በካይሮ ዋና ከተማ አዲስ አበባ

በካይሮ ዋና ከተማ አዲስ አበባ

የእኛ ነገር እንዳይሆን የሆነው ከግብጽ ጋር የምንካፈለው ወንዝ የኖረን ዕለት ነው። ‘ተፈጥሮ ተሳስታ አታውቅም’ የሚሉትን ሁሉ...

“በካይሮ ዋና ከተማ አዲስ አበባ”

የእኛ ነገር እንዳይሆን የሆነው ከግብጽ ጋር የምንካፈለው ወንዝ የኖረን ዕለት ነው። ‘ተፈጥሮ ተሳስታ አታውቅም’ የሚሉትን ሁሉ ለጥያቄ አስኪዳርግ ድረስ የሁለታችን ጉዳይ ለምንም የማይመች አይነት ከሆነ ዘመናት ተቆጠሩ። ከግብጽ ጋር ተገናኝተንም ተለያይተንም አናውቅም። ግንኙነታችን፤ “ቸቁሰገቂየሰፈወሉወደየወደዎጀ” ሊባል ይችላል። ትርጉመ ቢስ ነው። ግብጽ የምትፈልገውን ከማትፈልገው መለየት ያቃታት ሀገር ናት (በዚህ ምድብ እኛ ብቻ ብንበልጣት ነው) ። ግብጽ በናይል ላይ ያላትን ፖሊሲ “ከመጠን ባለፈ ፍቅር ሊተዳደር የሚገባውን ሀብት ከመጠን ባለፈ መጠራጠርና ጥላቻ ለማስተዳደር መሞከር” የሚለው አባባል የተሻለ ይገልጸዋል አባባል የተሻለ ይገልጸዋል።

ወንዝን የሚያህል ሀብት (ሊያውም ናይልን) “ግብጽ የናይል ስጦታ ናት” በሚለው የሄሮደተስ አባባል ለማዘዝ የሚሞክር ታጋይ ከገጠመን ሚሊዮን አመታት አለፈን። የታሪክ አባት እየተባለ የሚሞካሸው ሄሮደተስ ለግብጾች የዘለአለም ጥቅስ የሰጣቸውን ያህል፤ ለእኛም የሚሆን ጥቅስ አያጣም፤ እነዚህ አባባሎችም የእሱ ናቸው፤

‘In peace, sons bury their fathers. In war, fathers bury their sons’ (በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ፤ የጦርነት ነጋሪት ለሚጎስሙት ሁሉ። እንደወጉ ለሰላም እንትጋና ልጆቻችን ይቅበሩን፤ አለዚያ ልጆቻችንን እንቀብራለን)

Force has no place where there is need of skill. (ጥበብ በሚጠይቀው ቦታ ልጥበብ ለሚሉት፤ ብልሃት የሚሻውን በር በጉልበት ለመክፈት ለሚታገሉት ሁሉ)

Very few things happen at the right time, and the rest do not happen at all. The conscientious historian will correct these defects. (በገማል አብዱል ናስር መፈክር ሰልፍ ለመጥራት ለሚደክሙ ሁሉ። በትክክለኛው ሰአት የሚፈጠሩት በጣም ጥቂት ነገሮች ናቸው፤ ቀሪው በሙሉ ያለጊዜው የሚመጣ ወይም ከነጭራሹ የማይፈጠር ነው። ጠንቃቃ የታሪክ ሰዎች ብቻ እነዚህን ችግሮች እያስተካከሉ ይጠቀሙባቸዋል)

Of all men's miseries the bitterest is this: to know so much and to have control over nothing. (ግድቡን ያለእኔ ፈቃድ ማንም አይሰራውም ለሚሉትና፤ ሊያልቅ አንድ ሀሙስ ለቀረው ግድብ)

Now stop your dancing; you wouldn't come out and dance when I played to you. (ጨዋታው ከተጀመረ ቆየ፤ አንቺ አሁንም ዳንስሽ ላይ ነሽ)

