባል ትንሽ ከዕድሜው ላይ ቀንሰናል) የዘንድሮ ልጅ መቼም አይደርስበት የለ፤ ያየሰው ዶክተር ስለሺን ሀይድሮሎጂካሊ ምናምን ሊገመግመው ሲሞክር ያየሁባትን ዘመን መቼም አልረሳት።ግድ የለህም፤ የዶክተሩን ስም ጉግል ላይ ጻፍና የሰራቸውን ጥናቶች ብቻ ቼክ አድርጋቸው። ምናልባትም ስሙን ለብቻህ በክፉ ያነሳህበትን አጋጣሚ ሁላ እያስታወስክ ትጸጸታለህ። ቢያንስ ‘ደረቱን ነፍቶ የግድቡን ሀይል ቀንሰነዋል አለ’ እያልክ ፖስት ከማድረግ ያድንሃል። ንቀኸው ነው አይደል? ደፋርና ደንቆሮ አድርገኸው ነው አይደል? እፍረተ ቢስ የሀገርን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ አድርገኸው ነው አይደል? ……..)

I‹‹የግብጽ ደኅንነት በአል በሽር መወገድ ላይ ሚና ነበረው እያልከኝ ነው?›› ስል ጠየቅሁት፡፡
‹‹ይህንን ትጠራጠራለህ እንዴ ?!›› ሲል መልሶ ጠየቀኝ፡፡
በርግጥም አልጠራጠርም፡፡የእርሱን መረጃ በመሻት እንጂ በሱዳን ውስጥ ያለ ግብጽ ፈቃድ ሥልጣን የያዘ መሪ ታይቶ እንደማይታወቅ ጠፍቶኝም አይደል፡፡

(ያየሰው አያነብብም! አልበሺር ስልጣን የያዘውም ያንን ሁሉ አመት የገዛውም በግብጽ ፈቃድ አልነበረም። ከእንግሊዝ የእጅ አዙር አገዛዝ ነጻ ከወጣች ወዲህ ሱዳንን የመሩ ሁሉ ሲመጡ ከግብጽ ጋር ወዳጅ መሆናቸውን የሚናገሩ፤ ትንሽ ሲቆዩ ግን ከግብጽ ጋር ባለመስማማት የሚታወቁ ናቸው። በራሳቸው የውስጥ ትገል እና ፖለቲካል ኬሚስትሪ የተመለዱ ናቸው። የእሷ አለመፈለግ ነጥብ ሆኖ አያውቅም። ሱዳንን ክፉኛ ከመናቅ የሚመጣ ስህተት ነው። ማነህ ያየሰው! ሱዳን ከሁለቱም የተሻለ ሀብት ያላት ሀገር ናት። ከፈርኦን በኋላ ግብጽ የራሱዋንም መሪ በፈቃድዋ መርጣ አታውቅም እያሉ የሚሳለቁትን አልሰማም ማለት ነው። ሱዳንን ካርታ ላይ ያያት እንኳን ይሄንን አይነት መደምደሚያ ለመስጠት አይደፍርም። ለማንኛውም የDavid Mills መጽሃፍን አንብበው። Dividing the Nile: Egypt’s Economic Nationalists in the Sudan, 1918-56 ይላል። ከሱዳንና ከግብጽ ጋር ያስተዋውቅሃል። ለመጻፍ እንጂ ለመጽሃፍ ጊዜ ከሌለህ ደሞ፤ Egyptian-Sudanese relations amidst power struggles in the Middle East and Horn of Africa የምትለዋን የHousam Darwisheh ጥናታዊ አርቲክል አየት አድርጋት። ግብጽን አግንኖ ከማየት ትታደግሃለች። በህወሓት ጊዜ የናቁዋትን ሀገር በዐቢይ ዘመን ከማክበር ተራ ካልኩሌሽን ታድንሃለች) የሱዳንን መፈንቅለ መንግሥት በቀጥታ የመሩት ግብጽና ወዳጆቿ እንደሆኑ የቀድሞው የደኅንነት ኃላፊ ጎሽ ለዘኢኮኖሚስት የተናገሩትን አንበቤያለሁ፡፡

ፈረሷን መቼ ማንቀሳቀስ እንዳለበት የሚያውቅ ብልህ ሰው፣የሚሠራውን ሥራ ቅደም ተከተሉን የሚያውቅ ሰልፈኛ ወታደር፣ የዲፕሎማሲ ሀሁ የገባው የፈረኦን ልጅ! (ይሄንን አድናቆት ኤልሲስ ራሱ ቢሰማ አሽሟጠጠኝ ብሎ ይሰቅለው ነበር። በነገርህ ላይ ያየሰው፤ “በቀን ይሄን ያህል ሰው ይገደል ነበር!” የሚል ጥናት ባቀረብክበት አዳራሽ ውስጥ ባይሆንም ሌላ ቦታ ወዳጆችህ መሃል የምታወራት ስታትስቲክስ ልንገርህ፤ ብልሁና አዋቂው መሪህ ኤልሲስ ወደስልጣን ከመጡበት ከ2013 ጀምሮ 2443 ሰዎችን በሞት ቀጥተዋል። ከዚህ ውስጥ 82ከመቶው በፖለቲካ ምክንያት በስቅላት የተቀጡ ናቸው። ይሄን ያስተዋሉ The Hangman of the Middle East ይሏቸዋል። አልበሺርን ያወረደው ሰውዬ፤ እነዚህን ሁሉ ሰቅሎአል። ፈረሱን መች እንደሚያንቀሳቅስ አዋቂው የፈርኦን ልጅ! አሁንም በነገርህ ላይ! ኤልሲስን አስተዋይና ዲፕሎማት ብሎ መግለጽ፤ በፌስ ቡክ ሚስቴን አንጓጠጡ ብሎ እስር ቤት የሚወረውርን መሪ በአስተዋይነትና በምርጥ ዲፕሎማትነት መምረጥ ከባድ የእውቀት እጥረት ይፈልጋል። ተሳክቶልሃል። በዲፕሎማሲ አለም የውስጥ ቀጋ የውጭ አልጋ መሆን አይቻልም። ማዳ ማሰር የሚባል ወጣት ጸሃፍትን የሚያበዛ ሚዲያ አለልህ፤ ትንታጎች ናቸው። ስለሃገራቸው የሚብሰከሰኩ፤ እናንተ ዛሬ ዐቢይን ለማጣጣል ለስላሳና አርቆ አሳቢ የምትሉትን ጁንታ በምን መልኩ እንደሚተርኩት ግባና አንብብ! የግብጽ መሪዎች በየትኛዋም የአፍሪካ ገጽ አሪፍ የዲፕሎማሲ ታሪክ የላቸውም። የአረብም ሊግም የአፍሪካ ህብረትም አባል ነኝ እያለ ከሚወላውለው የማንነት ስቃያቸው ገና አልተፈወሱም። በህዳሴ ግድቡ ከተከተሉት ዲፕሎማ የትኛው ነው ብልህ? በሱዳን ላይ በደቡብ ሱዳን ላይ ከተገበሩት ዲፕሎማሲ የትኛው ነው ዲፕሎማቲክ? ከሊቢያ እሰከ አልጄሪያ ከማሊ አስከ ዶሃ ከአንካራ እስከ ጎላን ኮረብቶች ከሲናይ አሰከ ሃላይብ ከቀይ ባህር እስከ ስዊዝ ካናል የቱ ነው ጥበበኛው ዲፕሎማሲ? )

ከወራት በፊት የሱዳንን ፖለቲካ እርሱ በሚፈልገው መልኩ ቋጭቶታል፡፡ በሳቤር ቋንቋ ሲሲ ከኢትዮጵያ ጋር እርቅ አውርዶ፣በሽርን ከሥልጣን አወረደው፡፡ ቀጥሎ ቀጣዩን ትኩረት አዲስ አበባ ላይ አደረገ፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲከኞች በረዥሙ በለቀቀው ገመድ እየተቆጣጠራቸው ነው፡፡ (ይህቺን ቀደዳ ወረድ ብለን ስትፎርሽ እንይዛታለን) ለዚህም ሕዳሴ ግድብ የተሰኘ ፕሮጀክት ዋነኛ ማዕከሉ ሆነ፡፡

ዐቢይ እና ሲሲ

ይህንን የሰሙት ሲሲ እሳት ለብሰው እሳት እየተነፈሱ ስብሰባውን ጀመሩ፡፡‹‹ሳታማክረንና እኛ ሳናውቅ ለምንድን ነው ግድቡ በዚህ ጊዜ ኤሌክትሪክ ያመነጫል፤ በዚህ ዘመን ይጠናቀቃል የምትለው?!›› ብለው ዐቢይ አሕመድ አሊ ላይ አይኖቻውን አጉረጠረጡ፡፡ በቦታው የነበረው ሰው ጉዳዩን ሲገልፀው ‹‹አንድ ክፉ አለቃ፣ሠራተኛውን ሲቆጣ ይመስል ነበር›› ይለዋል፡፡ (የቅድሙዋን ቀደዳ ስትፎርሽ አያችሁልኝ? የኢትዮጵያን ፖለቲከኞች በረዥሙ በለቀቀው ገመድ እየተቆጣጠራቸው ነው” ያለውን ረስቶታል። ዐቢይ እንግዲህ ለሚቆጣጠረው ሰውዬ ሳያሳውቅ በመናገሩ ቁጣ እየተቀበለ መሆኑ ነው። ስለዚህ ፈረሷን መቼ ማንቀሳቀስ እንዳለበት የሚያውቀው ኤልሲሲ እዚህ ጋ ምን ነክቶት አመለጠችው? ገመድ አጥሮበት ገበያ በሄደበት ሰአት አምልጣው ይሆን?

ያየሰው የሚያሳዝነኝ ለዚህ ነው! ሲጽፍ ብቻ አይደለም ሲናገርም ይቸኩላል። አሁን ይሄ መረጃ ላይ ላዩን ሲታይ የአንባቢን ቀልብ ይይዛል። ጠለቅ አድርገው ከመረመሩት ግን ለያየሰው ቀለብ መግዣ መሆኑን እንረዳለን። ሲጀመር እንዲህ አይነት መረጃ ‘በስፍራው የነበረ ሰው ነገረኝ’ ተብሎ የሚጻፍ አይደለም። ወይም ‘በስፍራው የነበረው ሰው’ በሚለው ስታይል ከዚህም በላይ አስገራሚ መረጃዎችን መጻፍ ይቻላል። እንዲህ አይነት ሴንሰቲቭ ጉዳይ፤ ይሄንን የሚያህል ሀገራዊ ጉዳይ፤ እንዲህ አይነት የብዙ አካላት ፍላጎት ያለበት ጉዳይ፤ ‘ከሰው እንደሰማሁት እና በስፍራው የነበረ ሰው ሲገልጸው’ እያሉ መጻፍ በጣም አደገኛ አላዋቂነት ነው። የጸሃፊውን ፍላጎትና አቅም እንድንናጠይቅ የሚያስገድድ ነው። ለነገሩ ይህቺ ስታይል ያየሰውና የአለቆቹ መታወቂያ ናት። ስዩም መስፍን የተባለው GOOFY፤ በቃለመጠይቁ ላይ እንደውስጥ አዋቂ ቀርቦ “ድርድሩ ላይ ከነበሩ ሰዎች እንደሰማሁት’ እያለ ሲያወራ ታዝበነዋል። ለማንኛውም፤ እኔም “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአልሲስ ግድቡን በ10ቢሊዮን ዶላር ሊሸጡላቸው እንደተስማሙና ገንዘቡንም ከሲናይ በረሃ ወደግራ አጠፍ ብላ ከምትገኝ ካፌ ወሰጥ አርብ ምሳ ሰአት ላይ ሊረከቡ እንደሆነ በድርድሩ ላይ የነበረ አንድ ውስጥ አዋቂ ነግሮኛል ይሄንን ስሰማ አጠገቤ የነበሩት ታዛቢዎችም፤ ወደሰማይ ያንጋጥጡ ነበር…………..”)

