የልጅ ልጆቻቸውን ፎቶ ፌስቡክ ላይ የለጠፉት አያት በአውሮፓ ሕብረት ሕግ ተከሰሱ

የልጅ ልጆቻቸውን ፎቶ ፌስቡክ ላይ የለጠፉት አያት በአውሮፓ ሕብረት ሕግ ተከሰሱ

የልጅ ልጆቸቻቸውን ፎቶ ያለ ፈቃድ ፌስቡክ ላይ ለጥፈዋል የተባሉት አያት በአውሮፓ ሕብረት ሕግ ተከሰው ፎቶዎቹን እንዲያወርዱ ታዘዋል።

የልጅ ልጆቸቻቸውን ፎቶ ያለ ፈቃድ ፌስቡክ ላይ ለጥፈዋል የተባሉት አያት በአውሮፓ ሕብረት ሕግ ተከሰው ፎቶዎቹን እንዲያወርዱ ታዘዋል። አያት፤ የልጅ ልጆቻቸውን ፎቶ ፌስቡና ፒንተረስት የተሰኙት የማኅበራዊ ድር-አምባዎች ላይ ያለፈቃድ ለጥፈዋል የሚል ክስ የተመሠረተባቸው ከልጃቸው ነው።

ብይኑን የሰጠው አንድ የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት ዳኛ አያት የአውሮፓ ሕብረትን ሕግ ጥሰዋል ሲሉ ኮንነዋቸዋል። አያት የልጅ ልጆቼን ፎቶ ከፌስቡክ ላይ አላጠፋም ማለታቸውን ተከትሎ ነው በልጃቸው ክስ የቀረበባቸው። የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤት አያት የጠቅላላ መረጃዎች ጥበቃ የሚለውን የአውሮፓ ሕብረት ሕግ አልተከተሉም ሲል ፈርዷል።

የልጆቹ እናት የሆነችው ከሳሽ "ብዙ ጊዜ የልጆቼን ፎቶ አውርጂ ስል ጠይቅያለሁ" ስትል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታዋን አሰምታለች። ምንም እንኳ የአውሮፓ ሕብረት ሕግ ለግለሰቦች የሚያገለግል ባይሆንም፤ "አያት የልጆቹን ፎቶና መረጃ ለብዙሃን አጋልጠዋል" ብለዋል ዳኛው።

"ፌስቡክ ላይ የሚለጠፉ ፎቶዎች ለሦስተኛ ወገን ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። ፎቶዎቹ ለብዙሃኑ ስለሚጋለጡ ያለአግባብ ሊሰራጩ ይችላሉ" ብሏል የፍርድ ቤቱ ብይን። አያት ፎቶዎቹን አላወርድም የሚሉ ከሆነ በየቀኑ 50 ዩሮ [1800 ገደማ ብር እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። የቅጣቱ ከፍታ 1 ሺህ ዩሮ ነውም ተብሏል።

አያት ፍርድ አያግደኝም ብለው ሌሎች ፎቶዎች የሚለጥፉ ከሆነ ተጨማሪ 50 ዩሮ በየቀኑ ይቀጣሉ። "ፍርዱ ብዙዎችን ሊያስገርም ይችላል፤ በርካቶች ፎቶ ወይም ፅሑፍ ሳያስተውሉ ሊለጥፉ ይችላሉና" ይላሉ የቴክኖሎጂ ጠበቃው ኒል ብራውን።