As the old saw says well: every end does not appear together with its beginning (በ1959 ውል 2020ን ለማዘዝ ለሚመኙ ሁሉ)

ከግብጽ ጋር የሚያውለን ገበያ በኪሳራ ያበደ ነው። ግብጽ ማንም የማይመኛት አይነት አጋር ናት። ግብጽን አምኖ መቀመጥ አንገትን ቆርጦ ለማሰብ እንደሞመከር ያለ ቅብጠት ነው። ከግብጽ ጋር መስማማትም መጠላትም እኩል አደጋ ያለው ሀቅ ነው። ስለዚህ ‘እደራደራለሁ’ ስትልም፤ ‘አልደራደርም’ ስትልም በእኩል ጆሮ መስማት ነው። ‘በሰላም እንፍታው’ ስትልም፤ ‘ጦር እሰብቃለሁ’ ስትልም በእኩል ፈገግታ መቀበል ነው። ሳይዘናጉ ስራን መቀጠል ነው። እየተደራደሩም፤ እየተገዳደሩም መቀጠል ብቻ!!

ይህ ጽሁፍ፤ የግብጽን ዋና ከተሞች በኢትዮጵያ ያስተዋውቀናል። የካይሮን የመጫዎቻ ሜዳዎች ይጠቁማል። ከእነአጨዋወቷ፤ የዳኞቹንና የተመልካቾቹን ጠባይ ወዘተ በስሱ ለመጠቆም ይሞክራል። የእኛም የአጨዋወት ታክቲኮች ምን መምሰል እንደሚገባቸው የመመካከር ሀሳብም አለው። 

“አባይ ወንዛ ወንዙ ብዙ ነው መዘዙ”

ጥበበኛዋ እጅጋየሁ ሽባባው፤ ‘ብነካው ተነኩ አንቀጠቀጣቸው’ ትላለች። ትልቁን ችግር በአንዲት መስመር ገልጻዋለች። መንቀጥቀጣቸው ስህተት፤ መነካቱ ግን ልክ ነው። ፖለቲካው ሁሉ ያለው እዚህ ውስጥ ነው። ወንዙን እንድንነካው አይፈልጉም፤ ስንነካው ይንቀጠቀጣሉ። መንቀጠቀጣቸው ብዙ ነገር እንዲያንቀጠቅጥ ይፈልጋሉ። እስከ ቅርብ ጊዜም ፍላጎታቸው ሰምሮ ቆይቶአል። የህዳሴ ግድቡ እውን መሆን ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ የመንቀጥቀጣቸው ነገር ዜማ ቢቀይርም ግቡን ግን አይተውም።

እንዲንቀጠቀጡ ከሚፈለጉ ቦታዎች ዋናዎቹ ፤ ከእጇ ውጪ ያሉት የወንዙ ምንጮች ናቸው። ከምንጮቹ ዋናው ደግሞ እኛ ዘንድ ይገኛል። የግብጽን የውሃ ኮታ እስከ 86 ከመቶ የሚያቀርቡት ምንጮች መገኛቸው ኢትዮጵያ ነው። በሶስት ቀጠና ይከፈላሉ። ‘ንዑስ ተፋሰሶች’ (ሰብ ቤዚንስ) ይሏቸዋል። (የእኛን ብቻ ነጥለን ነው የወሰድነው) የአባይ (የሱዳንን ሲያካተት ብሉ ናይል) ተፋሰስ፤ የባሮ አኮቦ ሶባት ተፋሰስ እና የተከዜ አጥባራ ተፋሰስ ይባላሉ።   የኋይት ናይል (ነጩ ናይል) ተፋሰስ ውስጥም አለንበት።

