ትምህርት ቢሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በቴሌግራም መልቀቁን አስታወቀ

ትምህርት ቢሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በቴሌግራም መልቀቁን አስታወቀ

ትምህርት ቢሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በቴሌግራም መልቀቁን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ2012 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተናዎችን ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ በቴሌግራም ቻናል መልቀቁን አስታወቀ፡፡

ለ8ኛ በሁለት ቋንቋዎችና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተለቀቀው ፈተና  ከግንቦት 11 እስከ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ቢሮው ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደሚከናወን የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት በቢሮው የቴሌግራም ቻናል ላይ ለየክፍል ደረጃዎቹ የሚቀርበው የሞዴል ፈተናው ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲፈትሹ የተዘጋጀ ነው፡

ፈተናውም በሚሰጥበት ጊዜ ወላጆች ልጆቻቸው ላይ ክትትል በማድረግ የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ ትምህርት ከመጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ መዘጋቱ ይታወሳል፡፡