በጊዜው ሰዎች የጠቅላይሚኒስትር ዐቢይን ኮስታራ ምላሽ ቢጠብቁም አልሆነም፡፡ይልቁንም አንገታቸውን ደፉ፡፡ግብፆች አንዳንዴ እንዲህ ባለ ሁኔታ ከልክ ሲያልፉ፣ ‹‹ይህ እናንተን አይመለከትም፤ ይህንን ለመናገር የእናንተን ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም፤ማተኮር ያለብን በሌሎች የድርድር ሀሳቦች ላይ ነው፤ወዘተ›› የሚሉ መልሶች ከኢትዮጵያዊያን መሪዎች ዘንድ ይሰጥ እንደነበርም እነዚሁ ቤተመንግሥትኞች ያስታውሳሉ፡፡ ይህ ግን በጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ ዘመን ቀርቷል፡፡ይልቁንም በሲሲ ቁጣ አንገት መድፋት ተጀመረ፡፡

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይና ኤል ሲሲ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በሰኔ 2010 በካይሮ ነበር፡፡ያኔ ‹‹ወላሂ እናንተን አንጎዳም›› ብለው መምጣታቸውን ባሳለፍነው ሳምንት አስታወሰናል፡፡

በጊዜው ሰዎች የጠቅላይሚኒስትር ዐቢይን ኮስታራ ምላሽ ቢጠብቁም አልሆነም፡፡ይልቁንም አንገታቸውን ደፉ፡፡ግብፆች አንዳንዴ እንዲህ ባለ ሁኔታ ከልክ ሲያልፉ፣ ‹‹ይህ እናንተን አይመለከትም፤ ይህንን ለመናገር የእናንተን ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም፤ማተኮር ያለብን በሌሎች የድርድር ሀሳቦች ላይ ነው፤ወዘተ›› የሚሉ መልሶች ከኢትዮጵያዊያን መሪዎች ዘንድ ይሰጥ እንደነበርም እነዚሁ ቤተመንግሥትኞች ያስታውሳሉ፡፡ ይህ ግን በጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ ዘመን ቀርቷል፡፡ይልቁንም በሲሲ ቁጣ አንገት መድፋት ተጀመረ፡፡

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይና ኤል ሲሲ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በሰኔ 2010 በካይሮ ነበር፡፡ያኔ ‹‹ወላሂ እናንተን አንጎዳም›› ብለው መምጣታቸውን ባሳለፍነው ሳምንት አስታወሰናል፡፡

በወቅቱ ግብጽ ከድርድሩ አኩርፋ ወጥታ ነበር፡፡ በተለይም የግድቡን የውሃ አሞላል በተመለከተ የኢትዮጵያ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን መደራደሪያ ሱዳን ብትቀበለውም ግብጽ ውድቅ አደረገችው፡፡ በዚያውም ድርድሩን አቋርጣ ወጣች፡፡ (ውሸት ነው። ከድርድሩ የወጡበት ወይም ድርድሩ ቆሞ የነበረበት ምክንያትም የተጠቀሰው አይደለም። ሱዳን ስለውሃ ሙሌት ከኢትዮጵያ ጋር ተስማምታ የምታውቅበት ጊዜ መኖሩን የሚናገር ሰነድ የለም። ሌላ ያፈጠጠ ውሸት። የዚህ አይነት ወሬ አላማው፤ ‘ህወሓት በረቀቀ የዲፕሎማሲ ክህነቱ ከጎናቸን እንድትቆም ያደረጋትን ሱዳንን ዐቢይ አህመድ አስከፍቶ አባረራት’ የሚለውን የሾቀ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ማጠናከር ነው። ሱዳን ሲጀመር ‘ከእኛ ጋር ነበረች’ የሚያስብል ታሪክ ኖሮአት አያውቅም። ሱዳን እኮ የትብብር ማእቀፉን ካልፈረሙ ሀገራት አንዱዋ ናት። ከግብጽ ጋር ጥላ እንደወጣች ነው ያለችው። ሁሌ ከእኛ ጋር ነበረች እያሉ መጻፍ ምነድነው ጥቅሙ? ይልቅ ያየሰውን፤ Egypt versus Ethiopia: The Conflict over the Nile Metastasizes የሚለውን የFred H. Lawson ዘ ስፔክታተር ላይ የታተመ ጽሁፍ እንዲያነብብ ልጋብዘው። ሂደቱን በተሻለ መልኩ ከሚገልጹ ጽሁፎች ውስጥ አንዱ ነው። ለምሳሌ፤ መስከረም 19 2016 ላይ ሁለቱን የፈረንሳይ አማካሪ ድርጅቶች ለመቅጠር የተስማሙትም ያኔ ነው። የግድቡን ጉዳትና ጥቅም እንዲያጣሩ ተስማምተው ቀጠሩዋቸው። ኢትዮጵያ ግን በሚንስትሩዋ በኩል “የአማካሪዎቹ ሪፖርት ምንም ሆነ ምንም ስራውን በፕሮግራሙዋ እንደምትቀጥል ተናገረች። ያኔ የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም ግሃንዱር “የግብጽን ፍላጎት የሚጎዳ ማንኛውንም አይነት ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር እንደማታደርግ ተናገሩ። ለዚህ ውለታዋ ምላሽ ነው፤ ኦክቶበር ላይ ኤልሲሲ ህገመንግስታዊ ተሃድሶ ተብሎ በተዘጋጀ ድግስ ላይ ለመገኘት ካርቱም የሄዱት። በምላሹም ሱዳን የመስኖ ሚኒስትሩዋን ከግብጽ ጋር በጋራ ስለሚሰሩዋቸው ፕሮጀክቶች ለመወያየት ወደ ካይሮ የላከችው። በዚህ የተበሳጨችውና የተደናገጠችው ኢትዮጵያም በጌታቸው ረዳ በኩል ግብጽን የሚያወግዙ መግለጫዎች ስታንጋጋ ነበር። ይሄ የሚያሳየው፤ ሱዳን የኢትዮጵያንም ሆነ የግብጽን ፍላጎት ለይቶ የሚያሰተናግድ ልብ እንደሌላት ነው። ለራሱዋ ነው የምትጨነቀው፤ የራሱዋ ቁማሮች አሉዋት። ይህቺ ጽሁፍ ሱዳን በሞርሲ መፈንቅለ መንግስት እንዳኮረፈችና ወደ ግድቡ ጠጋ እንዳለች ታወራለች። ዝም ብለህ እያት እስቲ፤ 2013 ላይ መቅረቡዋንም እንዳትረሳ። Egypt-Sudan Ties Deteriorate Over Nile Ayah Aman – ዛሬ ዐቢይ ሊያባርራት አሊያም ነይ ሊላት አይችልም። ይህቺን ላለመሳት የሃላይብ ትሬያንግል ፖለቲካን ማንበብ ብቻ ይበቃል። ያየሰው አንብብ! የጻፍከውንም ቢሆን ደግመህ አንብብ! ቢያንስ ደንገጥ ያደርግሃል!)

ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ በቤጂንግ በተካሄደው የቻይና አፍሪቃ ጉባኤ ላይ ሁለቱ መሪዎች በድጋሚ ተገናኙ፡፡ ከሁለቱ መሪዎች ውይይት በኋላ ግብጽ ወደ ድርድሩ መመለሷን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ፡፡ ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ ለሲሲ ምን ቃል እንደገቡ እስካሁን ድረስም ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ በቤጂንግ በተደረገ ውይይት ግብጽ ወደ ድርድሩ ተመለሰች ተባለ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ፕሬዚዳንት ሲሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን በቤተመንግሥታቸው ተገኝተው የተቆጧቸው፡፡የግብጹ አለቃ ከባድ ሆኖባቸው የሰነበተው ነገር የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጎን መቆም ነበር፡፡በተለይ አል በሽር ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር በነበራቸው መልካም ግንኙነትና በዘላቂ ጥቅማቸው ምክንያት የሕዳሴ ግድብን ደግፈው መቆማቸው ራስ ምታት ነበር፡፡ይህንን አቋማቸውን እንዲያሻሽሉና ለዚህም በሱዳን የተቀሰቀሰውን አመጽ በማርገብ በኩል አንደሚተባበሯቸው ቃል ቢገቡም አልሆነም፡፡ በሽርን ደጋግመው ካይሮ በመውሰድ ለማሳመን ሞከሩ፡፡የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ግን ፍንክች ሊሉ አልቻሉም፡፡እናም ሲሲ ወደ ሁለተኛ አማራጫቸው ሄዱ፡፡በሽርን ለማውረድ ከወታደሩ ጋር ሰሩ፡፡ በመጨረሻም በሽር ተወገዱ፡፡ይህንን ሒደት ስለሚያውቅ ነው ጋዜጠኛው ሳቤር ‹‹ከኢትዮጵያ ጋር ታርቆ በሽርን አወረደው›› ያለው፡፡

ዐቢይ እንደ በሽር?

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢንዲያ ኒውስ ሌተር የተባለው ጋዜጣ ‹‹ዐቢይ አሕመድ በሕዳሴ ግድብ ላይ ተራማጅ አቋም አላቸው›› ሲል ለዘብተኛነታቸውን ዘገበ፡፡‹‹ጠቅላይሚኒስትሩ የሕዳሴውን ግድብ የማመንጨት አቅም ከ6450 ወደ 2022 ሜጋ ዋት ለማውረድ ወስነዋል፡፡ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታየው የብሔር ግጭት ጀርባ አለች ብለው የሚያስቧት ግብጽ እጇን እንድትሰበስብ ያደርጋል ብለው ያልማሉ›› ይላል-ጋዜጣው፡፡

ይህ ጋዜጣ የደኅንነት ዘገባዎችን የሚያስነብብ፣እስካሁንም በዘገባቸው መረጃዎች ላይ ብዙም ጥያቄ ያልተነሳበት ታማኝ ዘጋቢ ነው፡፡ (ይሄንን ዘገባ ብሎ ማመኑ ሲገርመን፤ የምንጩን አስተማማኝነትና አዋቂነት ለማስረገጥ የሄደበት ርቀት በጣም አሳፋሪ ነው። ‘እመኑት አይሳሳትም’ ይለናል። መቼም ጊዜ ዳኛው ይደብቀው የለው፤ ይኸው፤ ግድቡን ዐቢይ አህመድ ወደ 2000ሜጋ ዋት አውርዶ ሊያስመርቀው ሽር ጉድ እያለ ነው አይደል? ያመኑት ተሳስተዋል። በዚህ ደረጃ የዐቢይ መንግስት ግድቡን አይፈልገውም ብሎ የሚያምን የፖለቲካ ተንታኝ መኖሩ ዘላለማዊ ግርምትን ይፈጥርብኛል። ‘ግብፅ የብሄር ግጭት ታስነሳብኛለች ብሎ ስለሚፈራ የግድቡን ሀይል የማመንጨት አቅም ከ6ሺህ ምናምን ወደ 2ሺህ ምናምን ለማውረድ ወሰነ’ ሲባል አምኖ የሚቀበልን፤ ተቀብሎም ‘እናንተም ተቀበሉ’ የሚልን የፖለቲካ ተንታኝ ምን ይሉታል? ስንትስ ይከፍሉታል? በእርግጥ ለመናቅም ቢሆን ዕውቀት ያስፈልጋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍ ቢሰማው እንኳን መጠቀም ስለሌለበት የመረጃ አይነት አለቆቹ ቢያስተምሩት ጥሩ ነበር።)

ይህንን ጉዳይ ብዙም ትኩረት እንዲያገኝ የተፈለገ አይመስልም፡፡ መገናኛብዙሃኑ ሁሉ (ለወትሮው ግድቡን በተመለከተ ‹በቅሎ ወለደች› ብሎ የሚዘግብው ሁሉ) ምንም ሳይለው ቀረ፡፡ ይልቁንም ኢቴቪና መሠል የመንግሥት መገናኛብዙሃን የሕዳሴው ግድብ የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች ቁጥር በግማሽ መቀነሳቸውን ይፋ አደረጉ፡፡

ይህ የግብጽ መደራደሪያ ነው፡፡ግብፆች በመጀመሪያው አካባቢ ያቀርቡት የነበረው ሐሣብ፣ግድቡ ቁመቱ ይጠር፤የሚይዘው ውሃ መጠን ይቀንስ ወዘተ የሚል ነበር፡፡ይሁን እንጂ ይህ በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አጥቶ ኖሯል፡፡የግድቡ መገንባት የማይቀር መሆኑ የገባቸው የካይሮ ሰዎች ሌላ መደራደሪያ ይዘው መጡ፡፡ ይኸውም ‹‹የማመንጨት አቅሙ ይቀንስ፤የግድቡ ውሃ በሰባት ዓመት ይሞላ፤በየዓመቱ 40 ቢሊዮን ሜትር ኪዊቢክ ውሃ ይለቀቅልን፤ይህ ካልሆነ የአስዋን ግድብ ከባሕር ጠለል በላይ 165 ሜትር ቁመቱ ይቀንሳል፤ ሕዳሴ ግድብንም በጋራ እናስተዳድረው›› የሚል ነው፡፡

በዚህ ሐሣብ ነው እንግዲህ የኢትዮጵያ የባለሙያዎች ቡድንና ጠቅላይሚኒስትሩ ልዩነት ውስጥ የገቡት፡፡ጠቅላይሚኒስትሩ በሰባት ዓመት ይሞላ የሚለውን ሲቀበሉ፣ባለሙያዎቹ ደግሞ ቢያንስ በአራት ዓመት ተሞልቶ ማለቅ አለበት፣ከረዘመ ግን ከስድስት ዓመት በላይ መሄድ የለብንም የሚል ሳይንሳዊ ትንታኔ አላቸው፡፡

የሕዳሴ ግድብን ለመሙላት ከ74ቢሊዮን ሜትርኩዊቢክ የሚበልጥ ውሃ ያስፈልጋል፡፡ይህንን የሚያውቁት የኢትዮጵያ ባለሙያዎች 1ኛ-ውሃውን መልቀቅ ያለብን ቢበዛ 30/35 ቢሊዮን ሜትር ኪዊቢክ ነው፡፡2ኛ-ይህም አሳሪ ሳይሆን እንደየ ዝናቡ መጠንና በየዓመቱ እንደሚኖረው የውሃ መጠን የሚለያይ መሆን አለበት የሚል ነው፡፡ይሁን እንጂ ጠቅላይሚኒስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ሊስማሙ አልቻሉም፡፡ ይህም የሚሆነው ጠቅላይሚኒስትሩ ባለሙያዎችን ከአንድ ዓመት በላይ አንድም ቀን አግኝተው ሳያነጋግሯቸው ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ነው እንግዲህ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ግብጽ አቅንቶ የነበረው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ‹‹የግብጽን መደራደሪያ አንቀበልም ብለን መጣን›› ሲል በመስኖና ውሃ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ በኩል መግለጫ የሠጠው፡፡‹አንቀበልም አልነው› ያሉት በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ ገብቼ የሕዳሴ ግድብን በጋራ ላስተዳድረው የሚለውንና በዓመት 40 ቢሊዮን ሜትርኩዊቢክ ውሃ ልቀቁልን የሚለውን ነው፡፡

