የዐባይ አዘጋገብ… በነመሀመድ በኩል እኛን

የዐባይ አዘጋገብ… በነመሀመድ በኩል እኛን

የዐባይ አዘጋገብ… በነመሀመድ በኩል እኛን

"ኢትዮጵያዊ ሆኖ በህዳሴ ግድብ የተለየ አቋም ያለው ካለ ከሀገር ክህደት ይቆጠራል።"

 

ሕዳር 21 ቀን 1949 ዓ.ም ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ የተናገሩት ንግግር።

"ሐገሬ ኢትዬጵያ በዓለም ሸንጎ ላይ ፍርድ ተነፍጓት ስታዝን የመጀመሪያዋ አይደለም ። ኢትዬጵያ እና ያለፉት ታሪኮቾ በአግባቡ እንዳስረዱት ለነፃነቷ ለመብቷ፤ ከኮሎኒያሊስት ጣልያን ጋር በየጊዜው ስትዋጋ ያሸነፈችው ብቻዋን ነው። የተጠቃችውም ብቻዋን ስለሆነ፤ አገሬ መቸውንም ለሚደርስባት አደጋ ከማንም እርዳታ አገኛለሁ ብላ አትጠብቅም። ዛሬም ሆነ ነገ ነፃነቷን ለመጠበቅ፤ ታሪኳን ለማስከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ያለባት እሷ እራሷ ብቻ ናት። "

በአባይ ጉዳይ ላይ የሀገራችን አንዳንድ ዘጋቢዎችና አክቲቪስቶችን ለገመገመ ሰው፣ የነመሀመድ አልአሩሲና መሰሎቹ ተግባር፣ እነሱ ከተናገሩትም ሆነ እና ከምንናገረዉም በላይ ነዉ፡፡
መሀመድም ሆነ አሜሪካዊው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጄሲ ጃክሰን፣ በቋንቋ ከአብዛኞቹ ኢትዮጵያዉያን ጋር አይግባቡም፡፡ በሚችሉት ቋንቋ ግን ምን ማዉራት እንዳለባቸዉ ያዉቃሉ፡፡ የሚያወሩት ያልገባዉም በፍቅር ወድቆላቸዋል፡፡

ለምን? በቅድሚያ የሚያንገበግበዉ አባይ ነዉ! የሀገር ክብር ነዉ፡፡

Image

የአባይ አጀንዳ ሲጀመር ባዳዎቹ እንኳን ሙግታችንን ያቀርባሉ፡፡ የግብፅን ኢፍትሐዊ አካሄድና ጥያቄ ከመፈተሽ ይነሳሉ፡፡

"…. በአባይ ወንዝ ላይ የሚካሄድን ፕሮጀክት መቃወም ኢ-ፍትሀዊ ስለሆነ ያንን ለዓለም ህዝብ ማስረዳትና ድብቁን አጀንዳ ማጋለጥ የሁሉም ሃላፊነት ነው" መሀመድ አልአሩሲ።

የኛዎቹስ? ከዐብይ ይነሳሉ፡፡ ግብጽ አንድ ስትሆን እኛ ደግሞ ለሷ መወገን በሚባል ደረጃ፣ መሪውን እንደማጥቂያ መጠቀምን መርጠናል፡፡ በአባይ ወደ ዐብይ ተጉዞ ፖለቲካዊ ትርፍ ማስላት፡፡

 

የግብፅ ሚዲያዎችና ባለሙያዎቻቸው የሚያንፀባርቋቸውን አቋሞች በደንብ ለሚከታተል ... ግብፅ ግትር ሀገር መሆኗን ይረዳል።

አረብ ሊግ በተባለውና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ በታች በወረደ እድር በኩል ተፅዕኖ ለማሳደር የተሄደው ርቀት፣ በአሜሪካን በኩል ለማሳደር ታስቦ የከሸፈው ጫና የመፍጠር ሙከራ፣ ... ግብፅ ምን ያህል ከጉዳዩ ሩሩሩሩቅ መሆኗን ያየንባቸው አጋጣሚዎች ናቸው።

ግብፅ ግትርና ያረጀ አቋሟን ይዛ አረጀች ሲሉ የሚገልጧት አሉ። የሀገራችን የዘርፉ ባለሙያዎችም የግብፅ የሚዲያ ዘመቻና ፕሮፖጋንዳ አደገኝነት ደጋግመዉ ያነሳሉ፡፡

በአ. አ .ዩ. የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ "የግብፅ መረጃዎች አብዛኛዎቹ የተደራሲውን አስተሳሰብ ለማዛባት የታለሙ ናቸው" ይላሉ፡፡

