ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የምትገነባው ግድብ የመገንባት ሙሉ መብት ስላላት ነዉ!!

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የምትገነባው  ግድብ የመገንባት ሙሉ መብት ስላላት ነዉ!!

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የምትገነባው ግድብ የመገንባት ሙሉ መብት ስላላት ነዉ!!

"ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅማ ዜጎቿን ከድህነት የማላቀቅ ሙሉ መብት አላት። ሆኖም አባይን የመሰለ የተፈጥሮ ሀብቷን ስታለማ በዚህ ወንዝ ላይ ህይወታቸውን የመሰረቱ የታችኛዎቹ የተፋሰሱ ሀገራት በመኖራቸው የምትገነባው ግድብ በእነዚህ ሀገራት ላይ ጉልህ ተፅእኖ እንዳያሳድር በማድረግም ነው።
ለሁሉም መፍትሄ የሚሆነው መደራደር እና በመጨረሻም ስምምነት ላይ መድረስ ብቻ መሆኑን ግብፅ ተገንዝባ የምታሰማው ዛቻ ጥቅም የለሽ፣ ለማንም የማይጠቅም እና ግንኙነትን ከማሻከር ያለፈ ፋይዳ የለውም።"
ለኢትዮጵያ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለታላቁ ህዳሴ ግድብ ገለጻ ተደርጓል፡፡ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ ለኢትዮጵያ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም በግብጽ፣ ሰዳንና ኢትዮጵያ እየተካሄዱ ስላሉ ውይይቶች በተመለከተ ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ገለጻ ተሰጥቷል።
"የኢትዮጵያ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች ሚና ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግደብ ግንባታ ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ተሳትፎ" በሚል መሪ ቃልም ነበር መድረኩ የተዘጋጀው።
አቶ ገዱ ግድቡ በሁሉም ኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦ የተገነባ ፕሮጀክት መሆኑንና ግድቡ ከምርጫም ሆነ ከስልጣን በላይ መሆኑን አስረድተዋል:: አክለውም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባቸውም አንስተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት በሀገሪቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በሀገር ሉዓላዊነት እና አንድነት ጉዳይ እንደማይደራደሩ፣ በተለያዩ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ቢኖርም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ግን ምንም አይነት ልዩነት ሳይኖር በጋራ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናረዋል፡፡ ፖለቲካ ሊኖር የሚችለው የሀገር ሉአላዊነት እና ጥቅም ሲከበር መሆኑን ያነሱት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎቹ የትኛውም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲ በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የተለሳለሰ አቋም ሊያራምድ አይገባምም ብለዋል።