(እዚህ ጋ ያሉትን ቀዮች በሙሉ፤ ‘መሰረተ ቢስ’ በሚለው ስም አያይዘን መጥራት አንችላለን። የጠቅላይ ሚኒስትሩን በግድቡ ላይ ያለ አቋም፤ የተደራዳሪዎቹንና የእሳቸውን ልዩነት፤ እንዲሁም የግብጽን ፍላጎቶች በተመለከተ ያየሰው የሚነግረንን መረጃ ባልሰማ ማለፉ ነው የሚያዋጣው። ምንጭ አይጠቅስም፤ ያልሆነውን ሆነ ይላል፤ ከራሱ ፍላጎት ጋር ለማስተሳሰር በራሱ ደርዝ ለመለካት ይለፋል፤ ግቡ ሁሉ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ለሀገር ግድ የለሽ እንደሆኑ በማንኛውም መንገድ ተናግሮ ማለፍ ነው።የግብጽ

ተላላኪ እንደሆኑ አስገንዝቦ ማለፍን ይመርጣል። እሳቸውን ለመውቀስ ሲልም ሌላ ጊዜ የሚያንኳስሰውን ተደራዳሪ ቡድን፤ ረስቶት ሲያደንቀው እናገኘዋለን። ዝቅ ብሎ ደግሞ ከግብጽ ጋር ሳይስማሙ የወጡባቸውን ነጥቦች ያለምንም ማስረጃ ጠቅሶ ሲያበሻቅጣቸው እንታዘባለን። ያየሰው እንደልቡ፤ እንዳሰኘው ይተነትናል። በተለይም የዛሬ እውነታዎችን ለሚያገናዝቡ አንባቢያን ይሄንን በማብራራት ጊዜ አላባክንም።

‘ሰባት አመት’ የሚለው የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ምርጫ ተደርጎ መቅረቡና ለወቀሳ በመዋሉ ግን ለሌላ አስገራሚ መገረም መዳረጌን እወቁልኝ።

እዚህ ጋር ‹‹ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ ለምን ይህንን ያህል ለግብጽ ሸብረክ አሉ?›› (ምንም ሸብረክ የለም፤ ሸብረቅ ብሎ ነው ያየነው። ፖምፒዮ ላይ ቀጥ ብሎ የበቀለ ዝግባ ነው!) የሚል ጥያቄ እናንሳና፣ ‹‹ዛሬ ቢሆን ኢትዮጵያ እንኳን ግድብ ልትገነባ መሠረት ድንጋዩንም አታስቀምጥም ነበር›› የሚለውን የኤል ሲሲ ልበሙሉነት እናስቀጥል፡፡ (ድሮም የሚሉት ነገር ነው። “እኛ በአመጽ ስንመታ ነው ግድቡን የጀመራችሁት እንጂ ዛሬ ቢሆን አትሞክሩትም ነበር” ሲሉ ነው የኖሩት። ዛሬ ኤልሲስ እንዲህ ቢል፤ ዐቢይ በሰጠው ማረጋገጫ አይደለም)

ግብጽ በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ እጅግ የበለጠና የረቀቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት፡፡ በዓለማቀፍ ተቋማትና መንግሥታት ዘንድ ያላት ወቅታዊ ተሰሚነት ከኢትዮጵያ አንፃር ሲታይ የሠማይና የምድር ያህል ነው፡፡ ሲሲ የልብልብ እንዲሰማቸው ያደረጋቸውም ይሄው ሥራቸው ነው፡፡ (ይሄም የተዛባ ትንተና እና አረዳድ ነው። ዐቢይ ተሸንፎአል ለሚለው አጉል ድምዳሜ የቀረበ ሀሳዊ መስዋት ነው። ከሙባረክ አጋማሽ ዘመን ወዲህ የግብጽ አለማቀፋዊ የመደራደር አቅም እጅጉን ወርዶ፤ በተለይም የውሃ ፖለቲካው ውስጥ በሚታወቀው የሄጂመኒ ፖለቲክስ መሸነፉዋ ከተረጋገጠ በጣም ቆይቱዋል። ግድቡን መገንባት ከመጀመሩዋ በፊት ያለቀ ጉዳይ ነው። ስትጀምር ደግሞ የበለጠ ደመቀ። ዐቢይን ለማሳነስ፤ የግብጽንና የኤል ሲሲን ሀይል ማግዘፍ ከፈገግታ ሌላ የሚያተርፈው ነገር የለም። እስቲ “EGYPT’S NEW REALISM Challenges Under Sisi” የሚለውን የ Bakar Barfi ጥናት አንብበው። THE WASHINGTON INSTITUTE FOR NEAR EAST POLICY ላይ ታገኘዋለህ። ስለ ኤልሲስ ያለህን አድናቆት ባላንስ ያደርግልሃል። ስለተገረምክበት አይኤምኤፋዊ ጋብቻም ሲኦል ሲኦሉን ያጫውትሃል።)

በርካታ ግብፃዊያን ከሚሠሩባቸው ተቋማት አንዱ የዓለም ባንክ ነው፡፡ከሁለት ዓመታት በፊት ግብጽ ‹‹ስለ ሕዳሴው ግድብ የዓለም ባንክ ያደራድረን›› የሚል አማራጭ አምጥታ በኢትዮጵያ ውድቅ ተደርጎባት ነበር፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ቀጥታ በጀት የሚሆን የ1.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መስጠቱ የተሰማው፡፡ ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ ከወራት በፊት ‹‹ያለምንም ቅድመ ሁኔታ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ሰጠን›› ሲሉ ላደመጣቸውም ‹‹አልበላሽምን ምን አመጣው››ን ያስተርታል፡፡

(ወርልድ ባንክ ግሩፕ፤ በመላው አለም የሚሰሩ 16ሺህ ሰራተኞች አሉኝ ይላል። በ2017 Compensation, Diversity and Inclusion at the World Bank Group ሲል ባሳተመው ሰነድ ላይም፤ 164 ግብጻውያን ሰራተኞች ሲኖሩት፤ የኢትዮጵያውያን ሰራተኞቹ ቁጥር ደግሞ 185 ነው። በእርግጥ የዘንድሮን ዳታ ማግኘት ባንችልም፤ ያየሰው እንደሚለው ‘ለማዳላት እስኪያደርስ’ ድረስ የቁጥር ብልጫ እንደሌለ መጠቆም ይችላል ብለን እናስባለን። እዚህ የያሰው መረጃ ውስጥ፤ ሌላ አስገራሚ ስህተትና አላዋቂነትም አለ። የባንኩን ግዙፍነት፤ አሰራርና ታሪክ ለሚያውቅ ሰው፤ ‘ግብጻውያንን አብዝቶ በመቅጠርም ሆነ ቀጥሮ ተጽእኖ ሰር ለመውደቅ’ የሚያስችል አወቃቀር አያገኝበትም። ለባሀርይውም ስለማያመቸው፤ ግብጽም ይሄንን ያህል ዋጋ የሚያስከፍል ኪሎ ስሌለላት እንዲህ አይነት ትንተና መሰጠት ለነውር የቀረበ አላዋቂነት ነው። በእዚህ ግዙፍ ደርጅት ውስጥ፤ ትልቁ የስልጣን አካል የዳይሬክተሮች ቦርዱ ነው። ቀጥታ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሮችን ያዝዛል ይሄኛው ደግሞ ሁለት ቀጥታ የሚጠሩለት አካላት አሉት። ፕሬዚደንቱ ለኤክስኪዩቲቩ ይገዛሉ። እሳቸው ደሞ ስደስት ያህል አካላትን (ቦዲስ) በቀጥታ ያዝዛሉ። ሌሎች አምስት ክፍሎችም በፕሬዚዳንቱ ቀጥታ ትእዛዝ ይንቀሳቀሳሉ። በእነዚህ ስር የተለያዩ ቫይስ ፕሬዝዳንቶችን የያዙ ቀጣናዊ አወቃቀሮች ተዘርግተዋል። (ይህንን መረጃ የድርጅቱን ተቋማዊ ቻርት ነው የሚናገረው) ስለዚህ በጥቅሉ፤ ፕሬዚደንቱን ጨምሮ 34 ያህል ትልልቅ ባለስልጣናት አሉ ማለት እንችላለን። እዚህ ውስጥ አንድ የግብጽ ተወላጅ እና የፈረናሳይ ዜጋ የሆኑት ሃፊዝ ጋህኔም ይገኛሉ። የአፍሪካ ቫይስ ፕሬዚደንት ናቸው። በፕሬዚዳንቱና በእሳቸው መካከል ሌላ ሆላንዳዊ አለቃ አሉ። የግብጽን ስም ማንሳት የምንችለው በዚህ ደረጃ ብቻ ነው። በዜጋዋ ባይሆን በተወላጁዋ ሰው ፌቨር ይደረግላታል የሚባል ከሆነም፤ ኢትዮጲስ ተፈራ የተባለ ግለሰብ ጠቅሶ ኩም ማድረግ ይቻላል። ቀጥታ ለፕሬዝዳንቱ ተጠሪ ናቸው ካልናቸው ስድስት መዋቅሮች የአንዱ አላፊ ነው። ኢትየጵያዊ የዘር ግንድ ያለው አሜሪካዊ ለመሆናቸው ስማቸው ይናገራል፤ መልካቸውም እንዲሁ። የግብጹን ተወላጅ በስልጣን ይበልጧቸዋል። ለካ እነ ያየሰውንም በዘር ቆጠራ መርታት ይቻላል? በሜዳቸው!!

አይኤም ኤፍ ለኢትጵያ ሲያበድርም ሆነ ሲረዳ ከግማሽ ምእተ አመት በላይ የሆነው ድርጅት ነው። ኢትየጵያ አባል ከሆነችም የአንድ አዛውንት እድሜ አልፋለች። ጃንሆይም፤ መንግስቱ ሃይለማርያምም መለስ ዜናዊም፤ ሀይለማርያምም፤ ዐቢይም ወደፊት የሚመጣውም መሪ ከአይኤምኤፍ ጋር ያልሰራና የማይሰራ የለም። የማይበደር እርዳታ የማይቀበል የለም። ለሁሉም ቅድመ ሁኔታዎች ይቀርቡላቸዋል፤ ቅድመሁኔታዎቹ ሁሉ ግን በቀጥታ የአይኤምኤፍን ጥቅም ብቻ የሚያስጠብቁ ናቸው ለማለት አይቻልም። ቀጥተኛ የጥቅም ድርድር የሚደረግባቸው ይበዛሉ። ለጤናህ፤ ለትምህርትህ፤ ለመንገድህ፤ ለአካባቢ ጥበቃህ እየተባለ የሚሰጠውም ብዙ አለ (በእርግጥ አዚህ ውስጥም የአይኤምኤፍ ጥቅም የለም ብዬ የምከላከል ቀሽም አይደለሁም፤ ሆስፒታል ገንብቶልኝ ከሚያተርፍ አካል ጋር ለመደራደር ምንጊዜም ዝግጁ ነኝ ለማለት ያህል ነው ) የዐቢይ መንግስት በሁለቱም አይነት መንገድ ነው የአይኤምኤፍን ችሮታ የተቀበለው። ወደፊትም በሁለቱ መንግድ መቀበሉን ይቀጥላል። የያሰው አለቆችም እኔም በምናውቃቸው ምክንያቶች ተጠምዝዞም እየጠመዘዘም ይቀጥላል።

በነገርህ ላይ ከእነአይኤም ኤፍ ጋር በብልጠት በመደራደር ዐቢይ አህመድን የሚያህል የአፍሪካ መሪ ብትጠቅስልኝ ደስ ይለኛል። መለስ ዜናዊ እንዳትለኝ ብቻ።

እንደዚያ ካልክ ሁለት ነገሮች ያጋጥሙሃል። አንደኛ ምናላቸው ስማቸው ከሚባለው ሰውዬ ጋር ትመሳሰልብኛለህ። ሁለተኛው ስለቻይና መረብ ያለህን እውቀት ታስገምትበታለህ። መለስ ከአይኤምኤፍ ጋር አንዴ ውሃ አንዴ እሳት ሲያደርገው የነበረው እናንተ እንደምትሉት የሀገር ፍቅር አንገብግቦት፤ የአይኤም ኤፍ ሆዳምነት ተገልጦለት አይደለም። ከቻይና ጋር የነበረው እፍፍ ያለ ፍቅር ነው። የእናንተ መሸወድም የሚጀምረውም እዚህ ጋ ነው። ‘China is more sympathetic than you’ ይለው ነበር አቦይ ስብሃት ለአሜሪካው አምባሳደር። ዊክሊክስ ጽፎታል። ቻይና ከአይኤምኤፍ የተሻለች አበዳሪና ወለድ ተቀባይ እንደሆነች ለማሳመን የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በቻይና መረብ መጠለፍ የምልህ ይሄንን ነው። አሜሪካ ቻይና ላይ የምትሰነዝረውን ትችት እርሳው። ‘አምባገነን መንግስታትን ታገዝፋለች፤ ለዴሞክራሲ ግድ የላትም’ ምናምን የሚለው ተወው። ሁሉም አምባገነን ነው። እንዲያውም የቻይናው አገዛዝይሻለኛል። ቢያንስ በግልጽ ይናገራል። ከትራምፕ አይነቱ አክተር፤ ሪሉ ዢንፒንግ ይሻለኛል።