አቶ ገዱም ይህንኑ ጉዳይ አስረግጠዉ ይናገሩታል፡፡ አንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች ግድቡ በግብጻውያን ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማያሳድር እያወቁ በኢትዮጵያውያን ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ ዘመቻ ማካሄድ እና የግብፅን ህዝብ ለማሳሳት መምረጣቸውን ያነሳሉ፡፡ ይህ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን ጭካኔ የተሞላበት አካሄድ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዚህ አካሄድ ላይ የኛው ዜጋ አሉታዊ አካሄድ ከታከለበት፣ የራሳችንን ወገኖችከግብጽ በምን_እንለያቸው?

ቀጠናዊ ፖለቲካው እንዲህ በከረረበት:: የኮሮና ወረርሽኝ ሀገር ጠፍሮ በያዘበት ... በዚህ አስቸጋሪ ወቅት፣ መንግስትን ውጥረት ውስጥ ለመክተት፣ ከየአቅጣጫው የማይፈነቀል ድንጋይ የለም:: ግብጽስ ብትሆን ከዚህ በላይ ምን አደረገችን?

በእርግጥ በዚህ ረገድ ሰሞኑ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተደረገዉ ዉይይትና ስለታላቁ ህዳሴ ግድብ የተደረገዉ ገለፃ ጥሩ ጅምር ነበር:: በዚሁ መድረክ ላይ ታድሞ የቁርጥ ቀን ደራሽነቱን ያሳየው መሀመድ አል አሩሲ ያደረጋት አጭር ንግግር፣ ከመገናኛ ብዙሀኑና ከፖለቲከኞች በዚህ ረገድ የሚጠበቀውን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር፡፡

"እኔ እስካሁን ከ 20 በላይ የዓረበኛ የቴሌቪዢን ጣቢያዎች ቀርቤ ከ 100 በላይ ቃለ መጠየቆችና ክርክሮችን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ተሟግቻለሁ፡፡ በተለይም ተቀማጭነቱ ቱርክ ከሆነው #Asherq ከተባለ ከግብፅ ተቃዋሚ ቴሌቪዢን ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጌ የተገነዘብኩት ነገር ቢኖር፣ ሁሉም የግብፅ ተቃዋሚዎች መንግስትታቸውን  ቢቃወሙም በብሔራዊ ጥቅማቸው፣ ማለትም እንደ አባይ ግድብ ባሉት ላይ አቋማቸው  አንድ ነው:: ስለዚህ እናንተ ተፎካካሪ ፖርቲዎች ወይ በመሀከላችውና ከመንግስት ጋር የፖለቲካ ልዩነት ቢኖርም በህዳሴ ግድብና በሀገራዊ ብሔራዊ ጥቅም ላይ አንድ እንድትሆኑ እመክራለው" ብሏል፡፡

ይህ ግድብ ጣጣ የበዛበትና በጣም ስሱ የሆነ የፖለቲካ ጉዳያችን ነው። የብዙ አካላት ፍላጎት ያለበት፡፡ ትልቅ ብልጠትና እውቀት የሚጠይቅ፡፡ አለፍ ሲልም የህልውና ጉዳይና ብሔራዊ ጥቅሙ ለድርድር የማይቀርብ ነው።

እና በኛ ሀገር አዘጋገብ ውስጥ ያለው ሁኔታ አስደንጋጭም አሳፋሪም ሊባል የሚችል ነው። ማንም ብድግ ብሎ የመሰለውን ያወራል። ህይወት ገብረው የሚሰሩ ባለሙያዎች ይዘለፋሉ! ይንጓጠጣሉ! ይናቃሉ! ሀገር ሻጭ ይባላሉ፡፡ አለፍ ሲል ሌሎች ሀገራትም ይሰደባሉ። ምናልባትም ከአባይ ጋር በተያያዘ የአዘጋገቡ ጉዳይ ከህግ አንፃር የሆነ መፍትሄም የሚፈልግ ይመስላል። በጣም አስደንጋጭና ለመስማት የሚከብዱ ዘገባዎችና ሀሜቶች ናቸው በሀገራችን ውስጥ የሚሰሙት። አንዳንዴ ድንቅ ስራዎችን የሚሰሩ ባይጠፉም።

እንደ መሀመድ ያሉትን ሀገራዊ ቁጭትና አቋም በመዋስ፣ "በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሁላችንም በአንድ ልብና በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት ይጠበቅብናል::" ለማለት እንወዳለን፡፡