በኢትዮጵያ 137 አዲስ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ተገኙ

በኢትዮጵያ 137 አዲስ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ተገኙ

በኢትዮጵያ ትናንት በተደረገው የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሃገሪቱ መዝግባው የማታውቀው መቶ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በኢትዮጵያ ትናንት በተደረገው የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሃገሪቱ መዝግባው የማታውቀው መቶ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 
ከነዚህም መካከል 94ቱ የተገኙት የቫይረሱ መዛመት እየጎላባት ባለችው አዲስ አበባ መሆኑንም የጤና ሚንስቴር እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሚሰጡት ዕለታዊ መግለጫ ተጠቁሟል።
በሃገሪቱ ውስጥ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ስርጭት እየጨመረ መሆኑ ከሰሞኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 62ቱ የውጪ ሃገር ጉዞም ሆነ ከህሙማን ጋር የታወቀ ንክኪ አለመኖሩ ለዚህ አመላካች ነው ነው ተብሏል።
በዛሬው ዕለትም በተጓዳኝ ህክምና ላይ የነበሩት የ70 አመት ሴትዮ መሞታቸውን ተከትሎ፣ ሃገሪቷ ሰባተኛ ዜጋዋን በኮሮናቫይረስ አጥታለች። በአጠቃላይ በሃገሪቱ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 831 የደረሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል 191 አገግመዋል።