ምን እያልኩህ ነው? ቻይናም ጅብ ናት፤ አይኤምኤፍም ጅብ ነው። ሁለቱም ያለወለድ ያለቅድመሁኔታ አያበድሩም፤ አይደራደሩም። ወለድ አልባ የሚለውም የራሱ ጥቅም አለው። አላበላልጣቸውም እያልኩህ ነው። አማራጩ ሁለት ሁለት ነው፤ እንደመለስ አንዱን መምረጥ ወይም ወይም እንደ ዐቢይ ሁለቱንም መምረጥ። ነገርዬውን ፖለቲካሊ ከተነተነው ደግሞ፤ ለእኔ የዐቢይ መንገድ ይሻለኛል። ለተሻለ ድርድርና ዋጋንም ለማዋደድ የተሻለ ዕድል ይሰጣል። እደግምልሃለሁ፤ ከእነ አይኤምኤፍ ጋር በመደራደር ከዐቢይ የተሻለ መሪ አትጠራልኝም። ከጋናው ሰውዬ እኩል በእጁ ስለያዘው ወርቅ የተሻለ ግንዛቤ ያለው መሪ ነው። ያው እናንተ ብትንቁትም፤ መደመር የሚለው መጽሃፍ ላይ የሰውዬውን አረዳድ በግልጽ ሰፍሮ ማግኘት ይቻላል። ከዶሃም ከአቡዳቢም እርዳታ ተቀብሎ ሁለቱንም በእኩል አጋርነት በአደባባይ የሚያመሰግን አይነት ሰው ነው። ይህቺ ምርጥ ብቃት ናት።

ቢያንስ ለአድናቆት ባታበቃም፤ ከስድብ ግን ለመከላከል የምትበቃ ነበረች። እንደነገርኩህ ነው፤ የሀገርን ጥቅም ባለማወቅም ሆነ በጂኦፖለቲክስ አረዳዱ በእነደብረጺዮን ደረጃ የሚተች አይነት ሰው አይደለም። በነገርህ ላይ፤ በእዚህ አይነት የስልጣን እርከን ላይ መገኘት ከሚኖረው ጉዳት ውስጥ ይሄኛው ዋናው ነው። ሁሉም እንደፈለገው ሊናገርህ ይችላል፤ ለሁሉም መልስ መስጠት አትችልም። በዚያ እድል እየተጠቀማችሁ ነው እያልኩህ ነው።

የአይኤምኤፍን ጉዳይ ስንቋጨው፤ ‘አይኤምኤፍ በታሪኩ አድርጎት በማያውቀው መልኩ’፤ የሚያስብል ምንም ነገር የለም። ከሆነም ቅድም ከነገርኩህ የተገኘ ኳሊቲ እንጂ፤ እናንተ እንደምትሉት አየር መንገድን ከገዛበት ደረሰኝ ላይ የተጻፈ አይደለም። ብዙ መሆኑ አስደንግጦህ ከሆነም በግልጽ መናገር ነው። ሌላ ተጨማሪ መረጃ፤ አይኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ ቀጥተኛ በጀት መስጠት ካቆመ 13 አመቱ ነበር። በ2005 የምርጫ ውዝግብ ደስተኛ ባለመሆናቸው ነበር እርዳታውን የከለከሉት። ቀጥተኛ የበጀት ድጎማ ማድረጉን ነበር ያቆመው እንጂ እርዳታ አልተወም ነበር። በጣም መሳቀቅ ከፈለግክም Ethiopia Eritrea Somalia Djibouti የሚል የወወዳጃችሁ የእንግሊዝ በሆነው The Economist Intelligence Unit Limited የታተመ የ1998 ሪፖርት አለልህ። ገጽ 20 ላይ ግለጥና፤ መለስ ዜናዊ ከአይኤምኤፍ ጋር ስላደረገው ስምምነት አንብብ። መዋቅሬን አሻሽላለሁ እሺ ብሎ ስለፈረመው ብድር አንበብ። ESAF ይለዋል አይኤም ኤፍ ያኔ እንግዲህ ብዙ ግብጻውያን አልነበሩም መሰለኝ።

(ይሄ በጣም ተንኮለኛና ቆሻሻ ውንጀላን ያዘለ ግምት ነው።) (መቼም ጠቅላይሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት ባስጎበኙን የቤተመንግሥት ዕድሳት ላይ ‹‹የዓለም ባንክ እርዳታ የሰጠኝ በቢሮዬ ዕድሳት ተማርኮ ነው›› (አላለም፤ ለራስ በሚያመች መልኩ ተመዝዞ የገባ ነው።)

በርካታ ግብፃዊያን ከሚሠሩባቸው ተቋማት አንዱ የዓለም ባንክ ነው፡፡ከሁለት ዓመታት በፊት ግብጽ ‹‹ስለ ሕዳሴው ግድብ የዓለም ባንክ ያደራድረን›› የሚል አማራጭ አምጥታ በኢትዮጵያ ውድቅ ተደርጎባት ነበር፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ቀጥታ በጀት የሚሆን የ1.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መስጠቱ የተሰማው፡፡ ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ ከወራት በፊት ‹‹ያለምንም ቅድመ ሁኔታ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ሰጠን›› ሲሉ ላደመጣቸውም ‹‹አልበላሽምን ምን አመጣው››ን ያስተርታል፡፡

ሁለቱም መንገዶች በዘላቂነት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዱ ብቻ ሳይሆኑ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሥልጣን ዘመንም እንደ አል በሽር የሚያንኮታኩት ነው፡፡(አልበሺርን ያወረዱት አብረው ነው ሊለን ዳር ዳር ሲል ነበር። እዚያ ጋ የአልበሽር አውራጅ፤ እዚህ ጋ ደግሞ እንደአልበሺር ወራጅ ሆኖ ይመጣል።)

(18) ግብፃዊያን ደግሞ በኢትዮጵያ ያላቸውን ጥቅም ለማስከበር አገሪቱን ሲበጠብጡ ቀድመው የሚጠቀሙት የኤርትራንና የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ነው፡፡ጀብሐ/ሻዕቢያ ካይሮ መመስረቱንና በርካታ የኦነግ ክንፍ ከግብጽ መምጣቱን እንዲሁም ከኦሮሚያ አመጽ ጀርባ ግብጽ አለችበት የሚለውን ለእውነት የቀረበ መላምት ያስታውሷል፡፡ለዚያም ሊሆን ይችላል፤ጋዜጠኛው ሳቤር ‹‹ከኢትዮጵያ ጋር ታርቆ በሽርን አወረደው›› ሲል መሪውን ያደነቀው፡፡

የበሽር መውረድ የጠላት ቅነሳ ቅደም ተከተል ነው!! (የው ሲያምታታው! እስካሁን የኤል ሲስ አሽከር አድርጎ፤ የአልበሺር ጠላት አድርጎ የሳለውን ሰውዬ ከአልበሺር ቀጥሎ ያለ ጠላት አድርጎት ደግሞ ይመጣል። አልሲስ ለምን ይጥለዋል፤ አሽከሩ ነው አልተባለም እንዴ?)

ሕዳሴ ግድብና ዐቢይ

‹‹ግዴለም፤ መንግሥት ስመኘውን ላይወደው ይችላል፡፡ግን ያ ሁሉ ሕዝብ በዝናብ መጥቶ አልቅሶ ቀብሮታል፡፡ለዚህ ሕዝብ ክብር ሲል እንኳ አንዲት የኖራ ሃውልት ሊያሠራለት ይገባ ነበር››፡፡

ይህንን ያሉኝ በስላሴ ካቴድራል ግቢ ውስጥ ከሚውሉ አትክልተኞች አንዱ ናቸው፡፡(የተለመደችው ምንጭ ስወራ፤ ከእከሌ ሰማሁ ስታይል! ቢሉትም ስማቸውን መጥቀስ፤ ካልሆነም መተው! )

(በክብር መሸኘቱን ሀገር ያውቃል!!)

ጠቅላይሚኒስትሩ የተሾሙት የሕዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ በተጣለበት ቀን ነው፡፡በበዓለ ሲመት ንግግራቸው ላይም ጠቀስ አድርገውት ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ወደ ግድቡ ቦታ ሄደው (ቤኒሻንጉል ሲጓዙ እግረመንገዳቸውን)

ከስመኘው ሞት በኋላ በ2010 ክረምት በጽ/ቤታቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ሰብስበው ‹‹ይህ ግድብ ለፖለቲካ ፍጆታ የዋለ ነው፤…በሚቀጥለው 10 ዓመትም አያልቅም›› አሉ፡፡ (በቀጥታ እንደዚያ አለማለታቸውን ራሱ ወረድ ብሎ ይነግረናል!) በዚያን ወቅት የግድቡ ግንባታ ቆሞ ነበር፡፡ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮቹም ለዚህ ንግግራቸው ሞቅ ያለ ጭብጨባ ቸረዋቸዋል፡፡ በመሠረቱ አንድ መንግሥት ሥራ የሚሠራው ለፖለቲካዊ ፍጆታው እንጂ ለጽድቅ አይደለም፡፡

ከእርሳቸው በፊት የነበረው ኢሕአዴግ ግድቡን ለፖለቲካ ፍጆታ ቢጠቀመው አያስገርምም፡፡ጥያቄው መሆን ያለበት ሥራውን ሠርቶታል/አልሠራውም? ካልሠራውስ እኔ እንዴት እሠራዋለሁ የሚለው ነው ጉዳይ መሆን ያለበት፡፡ ግድቡ የዲዛይን ክለሳ የተደረገለትና የማመንጨት አቅሙም ከ5250 ወደ 6450 እንዲያድግ የተደረገ ቢሆንም፣ የሀብት ብክነትና የመፈፀም አቅም ችግር እንደነበረበት አይካድም፡፡ይሁን እንጂ ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ እስከተሾሙባት ዕለት ድረስ 65 በመቶ ተገንብቷል፡፡ይህ ማለት በየዓመቱ ከ9በመቶ በላይ ይገነባ ነበር ማለት ነው፡፡እርሳቸው የአገሪቱ መሪ በሆኑበት ባለፉት 17 ወራት ውስጥ ሁለት በመቶ እንኳን አልጨመረም፡፡

(በሜቴክ ምክንያት በ2017 ማለቅ የነበረበት ግድብ ወደ 2022 ተዛውሮአል። የዚህን ኪሳራ ስሌት በተራ ካልኩሌተር መስራት ነውር ነው። የሜጋ ፕሮጀክቶችን ኪሳራ አሰላል ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ በአመት ኮርስ እንዲያስጠኑልኝ በትህትና እጠይቃለሁ። ያልቃል በተባለበት ወቅት ያላለቀን ፕሮጀክት በየአመቱ ይሄንን ያህል ይሰራ ነበር ብሎ ለማነጻጸሪያ ማቅረብ ሞላው መበላሸቱን ይጠቁማል። የ17ወራቱ ስታስቲክስም ውሸትና በማስረጃ ያልተደገፈ ነው። ስልሳ አምስት ፐርሰንት ተጠናቀቀ የሚለውም ድፍንና ከፕሮጀክቱ ጸባይ ውጪ ነው። ሳሊኒ የተባለው ድርጅት ያነሳቸውን ወቀሳዎችና ቅሬታዎች ማዳመጥ ብቻውን የሜቴክን ጉድፎቸ አስምሮ ለማለፍ በቂ ነበር። ራሱ ያየሰውም የአቅም ችግርና የሀብት ብክነት መኖሩን አምኖ ነበር። ለሜቴክ ሀብት ማባከንና የብቃት ማነስ በጣም ተራ ችግሮቸ ስለሆኑ ይሆናል።መለስ ዜናዊ ግድቡን በመጀመሩ ዘላለማዊ ስራ ሰርቶአል። ለሜቴክ በመስጠቱ ግን ዘላለማዊ ስህተት ሆኖ ይመዘገብለታል። ያየሰው ለሜቴክ ዶሜስቲክ አፊሌሽን ምናምን በመፍጠር ለመከራከር ሲሞክር አየዋለሁ። ግድቡ ሎካል ጉዳይ አይደለም። በኢንዲጂኒየስ ፖለቲክስ የምታራቅቀው ወግ አይደለም። ብዙ ውስብስብ ነገሮች አሉበት። እንደሸገር አውቶብስ እየሰራህ የምትማርበት አይደለም (ይሄም ቢሆን ልክ ነው እያልኩ አይደለም)።

በነገርህ ላይ መለስ ቢኖር ኖሮ ወዲያው የሚያደርገውን የማስተካከያ እርምጃ ነው ዐቢይ አህመድም ያደረገው። ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ከሰሩዋቸው ድንቅ ስራዎች መካከል ሜቴክን አይነት የማፍያና እብሪተኛ ካርቴል መበጣጠሳቸው በዋናነት የሚጠቀስ ነው። እስቲ ይህቺን ጋብዙልኝ፤ አንብባት፤ What You Should Know about Megaprojects and Why: An Overview Bent Flyvbjerg, Oxford University, UK) PROJECT MANAGEMENT INSTITUTE የተባለው ተቁዋም ነው ያሳተማት።

"በሚቀጥለው 10 ዓመትም አያልቅም" የሚለውን ንግግራቸውን የተናገሩት ግብጽ ሄደው፣ "ወላሂ ወላሂ አንጎዳችሁም" ብለው ከማሉ በኋላ ነው፡፡ ይህ የ10 ዓመት ዕቅድ ደግሞ የግብጽ ተደጋጋሚ ጥያቄ ነው፡፡ (ይሄ የራስን ውሸት በመቀጣጠል እውነት ከማስመሰል ሙከራዎች አንዱን ይወክላል። )

በነገርህ ላይ መለስ ቢኖር ኖሮ ወዲያው የሚያደርገውን የማስተካከያ እርምጃ ነው ዐቢይ አህመድም ያደረገው። ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ከሰሩዋቸው ድንቅ ስራዎች መካከል ሜቴክን አይነት የማፍያና እብሪተኛ ካርቴል መበጣጠሳቸው በዋናነት የሚጠቀስ ነው። እስቲ ይህቺን ጋብዙልኝ፤ አንብባት፤ What You Should Know about Megaprojects and Why: An Overview Bent Flyvbjerg, Oxford University, UK) PROJECT MANAGEMENT INSTITUTE የተባለው ተቁዋም ነው ያሳተማት።

