የመጪዎቹ ዐሥር ዓመታት የልማት ዕቅድ ማብራሪያ ቀረበ

የመጪዎቹ ዐሥር ዓመታት የልማት ዕቅድ ማብራሪያ ቀረበ

ኢትዮጵያ፡- አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት የሚል ርዕስ ያለው የመጪዎቹ ዐሥር ዓመታት የልማት ዕቅድ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡

ኢትዮጵያ፡- አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት የሚል ርዕስ ያለው የመጪዎቹ ዐሥር ዓመታት የልማት ዕቅድ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ የዕቅዱ ዓላማዎች ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት፣ ምርታማነት እና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት፣ የሥርዓታት ለውጥ ማምጣት፣ የሴቶች እና የወጣቶችን ፍትሐዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ መሪነት ማረጋገጥ ናቸው፡፡

ሌሎች ዘርፎች ውጤታማ ዕድገት እንዲኖራቸው መሠረት የሚሆኑ አምስት ምሦሦዎችም ያሉት ይህ ዕቅድ፣ ያሉንን ጥንካሬዎች እና ዕምቅ ሀብቶች ጥቅም ላይ ለማዋል የታለመ ነው፡፡ በተለይም የኢነርጂ ዘርፍን የሚመለከተው ዕቅድ፣ ለአብዛኛዎቹ የልማት ፍላጎቶች እንዲሁም ለሁሉም ዘርፎች ኢነርጂ አስፈላጊ መሆኑን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡

የዐሥር ዓመት ዕቅዱ በውጤታማነት እንዲፈጸም 

  • 1. የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች እና ኢንቨስትመንቶች በሙሉ የነፍስ ወከፍ ገቢን ለማሳደግ አስተዋጽዖ እንዲኖራቸው ማስቻል፣
  • 2. ፕሮጀክቶች ጥራት እንዲኖራቸው በሚያስችል መልኩ ማንኛውም ወጪ በአግባቡ በጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፣ እና
  • 3. ‘ድህነትን ከመዋጋት’ ትርክት ወጥቶ ባለ ብዙ ገጽ ብልጽግናን ወደ መገንባት መሸጋገር፡፡

የሚሉትን ዐበይት ተግባራት የፌደራል መንግሥት እና የክልል መንግሥታት መከወን ያስፈልጋቸዋል ተብሏ