በርግጥ ‹‹በዚሁ ከቀጠልን በሚቀጥለው 10 ዓመትም አያልቅም›› ነው ያሉት፡፡ በእርሳቸው ዘመን እንዳለው አፈፃፀም ከሆነ (በዓመት 2በመቶ እንኳ የማይሠራበት) ግድቡ ለመጠናቀቅ 17 ዓመታት ይፈጅበታል፡፡ በግድቡ ግንባታ ላይ ሕዝቡ 12 ቢሊዮን ብር (በተለይ የመንግሥት ሠራተኛውና ባለሃብቱ) አዋጥቷል፡፡ይሁን እንጂ ጠቅላይሚኒስትሩ የአንደኛ ደረጃ መምህራንን ሰብስበው ‹‹ብዙ ያዋጣችሁ እንዳይመስላችሁ፣ከ10 በመቶ የሚዘል አስተዋጽኦ የላችሁም›› ብለው የሕዝቡን ሞራል ‹ከሸከሹት›፡፡

(እውነታቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ግድቡ ከፈጀውና ከሚፈጀው ገንዘብ 12ቢሊዮን ብር 10 ፐርሰንት አይሞላም።) ድሃ የመንግሥት ሠራተኛና ወታደር ለልማት ብሎ ያዋጣውን ገንዘብ አጣጣሉበት፡፡

ይህን ንግግራቸው የጠቅላይሚኒስትሩ ንግግር ችግር ይዞ ሲመጣ ዓመት አልሞላውም፡፡አሁን ለግድቡ ተብሎ የሚሸጠው ቦንድ በአንድ ቢሊዮን ብር አሽቆልቁሏል፡፡ (ይሄም መረጃ ያለምንጭ የተጠቀሰና በቆርጦ ቅጠላ የተዋበ ነው። የቦንድ ግዥው መቀነስ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም።

ከሰውየው ስልጣን መያዝ በፊትም የነበረና ብዙ ምክንያቶች ያሉት ችግር ነው።)

ጠቅላይሚኒስትሩ ለቀደመው ኢሕአዴግም ሆነ ለሕወሓት መራሽ አለቆቻቸው የመረረ ጥላቻ ቢኖራቸውም እንዲህ ያሉ አገራዊ ፕሮጀክቶች ከኢሕአዴግም፣ከመለስም፣ከዐቢይም በላይ መሆናቸውን ቢያንስ መገንዘብ ነበረባቸው፡፡

ይህ ውስጣዊ ብሽቀታቸውም በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ እስከመደራደር የሚያደርሳቸው እየሆነ ነው፡፡ ‹‹ድሃ አገር ሉዓላዊነት የለውም›› በማለት፡፡ (ያለቦታው ያለአውዱ የዋለ ሌላ ውንጀላ፤ ‘ይህቺን አባባል’ የቀድሞው የህወሓት አለቃና አሁን ዐብይ አይወደውም ይበሽቅበታል የተባለው መለስ ዜናዊም በሌላ ፎርም ተናግሮአታል። ዐብይ አህመድም እንደሱ አይነት ንግግር ነው የተናገሩት። በደብል ስታንዳርድ የታመመው ተንታኝ እሳቸውን ለይቶ ለመኮነን በቃ። በመጽሃፋቸው የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ፤ ስለድህነታችንና፤ ስለሉአላዊነታችን ያላቸውን አረዳድ በግልጽና በውብ መንገድ አስቀምጠውታል።)

ግድቡ ቢያንስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊተባበርበትና ሊተጋገዝበት፣ ለብሔራዊ መግባቢያም ጥሩ መሣሪያ መሆን የሚችል ነበር፡፡ ሆኖም ከአያያዝ ተሰበረና፣ እንኳን በጋራ ልንግባበት መሪዎቻችንም ሊያምኑበት አልቻሉም፡፡የኤል ሲሲዋ ግብጽ ግን ሥራዋን በንቃት እየሠራች ነው፡፡

ደሴታማዋ የመዝናኛ ከተማ ሶች፣የኢትዮጵያንና የግብጽን መሪዎች አገናኝታለች፡፡ 45 ደቂቃ የፈጀው ውይይት ግብጽ ባለችው መንገድ ተጠናቅቋል፡፡እነሆ የስምንት ተከታታይ ዓመታት ጥያቄዋ መልስ አገኘ፡፡አንድ ጊዜ የዓለም ባንክ ያደራድረን፣ ሌላ ጊዜ አሜሪካ ታሸማግለን ሲል የነበረው የካይሮው መንግሥት ተሳክቶለታል፡፡ አሁን ሁለቱም በአንድ ጊዜ በአንድ ቀን በአንድ አዳራሽ ውስጥ ያለውን ሊፈጽሙ ቀን ቆርጠዋል፡፡ የአዲስ አበባ አቻው ይህ ይሆን ዘንድ ከስምንት ክረምቶች በኋላ በሶስተኛው ጠቅላይሚኒስትር ተስማምቷል፡፡‹‹ከማንም ጋር ብንደራደር ችግር የለውም›› ሲልም እሺታውን ገልፁዋል፡፡

(ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን አንጀት አርስ ነው አቦ! ከማንም ጋር ብንደራደር ችግር የለውም! ከማንም ጋር ብትደራደር አቁዋምህን ካወቅክ ምን ይመጣል?)

ለአፍሪቃ-ሩሲያ ጉባኤ ሶች የተገናኙት የግብጽና የኢትዮጵያ መሪዎች በሕዳሴው ግድብ ላይ የተቋረጠውን ውይይት/ድርድር ለማስቀጠል ተስማምተዋል፡፡

ነገርን ከስሩ

የሕዳሴ ግድብ እንደ አንድ ተራ ፕሮጀክት የሚወሰድ አይደለም፡፡ጉዳዩ ከኃይል ማመንጨትም በላይ ነው፡፡ይህ በተለይ በኢትዮጵያ ላይ ሁለት ነገር አምጥቷል፡፡አንደኛው ይህንን ግድብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ አድርጎ እንዲያስበው በማድረግ፣ ለብሔራዊ መግባባት ግብዓት ሆኖ ነበር (ነበር? እና ዐቢይ አበላሸው አይደል? ለብሔራዊ ኢ መግባባት አዋለው አይደል?) በዚህም ግብጽ ለዓመታት የተወሰኑ ልሂቃን የሚከራከሩለት ወንዝ ብቻ አድርጋ የምታስበውን አባይን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚቆረቆሩለት እንደሆነ እንድትገነዘብ አድርጓል፡፡ (ይሄ ነው ባለልከኝ ተራ ፕሮጀክት ላለመሆኑ ማሳያው? ‘የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው’ የሚለው ተረት ከህዳሴ ግድቡ በሁዋላ ነዋ የተተረተው? የግድቡ መሰረት ሲጣል ነዋ ለጂጂ ግጥምና ዜማውን የሰጣችሁዋት? አባይ አባይ የሚለው የቁጭትና የመብሰክሰክ መዝሙር መቼ እንደተሰራ አዋቂ ሰው ጠይቅ። ይሄንን መቆርቀር ግብጽ ዛሬ አይደለም የምታውቀው!)

ሁለተኛው በዲፕሎማሲ የሚገለጽ ነው፡፡ለዘመናት ‹ታሪካዊ መብቴ ነው› በምትለው የአባይ ወንዝ ላይ ለውይይት መቀመጥ የማትፈልገውንና ስለወንዙ በተለይ ከኢትዮጵያ ጋር መነጋገርን እንደ ግዴታ የማታየውን ግብጽን ለፍትሐዊ ድርድር ወደ ጠረጴዛው አምጥቷል፡፡ (ውሸት! ከግድቡ በፊት ሌላ ብዙ መወያያ መድረኮች ነበሩ! የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ የተመሰረተው በ1999 ነው። ዋና ግቡም የተፋሰሱን ሀገራት ለጋራና ለዘላቂ ጥቅም በአንድ ማዕድ ዙሪያ ማስቀመጥ ነው። ግብጾቹ ከህዳሴ ግድቡ መጀመር ይልቅ የኪንሻሳው ስምምነት (የትብብር ማዕቀፉ) የበለጠ ለሽንፈታቸው አስተዋጽኦ አድርጎአል። Unstable power structure, regional disagreement : Water politics along the Nile የሚለውን የ Nizar Manek ጽሁፍ አንብበው። ግድቡ የኪንሻሳው ስምምነት ውጤት ነው የሚሉም ብዙ አሉ። ካንተ ይሻሉኛል። የተፋሰሱ ሀገራት በኢኒሼቲቩ እንቅስቃሴ ውስጥ የግብጽን አይን አውጣነት በደንብ ለመታዘብ ጊዜ አግኝተዋል። ያ ነው ወደ ጋራ አቁዋም የመራቸው። ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ በ 2011፤ Negotiations for a Nile-Cooperative Framework Agreement ሲሉ ISS ላይ ያስነበቡትን ጽሁፍ አየት አድርገው። ከግድቡ በፊት ስለነበሩ ግብጽን ወደ ትበብር ውይይት ለማምጣት ስለሞከሩ ኢኒሼቲቮች ጥሩ ገንዛቤ ይሰጥሃል። ፌክ እና እኛን አግላይ ቢሆኑም፤ Hydromet (1967)፤ Undugu in (1983፤) እና Tecconile (1992) የተሰኙ የትብበር ማዕቀፎች ከተወሰኑ የተፋሰሱ ሀገራት ጋር . ልታካሂድ ሞክራ ነበር። ‘በትብብር’ መንፈስ ወደጠረጴዛ ዙሪያ በማምጣት ከ1999–2010 የዘለቀውንና በናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ አማካይነት የተካሄደው ድርድር ቀድሞ ይጠቀሳል። በአጭሩ የሲኤፍኤው ደርድር ልንለው አንችላለን። ነገርዬው፤ Cooperative Framework Agreement ይባላል። የትብብር ማእቀፍ ስምምነት ልንለው አንችላለን። የተፋሰሱን ሀገራት በ1997ቱ በተባበሩት መንግስታት የውሃ ህግ መሰረት የሚያስተዳድር ማእቀፍ ነው። የተፈጥሮ ሀብታቸውን በእኩል እና በምክንያታዊ መርሆች እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ ድንጋጌ ነው። የናይል ተፋሰስ ሀገራትም የዚህ አለማቀፋዊ ድንጋጌ ተገዥ ናቸው። በትብብርና፤ ጉልህ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ ሀብታቸውን የሚጠቀሙበተን መንገድ ለመዘርጋት የደከሙበት ጉዞ ነበር። ‘በተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሚኒስቴሮች ካውንስል አማካይነት ለ10 ዓመታት የተደረገው ውይይት በልዩነት ነበር የተጠናቀቀው። ልዩነቱን የፈጠረው በሰነዱ አንቀጽ 14(b) ላይ ያለው ሀሳብ በሱዳንና ግብጽ በኩል ተቀባይነት በማጣቱ ነው። ‘በተፋሰሱ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ ” የሚለውን፤ ግብጽና ሱዳን ‘ ‘…አሁን ባለው የውሃ ተጠቃሚነት እና መብት ላይ ጉዳት የማያደርስ’ በሚለው ይስተካከልልን ብለው ጥለው ወጡ። ግንቦት 2009 ኪንሻሳ ላይ በተካሄደው ጉባኤ፤ ሰባት ለአንድ በሆነ ድምጽ ማዕቀፉ ተቀባይነት አገኘ። ግብጽና ሱዳንን ለማካተት የተደረገው እልህ አስጨራሽ ሙከራም ሳይሳካ ቀረ።’ ይላል የዶክተሩ ሰነድ። ይህን ሰነድ ጥለው በመውጣታቸው ብቻ የአለማቀፉን የውሃ ህግ መሰረታዊ መርሆች ጥሰዋል። ‘አሁንም በአግላዮቹና ለእኛ ብቻ በሚሉት የቅኝ ግዛት ዉሎች እንቀጥል’ ማለታቸውን ያረጋግጥልናል። ይሄ እነሱን እንጂ እኛን የሚጎዳበት ምንም መንገድ የለም። ለዚያ ነው ግድቡን ሳናማክራቸው በራሳችን ውሳኔ ብቻ የጀመርነው። የእኛ ድርሻ ጉልህ ጉዳት አለማድረስና በፍትሃዊ አጠቃቃም ላይ መመርኮዝ ብቻ ነው። ለአለም አቀፉ ህግ ተገዢ ቢሆኑ ኖሮ፤ ዲዛይኑንም አብረን ልንሰራው በቻልን (ህጉ ይላል አላልኩም፤ ፍቅራቸው ይሉኝታ ካሲያዘን ብዬ ነው)። ግብጽ ህዳሴ ግድቡን ከመጀመር ያላገደችው አመክንዮአዊም ህጋዊም ሞራላዊም መሰረት ስሌላት ነው።

‹‹ግብጽ በናይል ወንዝ ዙሪያ ምንም ዓይነት የትብብር መንፈስ ለማሳየት ፈቃደኛ ሳትሆን ለረዥም ዘመናት የቆየች አገር ነበረች፡፡የናይል ወንዝ ድንበር ዘለል ባሕርይ ያለው መሆኑን እስከመካድ የሚደርስ አካሄድን ስትከተል የቆየችም አገር ነበረች፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ መጋቢት 23-2015 (እ.ኤ.አ) ለዓለም አቀፍ ሕግ ተገዢ በመሆን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ስምምነት መምጣቷ ታላቅ እርምጃ ነው›› ይላሉ፡፡ (ሰውዬው እንዲህ ብለው ጽፈው ከሆነ፤ በእውነቱ መጽሃፉን ባለማንበቤ ደስታ ይሰማኛል። ጸሃፊው የህወሓት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ናቸው። ይሄንን ሰነድ የሚያጋንኑበት ምክንያትም ከሰነዱ ቅሽምና ጋር የተያያዘ ነው።ቀደም ሲል እንደገለጽኩት በዚህ ስምምነት ሳቢያም አይደለም ግብጽ ወደ ድርድር የመጣችው። ሰነዱ ምን ያህል ቀሽም እንደሆነም ወረድ ብዬ አመለስበታለሁ)

በዚህ መልኩ ብሔራዊ ሕብረትንና የዲፕሎማሲ ድልን ያጎናፀፈው የሕዳሴው ግድብ አሁን እነዚህን ሁለት ውጤቶቹንም እያጣ ይመስላል፡፡ በአንድ በኩል ግድቡን በተመለከተ የአሁኑ መንግሥትና መገናኛብዙሃን ካላቸው አተያይ ይመነጫል፡፡

ግድቡን ‹50 በመቶም ያላለቀ፤የተዘረፈ፤ለፕሮፓጋንዳ ሥራ ተብሎ የተጮኸለት፤ሕዝቡም 10 በመቶ እንኳን ያላዋጣለት፤ የጥራት ችግርም ያለበት› እንደሆነ በተለይ ጠቅላይሚኒስትሩ ደጋግመው መናገራቸው ግድቡ ፈጥሮት የነበረውን ብሔራዊ የልማት መነቃቃትና መግባባት ውሃ ቸለሰበት፡፡የአገሪቱ መገናኛብዙሃንም እንደ ግብፃዊያን ግድቡን ማራከስና ስም ማጥፋት ቀጠሉ፡፡ (ይህቺን በመጀመሪያው ጽሁፍ ውስጥ ተችቻታለሁ። እዚህች ጋ አዲስ ነገር የተጨመረችው፤ ሚዲያዎቹ ግድቡን አራከሱ ስም አጠፉ የምትለው ነገር ናት። ውሸት! ሚዲያዎቹ ግድቡን አራክሰውም አያውቁም፤ አዎ ሜቴክን ወቅጠውታል። ሲያንሰው ነው። ሜቴክን ማራከስ ደግሞ ግድቡን ማዋደድ ነው። ካንተ የማያንስ የሀገር ፍቅር ያላቸው ጋዜጠኞች ብዙ አሉ። ፌዴራሊዝሙንም ካንተ በተሻለ ደረጃ የሚረዱ (ደራን አላውቃትም ሳይሉ መቀሌን ጽቡቅ የሚሉ) ብዙ የሰሜን ሸዋ ልጆችም ይኖራሉ። ለቫራይቲ ከፈለግካቸው ብዬ ነው። ሌላውን ግርግር ተይው ያየሰው! ‘ብሄራዊ ስሜቱ ላይ ውሃ ቸለሰበት’ ምናምን የምትለውም ተራ ሴንሴሽናላይዜሽን ናት። ብሄራዊ ስሜት ሲኖር እኮ ነው የሚቸልስበት፤ ህወሓት ቀድሞ ቸላልሶ የጨረሰውን ዐቢይ ከየት አምጥቶ ነው የሚቸልስበት?) ከዚያም ስለዚህ ግድብ የሚጽፍ፣የሚናገርና የሚከራከር ልሂቅ አነሰ፡፡ በአንድ ጊዜ 1300 ሜጋ ዋት እንዲቀንስ ሲደረግ እንኳ የሚቆጭ ጠፋ፡፡ (አልተቀነሰም! የተርባይን ቁጥር እንጂ ሀይል አልተቀነሰም። ያየሰው ለሚፈልገው ሀሳብ ማጠናከሪያ ነው ሀቁን ያዛበው። ወረድ ብዬ አብራራለሁ ) መገናኛ ብዙሃንና መሪዎቻችን ከግብፃዊያን በበለጠ ስለዚህ ግድብ አፍራሽ ዘመቻ ከፈቱ፡፡

እዚህ ጋር ግልጽ መደረግ ያለበት ነገር አለ፡፡

(በነገራችን ላይ፤ በ2014 ማርች ላይ፤ አስር አባላት ያሉትና በሶሰቱ ሀገራት አማካይነት የተደራጀው የሶስትዮሽ የቴክኒክ ኮሚቴ ባወጣው ሪፖርት ዙሪያ ከባድ ወዝግብ ነበር። ሪፖርቱ ላይ ኢትዮጵያም ማስተካከል ያሉባትን ነገሮች ተቀብላ ስራዋን ቀጥላለች። ግድቡ መቆም አለበት እስከሚለው የከከረረ ውዝግብና ፤ ተሰርቆ ቀድሞ ስለወጣው ሪፖርትም በሀገር ደረጃ መግለጫ የተሰጠበት በጭቅጭቅ የተሞላ አመት ነበር። ሰውዬው የመጡት መስከረም 21 2014 ነበር። ጎብኝተው ሲመለሱ ለአልሞኒተር የሰጡትን ቃለምልልስ የተወሰነውን ቃል በቃል ማንበብ ነው። አንዳችም ቦታ ስለ ግድቡ ጥራት ጠብቆ መገንባት የተናገሩት ነገር የለም። እንዲያውም በተቃራኒው ነው ያወሩት። በግንባታው ፍጥነት ገን ረክቻለሁ ብለዋል። እንግዲህ በእሳቸው ዘንድ እርካታ ከፈጠረ እንደተንታኝ መጠርጠር ነበር አንጂ፤ ለራስ ፍጆታ ግብጻዊን ማስዋሸት ትንሽ አስቂኝ ነው። የእስከዛሬውንም ውሸታቸውን አልቻልነው። ስለቴክንክ ችግሩ ነው ያግድቡን መጎብኘቴ በግድቡ መስማማቴን አያመላክትም። የሚል ቃላቸውንም ሰጥተዋል። የውሃ ድርሻችን እንደማይነካ ማረጋገጫ አግኝቼ ነው የተመለስኩት ሁላ ብለዋል። ያው ከዜናው መካከል የቀነጨብኩት። ሙሉውን ዜና ለማንበብ ደግሞ፤ Egyptian visit to Ethiopian dam raises hopes for resolution በሚል ርእስ EECCA ላይ ያገኙታል። 15 October 2014 ነው የወጣው።

 In an interview with Al-Monitor, Moghazy said, “We have assurances from the Ethiopian side that there will be no prejudice to the amount of water flowing to Egypt from the Ethiopian plateau through the eastern Nile. My visit with Ethiopia’s water minister is strong evidence that there are good intentions.”

After Moghazy returned from Addis Ababa, he said the visit did not and would not necessarily mean that Egypt has agreed to the building of the dam based on the current specifications. This visit proved controversial in some decision-making circles, with a fear that the visit would be misinterpreted as Egypt’s implicit approval for the construction of the dam without conditions.

Moghazy said, “We have not yet agreed upon the dam’s stated specifications and our final decision will depend on the results of studies to be conducted by an international consultancy bureau, in collaboration with the national committee of experts.”

Moghazy affirmed that, “My visit to the dam’s site was not political, but rather technical.” But the minister expressed satisfaction at the pace of construction. “I have found that construction works at the dam’s site are preliminary, ranging between 15-20%,” he said.

 “Technically, the storage of water and generation of electricity are not possible in the first stage, as Ethiopia says, in September 2015.” He also said, “The topographic nature in the dam’s area does not allow the water stored behind the dam to be exploited in agriculture.”

 Nevertheless, in an interview with Al-Monitor, Mahmoud Abu Zeid, head of the Arab Water Council and expert in water management, said it is not technically feasible to judge the dam’s details from one quick visit by a minister.

  “It would have been better to put off the minister's visit to Ethiopia and the dam’s site until the national committee completed its work and until we made sure that Ethiopia will be committed to the results of the studies on the dam’s impact on Egypt’s water interests,” he said.

“የእኛ መሪዎች ግን ከግብፃዊያንም በላይ ግድቡን ስም ማጥፋት የጀመሩት ሥልጣኑን በያዙት ማግስት ነበር፡፡ በግድቡ ላይ ገንዘብ አባክኗል ተብሎ ዶክመንተሪ የተሠራበት ሜቴክ ነው፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ በዚህ ጥፋት የተከሰሰ አንድም የኮርፖሬሽኑ አመራር አለመኖሩን ስንመለከት፣ይህ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ኩራት የሆነ ግድብ ስሙ እንዲጠፋ የተደረገው በየትኛው አገር ትዕዛዝ ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ (አለመከሰሳቸው ብቻውን ነጻ ስለመሆናቸው ማስረጃ ሆኖታል ማለት ነው? በግብጽ ትዕዛዝ ሜቴክ ለመመታቱም ማስረጃ ሆኖታል የሰዎቹ አለመከሰስ፤ ያው የእነ ክንፈን አናካትተውም፤ ከመታሰሩ በፊት ነው የጻፈው። የሜቴክ ባለስልጣናት አብዛኞቹ ያልተቀፈደዱትን ምክንያት ሀገር ያወቀዋል። ቆይቶም የተፈረደባቸወ አሉ!)

ሁለተኛውና ኢትዮጵያ በዚህ ግድብ ያሳካችው ዲፕሎማሲያዊ ድልም፣ አሁን እየተቀለበሰ ነው፡፡ ግብጽን ከታሪካዊ ባለቤትነት ወደጋራ ልማት ስሜት ያመጣው ይህ ፕሮጀክት፣ለውይይትም አስቀምጧታል፡፡

በአንድ በኩል፣በሌሎች ግድች ላይ የነበረው (ለምሳሌ ጊቤ) ዓለማቀፋዊ መንጫጫት በሕዳሴ ግድብ ላይ አልነበረም፡፡ ከግብጽ በስተቀር ይህንን ግድብ የተቃወመ፣የተቸ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ አለው ያለ አገር፣ድርጅት፣አለያም መሪ የለም፡፡ (በ2017 አረብ ሊግ በከረረ ተቃውሞ አውግዞታል፤ ዐቢይ ያኔ ስልጣን ላይ አልነበረም። Arab League “extreme concern” over Ethiopia’s Nile dam 27 November 2017 ላይ የወጣ ነው። ኤርትራም ዛሬ ነው የደገፈችው፤ ያኔ ሀገር አልነበረችም አይደል? ድሮስ ኤርትራና አረብ ሊግ ግድቡን ሊደግፉ ነበር ወይ? የሚለውን ጥያቄ፤ በሌላ ጥያቄ እመልሰዋለሁ፤ ድሮስ ያየሰው እና ህወሓት የዐቢይ አህመድን መንግሰት ሊደግፉ ነበር? የተቃወመ ድርጅት የለም የሚለውን እንተወው።)

ይህም ግብጽን ብቻዋን ያስቀረና ኢትዮጵያም ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ሥራ መሥራቷን ያሳያል፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ግብጽ ሳትወድ ወደ ድርድር እንድትመጣ አድርጓል፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታትም ሄድ መጣ እያለች ስትደራደር ከረመች፡፡

ግድቡ ቆሞ እንነጋገር ብትልም፣ በኢትዮጵያ በኩል አወንታዊ ምላሽ አላገኘችም፡፡ የግድቡ ቁመት ይነስ፣የማመንጨት አቅሙም ይቀንስ፤ የሚይዘው ውሃ አነስተኛ ይሁን፤ ተርባይኖች ይቀነሱ ወዘተ የሚል ጥያቄ ስታቀርብም፣ከኢትዮጵያ በኩል በዚህ ላይ ድርድር የለኝም ስትባል ከረመች፡፡

በመጨረሻም መጋቢት 23፣2015 (እ.ኤ.አ) ኢትዮጵያ ጥቅሟን ያስከበረችበትን ድንቅ ስምምነት ተፈራረመች፡፡ (ምንም የተከበረ ጥቅም የለም። የተደፈረ እንጂ። የተከበራችሁ አንባቢዎች፤ ያየሰውና አለቆቹ በ2015 ከግብጽና ከሱዳን ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ (Declarations of Princeples) አለ። እሱን ነው፤ ድንቅ አያለ የሚያሞካሸው። አለቆቹም ይኩራሩበታል። ግብጽን ያንበረከክንበት ነው ይሉታል። አዋቂዎች ገን ይስቃሉ። ምክንያቱም ሰነዱ በብዙ ነገሩ የግብጽን ወገብ ያጠና ነው። በዚህ ሰነድ ውስጥ ዛሬ ዐቢይ አህመድ አደረጋቸው እየተባሉ ለወቀሳ መዋያ የተደረጉ ነጥቦች በሙሉ ተካትተውበታል።

Declaration of Principles on the Grand Ethiopian Renaissance Dam: Some Issues of Concern  የሚለው የደረጄ መኮንን ጥናት የእነያየሰውን ድንቅ ስምምነት በጥልቀት ይተቸዋል። እንግዲህ የኪንሻሳውን የትብብር ማእቀፍ አንቀበልም ካሉት ሀገራት ጋር ነው፤ በ2015 ሌላ ሰነድ የተፈራረምነው። ዋናው ችግር ከዚህ ይነሳል። ለአለም አቀፍ ስምምነት ተገዥ አለመሆናቸውን የCFAውን ሰነድ ባለመፈረም ካረጋገጡልን አካላት ጋር ምን አይነት የትብብር ውል ነው የምናስረው? የሚለው ጥናቱ፤ 2015ቱን ስምምነት የአለም አቀፍ የውሃ ድንጋጌዎችንና የኢትዮጰያን ጥቅም አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ያብራራል። ‘የግድቡን ውሃ ለሀይል ማመንጫ ብቻ ነው የምንጠቀምበት’ ብለን በመፈረም፤ የግብጽን የቅኝ ግዛት ኮታ በእጅ አዙር እንደማንነካ ማስተማመኛ ሰጥተናል። ይሄንን አለማቀፋዊ ህግም የማይደግፈውና፤ ዛሬም ቦይነታችንን በፊርማ ያረጋገጥንበት፤ ዛሬም በተፈጥሮ ሀብታችን ለመጠቀም የሌሎች ፈቃድና ይሁንታ እንደሚያስፈልገን የተስማማንበት ሰነድ ነው። ይሄም ብቻ አይደለም በሲኤፍኤው ላይ ያልተስማሙባቸውን የቃላት ጉዳዮችም ‘በአሻሚ መልኩ ክፍት አድርገው እንዲተዋቸው እድል ከፍቶላቸዋል። የአቶ ደረጀ ጥናት፤ ሌሎች የስምምነቱን ከባባድ ድክመቶችም ቃኝዋቸዋል። ተመልከተው!

ይልቅ እኔ ሰነዱን ሳነብበው፤ የታዩኝን አንድ ሁለት ነጥቦች ልጨምርና ያየሰው አንደሚለው ‘ድንቅ’ አለመሆኑን አመላክቼ ልለፍ። በሰነዱ አንቀጽ 4 ላይ የግድቡን ውሃ አሞላልና ፤ አጠቃቀም በተመለከተም መጀመሪያ ሶሰቱ ሀገራት መስማማት እንዳለባቸው በግልጽ ተቀምጧል። ወረድ ይልና ደግሞ፤ ‘ከሚመረተው ሀይል ግብጽና ሱዳን ቅድሚያ  የመግዛት መብት ይሰጣቸዋል’ ይላል፤ በቶሽካና በሜሮኢ መስኖዎች ከሚያመርቱት ሽንኩርት አቅምሰውን ከማያውቁ ና ባስ ሲልም የሽንኩርት ፖለቲካ ሲጫወቱብን ለኖሩ ሀገራት እንዲህ አይነት ችሮታ የሆነ አዝናኝ ነገር አለው።

የመጨረሻዋን ትዝብቴን ልጨምር፤ በአጋጣሚ ይሄንን ስምምነት ከሁለት ምንጮች ወስጄ ነበር ያነበብኩት።  ከHorn affairs ላይOfficial Text: Egypt, Ethiopia, Sudan – Declaration of Principles  የሚለውንና ከAhram Online ላይ ደግሞ  Full text of 'Declaration of Principles' signed by Egypt, Sudan and Ethiopia በሚል ርእስ አግኝቼ ነው። በሁለቱ ሰነዶች ላይ አንዲት አስገራሚ ልዩነት አጋጥማኛለች። ሙሉ በሙሉ አሰፍራታለሁ፤ ክፍል 4(b) እና 5(b) ላይ ያገኙታል።

  1. Agree on guidelines and rules for the annual operation of GERD, which the owner of the dam may adjust from time to time.
  2. An agreement on the guidelines and annual operation policies of the Renaissance Dam, which the owners can adjust from time to time

ባለቤት እና ባለቤቶች የሚል ወግ እንዳይመጣ ስጉልኝ ብቻ!! የያየሰውን ርእስም ከ’ሶች እንደውጫሌ’ ወደ ‘ካርቱም እንደ ውጫሌ’ ማስተካከያ እንዳያደርግ……..በአርግጥ ጋዜጣው በፈለገው መነገድ ተርጉሞት ሊሆን አንደሚችል ይገመታል።

ቢሆንም…

ይሁን እንጂ ግብጽ በዚህ የምታቆም አልሆነችም፡፡ ሶስተኛ ወገን ያደራድረን ብላ የዓለም ባንክን አማራጭ አቀረበች፡፡ ኢትዮጵያ በአንፃሩ እራሳችን መነጋገር እንችላለን ብላ ተቃወመች፡፡

አድካሚው ድርድር ከተካሄደ ከዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ የአስተዳደር ለውጥ ተደረገ፡፡ የተቀየረው መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ግድቡን በተመለከተ ከላይ የተዘረዘረውን ጉዳት በኢትዮጵያ ላይ አድርሶ፣ (የተለወጠው መንግስት ግድቡ ላይ ምንም ያደረሰው ጉዳት እንደሌለ አይተናል።) የግብጽን ጥያቄዎች አንድ በአንድ መመለስ ጀመረ፡፡ በአንድ ጊዜ ሶስት ተርባይኖች ቀነሰ፡፡ (ምንም የተመለሰ ጥያቄ እንደሌለም አይተናል) የግድቡን የማመንጨት አቅም በ1300 ሜጋ ዋት እንዲቀንስ አደረገ፡፡ በዚህም ከ6450 ወደ 5150 ሜጋ ዋት ወረደ፡፡ (ይህንን የተናገሩት የውሃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ናቸው)፡፡ (በዚህ የያየሰው መረጃ ውስጥ አስገራሚ ስህተትና ጥፋት እንዲሁም ውሸት ተካትቷል።

ሲጀመር 6450 የሚለው ወደ 6350ሜጋ ዋት መስተካከል ይኖርበታል። ዶክተሩ ከተናገሩት ውስጥ ለራስ በሚመች መልኩ ቆርጦ በማውጣት የተሰራ የመረጃ ሸፍጥ አለ። ሰውዬው እንዲህ ነው ያሉት፤  ግድቡ ቀደም ሲል ተደረገለት በተባለው የዲዛይን ማሻሻያ 6 350 ሜጋ ዋት ኃይልን እንደሚያመነጭ ታስቦ ነበር፡፡ ይህ ኃይል የሚመነጨውም በወቅቱ ይተከላሉ በተባሉ አስራ ስድስት ተርባይኖች በኩል ነው፡፡ ከአስራ ስድስቱ ተርባይኖች መካከል አስራ አራቱ እያንዳንዳቸው 4 መቶ ሜጋ ዋት ሁለቱ ደግሞ እያንዳንዳቸው 3 መቶ 75 ሜጋ ዋት አመንጭተው ነው በድምሩ 6 350 ሜጋ ዋት ኃይልን የሚያስገኙት፡፡ ተርባይኖቹ በሰዓት 15 692 ጊጋ ዋት ኃይልንም ያመነጫሉ፡፡ ሆኖም ይህን ሀይል ለማግኘት ተርባይኖቹ ከዓመቱ ቀናት ውስጥ 28 ነጥብ 2 በመቶ ያህሉን ወይም በዓመት ውስጥ 2 471 ሰዓታትን አለበለዚያም በዓመት ውስጥ 103 ቀናትን መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የተርባይኖቹ ቁጥር ወደ 13 ዝቅ ሲል ግድቡ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫል ፡፡ ይህን ለማግኘትም 11 ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 4 መቶ ሜጋ ዋት ቀሪዎቹ ሁለት ተርባይኖች ደግሞ እያንዳንዳቸው 3 መቶ 75 ሜጋ ዋት ኃይልን ማመንጨት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚመነጨው የኃይል መጠን ግን ቀደም ሲል ታቅዶ ከነበረው (6 350) 1 2 መቶ ሜጋ ዋት ያነሰ ነው፡፡ይህ የተርባይኖቹ የማመንጨት ዐቅም እና የስራ ሰዓት ባለበት ሆኖ ነው፡፡  ሆኖም የተርባይኖቹን የስራ ሰዓት ከዓመቱ ቀናት ውስጥ 34 ነጥብ 8 በመቶ ወይም በዓመት ውስጥ 3 66 ሰዓት አለበለዚያም በዓመት ውስጥ 128 ቀናት በማድረግ ተርባይኖቹ በሰዓት እንዲያመነጩ ታስቦ የነበረውን 15 692 ጊጋ ዋት ኢነርጂን ማግኘት ይቻላል። የተርባይኖች ቁጥር ቢቀንስም ግድቡ ተመሳሳይ የሀይል መጠንን ያመነጫልበዚህም እስከ 210 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለመቆጠብ የሚያስችል  ነው።


Image

ከላይ የሚታየው ፎቶ በማብራሪያው ወቅት ከቀረበው ሰነድ ላይ የተወሰደ ነው። ፎቶውንም ሆነ ንግግሩን (ለራሳችን በሚመች መልኩ የቀናነስነው አለ) የወሰድነው፤ አል ዐይን ከተባለው የመረጃ ምንጭ ነው።

ሰውዬው እንዲህ በቀላሉና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ያብራሩትን ነው፤ ያየሰው ተንታኙ በራሱ መንገድ ተርጉሞ ያቀረበው።)

የሶስተኛ ወገን አደራዳሪነትን ተቀበለ፡፡ ግብጽ የውሃ ሙሌቱ በ7 ዓመት ይሁንልኝ ስትልም ተስማማ፡፡ (በነገርህ ላይ፤ የ2015ቱ ስምምነት፤ እርስ በርስ ካልተስማሙ በየሀገራቸው መሪዎች ምክር ሀሳብና አደራዳሪነት ይመራሉ ይላል። ይሄንን ተከትለው ሁለቱ መሪዎች ገብተውበት ይሆናል። ይሄም ለሶስተኛ ወገን አደራዳሪነት መግባት ዋናው በር ከፋች ተደርጎ መወሰድ አይችልምን?። ያን ያህል አናሊቲካል እይታ አይፈልግም። ግብጽ በሰባት አመት ብላ የምታወቀው መቼ ይሆን? )

የግድቡን የቁመት መጠንም አስቀድሞ ከ80 በመቶ በላይ ስለተገነባ ነው እንጂ፣እዚህም ጋር የግብጽ ጥያቄ ሊመለስ የሚችልበት እድል አይኖርም ብሎ መናገር አይቻልም፡፡ አሁን የቀረበው ጥያቄ ‹አስዋን በተራበ ቁጥር ከሕዳሴ ግድብ ውሃ ልቀቁለት› የሚልና መሠል ሉዓላዊነትን የሚጋፋ ዕቅዷ ነው፡፡ በሩሲያ ሶች የነበረው፣የዐቢይ አሕመድና የኤል ሲሲ ውይይት ይህንንም ፈር አስይዞት ሊሆን ይችላል፡፡

እስካሁን ባለው ሁኔታ ግን ሌላው ቀርቶ ግብጽ ከኢንቴቤው ስምምነትም ሆነ ከናይል ቤዚን ኢኒሽዬቲቭ የወጣችባቸውን ስምምነቶች እኛ በጓሮ በር ተቀብለናል፡፡ (ለምን ከናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ እንደወጣች ተናግሬያለሁ። ሱዳንም አብራ መውጣቱዋን እንዳትረሱ። በጓሮ በር ማን እንደተቀበለም በመረጃ አስነብቤያለሁ። ያየሰው ማለት ይህቺ ናት። ውሸታም፤ ከመረጃ ሩቅ! ከእውቀት ጽዱ!)

የሶች ስምምነት

ግብጽ የሕዳሴ ግድብን ዓለማቀፋዊ ገጽታ በማላበስ እንዴት እየሠራች እንደሆነ ከወር በፊት የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ መነሻ በማድረግ ከአሁን በፊት በዚሁ መጽሔት ላይ በስፋት አንብበናል፡፡ በወቅቱ ኤል ሲሲ በጉባኤው ላይ ከተናገሩ በኋላ አሜሪካ እንድታደራድራቸው በይፋ ጠይቀው ነበር፡፡

ትንሽ ቆይታም እኔ ላደራድራችሁ አለች፡፡ግብጽም አስቀድማ የሠራችው ሥራ ስለነበር ከብርሃን ፈጥና ‹አዎ!አደራድሪን› አለች፡፡ በዚህ መሀል የጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ የኖቤል ሎሬትነት ይፋ ሲደረግ ኤል ሲሲ ተሸቀዳድመው ደውለው ‹እንኳን ደስ አለህ› አሉ፡፡የግብፁ ፕሬዚዳንት የዲፕሎማሲ ረቂቅነት የሚመጣው እዚህ ጋር ነው፡፡‹የሠላም ሎሬት ሆነህማ በግድብ ምክንያት የምጠይቅህን እምቢ ብትል እንደ ሠላም ጠልና ጦረኛ ትቆጠራለህ› የምትል ይዘት ያላት ‹የደስታ መግለጫ› ነች፡፡ከዚያም ሩሲያ ለመገናኘት እንደተስማሙ ተዘገበ፡፡ ከሳምንት በኋላ ጠቅላይሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ ቀርበው፣‹ፕሬዚዳንት ሲሲን አውርቻቸዋለሁ፤በቅርቡም እንገናኛለን፤እንወያይበታለን›› አሉ፡፡እንዳሉትም በማግስቱ በሩሲያ ሶች ተገናኙ፡፡

አሁን ጥያቄው በሩሲያ ተገናኝተው ምን ተስማሙ የሚለው ነው፡፡ተከትለዋቸው ለሄዱት የመንግሥት መገናኛብዙሃን ጠቅላይሚኒስትሩ ሲናገሩ ‹ግብፃዊያን በኢትዮጵያ መጥተው ችግኝ እንዲተክሉ ያቀረብሁትን ጥያቄ ፕሬዚዳንቱ በአወንታ ተቀበሉኝ› በማለት ነው፡፡ይህ መልካም ነው፡፡

ሶስተኛ ወገን ያደራድረን የሚለውን የግብጽን የዘወትር ጥያቄ እንዴት እንዳስተናገዱት ሲጠየቁ ደግሞ ‹‹ግብጽና ኢትዮጵያ በጣም ትላለቅ አገራት ስለሆኑ በእነርሱ መካከል የሚፈጠር ችግር አፍሪቃ ላይ አደጋ ያመጣል የሚል ፍራቻ ስላላቸው፣ራሺያን ጨምሮ በርካታ አገራት ጣልቃ መግባት ማወያየት ይፈልጋሉ፡፡ ፖለቲካዊ ውይይቱን ከማንም ጋር ብናደርገው ችግር የለውም››አሉ፡፡

እዚህ ጋር አስገራሚ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ጠቅላይሚኒስትሩ  ‹‹ከማንም ጋር ብናደርገው ችግር የለውም› ያሉት በውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ መሪነት እየተደራደረ ያለው የኢትዮጵያን ቡድን የሶስተኛ ወገን አደራዳሪነት አስፈላጊ እንዳልሆነና ኢትዮጵያም እንደማትቀበለው በይፋ ከገለፀ ከአንድ ሳምንት በኋላ መሆኑ ነው፡፡ ከዚያ ቀጥሎ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን አሜሪካ ልታደራድር መወሰኗንና የዓለም ባንክም በአደራዳሪነት እንደሚሰየም ዘገቡ፡፡

በተለይ አሜሪካና የዓለም ባንክ ከግብጽ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው ናቸው፡፡ የካይሮው መንግሥት በየዓመቱ ከዋሽንግተን እስከ ስድስት ቢሊዮን ዶላር የሚሠጠው (ለጦሩ) እና በመንግሥታት መቀያየር ውስጥ ያልዋዠቀ ወዳጅነት ያለው ነው።
 
ግብጽ ለዓመታት በሠራችው ሥራ የግድቡ ፋይናንስ ከውጭ እንዳይገኝ አድርጋለች፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ ኃላፊነት ይዛ ተነስታለች፡፡ከሳምንት በፊት Forum for Social Studies ባዘጋጀው መድረክ ላይ ሕሩይ አማኒኤል (ጡረተኛ አምባሳደር)
 
ጠቅላይሚኒስትሩ በእነዚህ አማካኝነት ለመደራደር ነው እንግዲህ፣ካቢኔያቸውንም ሆነ በጉዳዩ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ሳያማክሩ ተስማምተው የመጡት፡፡ይህም ለዘመናት በግብጽ በኩል ሲጠየቅ የነበረ በመሆኑ ለካይሮ ትልቅ ድል ነው፡፡ኢትዮጵያን ግን ዋጋ የሚያስከፍላት በብዙ መልኩ ነው፡፡በአንድ በኩል፣ ‹ሕዳሴ ግድብን በጋራ እናስተዳድረው› የሚለው የግብጽ ሉዓላዊነትን የሚጋፋ እቅድ፣አደራዳሪ ትሆናለች በተባለችው በአሜሪካ በኩል አስቀድሞ አቋም ተይዞበታል፡፡
 

ከሳምንታት በፊት የወጣው የዋይታውስ መግለጫ ‹በግድቡ አስተዳደር ላይ ተስማሙ› (ከላይ ገልጬዋለሁ) በማለት ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቷ ውስጥ የሚሠራን ግድብ ግብፃዊያን መጥተው እንዲያስተዳድሩ (Operation) ትፈቅድ ዘንድ አዟል/ጠይቋል፡፡ይህ በኢትዮጵያ ባለሙያች በኩል ውድቅ ቢደረግም፣

ከሕዳሴ ግድብ ጅማሮ ማግስት የኢትዮጵያን አቋም ደግፋ የፀናችው ሱዳን፣በእያንዳንዱ ውሳኔና እንቅስቃሴ ላይ የጋራ የአቋም ስትይዝ ከርማለች፡፡ (ሱዳን በየጊዜው እንደምትቀያየር በመጀመሪያው ትችቴ ውስጥ ጠቅሻለሁ) የሶስተኛ ወገን አደራዳሪን አላስፈላጊነትም ውድቅ ያደረገችው ከኢትዮጵያ ጋር ሆና ነው፡፡ (አድርጋ አታውቅም)

አሁን ግን የኢትዮጵያ ጠቅላይሚኒስትር ሱዳንን ትተው ምዕራባዊያን ያቀረቡላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ተመልሰዋል፡፡ ይህ በቀጥታ ሱዳንን ቅር የሚያሰኝ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃን ችግር በአፍሪቃዊያን እንፈታለን ከሚለው የአፍሪቃ ሕብረት አጀንዳም ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው፡፡ ጠቅላይሚኒስትሩ ‹ፖለቲካዊ ውይይቱን ከማንም ጋር ብናደርገው ችግር የለውም› ያሉት ነገር ትልቅ ስህተት የሚሆነውም ለዚህ ነው፡፡

በአንድ በኩል ግብጽ በወንዙ ላይ ከዚህ በኋላ ሌላ ምንም ዓይነት የልማት ሥራ እንዳይሠራ የሚያደርግ ፕሮፖዛል ይዛ ልትቀርብ ትችላለች፤ እስካሁን ያላነሳቻቸውን አጀንዳዎችም ልትመዝ ትችላለች፡፡ (አቤት ጉድ! በ2015 ላይ ከመብራት ሌላ ምንም አልሰራበት ብሎ በድንቁ ሰነድ ያሰፈረውን ረስቶት ነው። ከዚህ ውጪ ዐቢይን ምን አይነት የልማት ስራ እንዳትሰራ ልትከለክለው ይሆን? እንዳትዋኙበት እንዳትለን ይሆን )

ለዚህ ደግሞ ባንኩና አሜሪካ ያግዟት ዘንድ ለዓመታት ስትሰራ ቆይታለች፡፡እናም ይህ ድርድር በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምኑችን ቢሮ በመጪው ረቡዕ ይካሄዳል፡፡ የማይመጣጠኑ ኃይሎች የሚያደርጉት ድርድር መሆኑ ውጤቱን ከወዲሁ ተገማች ያደርገዋል፡፡

ከሶች በፊት፣በፓርላማው ፊት

ጠቅላይሚኒስትሩ ወደ ሩሲያ ተጉዘው ኤል ሲሲን ከማግኘታቸው በፊት፣በፓርላማ ቆይታ ነበራቸው፡፡ስለ ግድቡ ተጠይቀው የመለሱት መልስ፣በዲፕሎማሲያዊ ስህተቶች የተሞላ ነበር፡፡‹‹ያው ኢትዮጵያውያን በውስጥም በውጭም በታላቅ ትህትና እንድትገነዘቡ የምጠይቀው፣ 1/4ኘኛው የአገሪቱ ሕዝብ ድሃ ነው፡፡እና ወጣት ነው፡፡ስለዚህ ከአፍሪቃ ጋር እንዋጋ ከተባለ ብዙ ሚሊዮን ማሰለፍ ይቻላል ማለት ነው፡፡አንዳንዱ ሚሳኤል መተኮስ የሚችል ከሆነ አንዳንዱ ደግሞ ቦንብ ታጥቆ፣ለኢትዮጵያ (ለባንዲራ) ከሆነ፣…ካይሮ ላይ ያፈነዳል ማለት ነው፡፡ግን በማፈንዳት በጦርነት ጥቅም አይገኝም››፡፡

እንዲህ ያለውን ነገር በ21ኛው ክፍለዘመን የአገር መሪ ሲናገረው ያስደነግጣል፡፡


 

በአንድ በኩል 1/4ኛው ድሃ ስለሆነ ይዋጋል ማለት ‹ኮሎኔልነት› ማዕረግ ላይ ከደረሰ መሪ የማይጠበቅና ውትድርና የድሃ ሥራ አድርጎ ማየቱ ትልቅ ችግር ነው፡፡ (ሃሃሃ! ማቀሳሰር ይልሃል እንዲህ ነው! ያየሰው እንዲህ አይነቱን ተራ ማቃጠር ትተህ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስህተት በግልጽ ነግረህ ብታልፍ ደስ ይለኝ ነበር። እኔ ልንገርልህ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ነግግር አላስፈላጊ ነበር!!!!)

ሁለተኛው ግን ‹ካይሮ ላይ ቦንብ እናፈነዳለን› ማለት ፍፁም ኢ-ዲፕሎማሲያዊና አቅምን አለማወቅ ነው፡፡ጉዳዩ ወዲያው ነበር ያንጫጫው፡፡አሶሽዬትድ ፕሬሰ ‹የኖቤል ተሸላሚው ጠቅላይሚኒስትር ግብጽን አስጠነቀቁ› ብሎ ዘገበው፡፡አልጄዚራ ‹የሠላም ሎሬቱ ከግብጽ ጋር እስከ ጦርነት ከደረሱ ሚሊዮኖችን አዘምታለሁ አሉ›› አለ፡፡ የካይሮ መገናኛ ብዙሃን ይህንን የዘገቡት በሰበር ዜናነት ነው፡፡ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚያኑ ዕለት ማታ ባወጣው መግለጫ ‹ደንግጫለሁ› አለ፡፡

‹“የግብጽ አረባዊ ሪፐብሊክ የጠቅላይሚኒስትር ዐቢይን የፓርላማ ንግግር ስትሰማ ደንግጣለች፤ጠቅላይሚኒስትሩ ያሰሙት ንገግር ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን በሕዳሴ ግድብ አጀንዳዎች ላይ አሉታዊ ግብዓት የሚሆን ነው››ነበር ያለው-የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡በርግጥም ይህ በድርድሩ ላይ የበዛ አሉታዊ ሚና አለው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ‹ግን ጦርነት አይጠቅምም› ያሉት ነገር አያዎ ነው፡፡ የጦርነት አላስፈላጊነት ገና ድሮ የታመነበትና ተትትኖ የሚታወቅ ነው፡፡ወሳኙ ነጥብ ግጭት ቀስቃሽ ንግግርን መተው ነው፡፡ለዚያም ነው፣ግብጽና መገናኛብዙሃኖቿ ስለ ማፈንዳትና መዋጋት ብቻ የተናገሯትን ያራገቧት፡፡


 

ያየሰውን ስናጠቃልለው

በሁለቱ ጽሁፎቹ ውስጥ፤ መአት ትዝብቶችን መውሰድ ይቻላል። ውሸት፤ ማስመሰል፤ ስም ማጥፋት፤ ማለባበስ፤ የራስን ስህተት መሸፈን፤ ማወናበድ፤ የእውቅትና የመረጃ እጥረት፤ ጭፍን ጥላቻ ወዘተ ……….በዚህ ሁኔታ ነው ያየሰው በርካታ ጽሁፎችን ያስነበበን። ሌሎቹንም አይቶ መፍረድ ይቻላል። ተመሳሳይ ናቸው።  በተለይም ዛሬ ላይ ሆኖ ለሚያየው ሰው ከትዝብት በላይ ለሆነ ምላሽ ይዳረጋል። የእነ ህወሓትን መሰል እንቅስቃሴ ስንመለከትም እርስ በርሱ እየተናበበ ተራ ጥላቻውን የሚዘራ የሚዲያ ማፍያ እንዳለ እንረዳለን። ብዙ አሉ! ግድቡን ለተመሳሳይ አላማቸው የሚጠቀሙበት። በርካታ የፕሮጀክቱን ሰራተኞች፤ የተደራዳሪዎቻችንን ሞራልና ሰብእና የሚነኩዐ የለውጡን መንፈስ ለመጎዳት የታቀዱ  አደገኛ የፕሮፓጋንዳ ስራዎች ተሰርተዋል፤ እየተሰሩም ነው።

ከሁሉም በላይ አስገራሚው ግን ይሄንን አይነት ስህተት ሲፈጸም ምላሽ የሚሰጥ አካል መጥፋቱ ነው። አንድ ሁለት ጊዜ በመጽሄቱ ላይ ምላሽ ለመስጠት አንደተሞከረ አይቻለሁ። እነሱን አመሰግናለሁ። ጉዳዩ ግን ከዚህም የባሰ ምላሽ እንደሚያስፈልገው መማሪያው ጊዜ አሁን ነው።

ይሄንን ውድ እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክት ከሚሰነዘርበት የሚዲያ ጥቃት የሚከላከል ቡድን ማደራጀት፤ በፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ስር ማዋቀር ይቻላል። ለብቻው እንደ ቲንክ ታነክም ሊደራጅ ይችላል። ጉዳዩ ይሄንን መስራት ይሆናል። ወደራሱ የሚዲያ ፕሮጀክቶች የሚያድግበትም መንገድ ይመቻቻል። ብቻ፤  ከተለመደው የህዝብ ግንኙነት ስራ ከሚሰራው አካል የተለየ መሆን ይኖርበታል። ለእያንዳንዱዋ ሚዲያ ላይ ለምትወጣ ስህተት ማጣሪያ የሚሰጥ አካል ይሆናል። በመረጃ የበለጸገ፤ ፎርማል አካል መሆን አለበት። ተመጣጣኝ የሚዲያ ምላሽ መስጠት ህጋዊ እርማት ለሚያስፈልጋቸውም አቻውን መስጠት።

ይህ ፀሀፊ የህወሓት ዋነኛዉ የፕሮፖጋንዳ ማሽን በመሆኑ፣ በዚህ መልኩ የያየሰውን ጽሁፎች በተከታታይ እትማችን እንሄድባቸዋለን። በዛዉም የአለቆቹን ዓላማና ማንነት እንዲሁም አቅም ያሳይልናል ብለን እናምናለን፡፡
ትዝብታችንን ከታዘባችሁትም ጻፉልን፤ አንደወረደ ይነበባል