በጂኦፖለቲክስም ሆነ በሀይድሮፖለቲክስ ትንተናው ሁሉንም ሰብ ቤዚኖች በራዳራችን ስር አድርገን መከታተሉ ይመከራል። በቀጥታ ከግብጽ ጋር የሚያፋልሙን ግን አራቱ ተፋሰሶች ናቸው (የብሉ ናይል፣ የተከዜ አትባራ፣ የባሮ አኮበ ሶባት እና የነጩ ናይል) በወፍ በረር እንተዋወቃቸውና ወደ ግብግባቸው እንሄዳለን።

ግብጽ የሚከተሉትን አራት ቀጠናዎች፤ እንደዋና ከተማዋ ታያቸዋለች፤ ውላ ታድርባቸዋለች፤  ናይ)ዚን

ለጠቅላላው ፍሰት 62 ከመቶ ያበረክታል። የሀገራችንን ሶስት ክልሎችና አምስት የሱዳንን ግዛቶችን ያካልላል፤  ከሀገራችን መሬት 20 ከመቶ ይሸፍናል። የ23 ሚሊዮን ዜጎች መኖሪያ ነው። የሀገሪቱን 40% የእርሻ ምርት ይሸፍናል። እስከ 13500ሜዋ ሀይል የማመንጨት አቅም አለው።

አባይ በጉባ በኩል ከወጣ በኋላ ሌሎች ወንዞቻችንን ትንሽ ወረድ ብሎ ይቀላቅላል። ዲንደር፣ ገለግ፤ እና ረሃድ ሱዳን ላይ ይቀላቀሉታል። ከጎንደር ወደ ሱዳን የሚወጡ ናቸው። ካርቱም፤ አል ጀዚራ፣ ቀዳሪፍ፣ ሰናር እና ፣ ብሉ ናይል የተባሉ የሱዳን ግዛቶችን ያጠቃልላል። ብሉ ናይል ይሉታል።

ከተከዜ-አትባራ እና ከባሮ-አኮቦ-ሶባት ጋር ከተገናኘ በኋላ ወደ ዋናው ናይል ይደባለቃል፤ ካርቱም ላይ። በናይል ስም ለካይሮ ይሰጣታል። እሱዋም በአስዋን ግድብ ተቀብላ፤ በናስር ሀይቅ ቀቅላ አፍልታ  እስከ 10ቢሊዮን ኪዩቢክ ሊትር ውሃ ካባከነች በሁዋላ ለምትፈልገው ነገር ታውለዋለች። ለማትፈልገውም ነገር እንዲሁ!

የተከዘ አጥባራ ሰብ ቤዚን

የኢትዮ ኤርትራን ውስብስብ ፖለቲካ በግማሽ ያዘለ ቀጠና ነው። ተከዜ ከላስታ ላሊበላ ቅጨን ከተባለ ተራራ ይነሳል። ኤርትራና ኢትዮጵያን እያዋሰነ ፈስሶ ሱዳን እስኪገባ ድረስ ሰቲት ይሉታል። የመረብና ፤ የጋሽ ባርካ ተፋሰሶችን ከኤርትራ ጨምሮ ሱዳን ይገባል። የጋሽ ባርካ ወንዝ ከማእከላዊ ኤርትራ ይነሳል። ከደቡብ ምእራብ አስመራ 19ኪሜ ርቆ ይነሳና ወደ ደቡብ ሄዶ ኢትዮጵያና ኤርትራን እያዋሰነ ወደ ሱዳን ይገባል። ከሰላ በረሃ ሜዳ ላይ ይጠልቃል። የተከዜ አትባራ ጥላ ውስጥ ይቀላቀላል።

ጊራና፤ በለሳ፤ ሙና፤ ካዛ፤ በለገዝ፤ አረክውሃ፤ መሪ፤ ወረኢ፤ ፍራፍር ወዘተ የተከዜ ዋና ዋና ገባሮች ናቸው። ከ20 በላይ ገባሮቹን በሶስት ንኡስ ሰብ ቤዚኖች ይከፍሏቸዋል። ተከዘ፤ አንገረብና ጉአንግ ይባላሉ። የወልቃይትና የሁመራ የመስኖ ፕሮጀክቶች ትንቅንቅ የሚካሄድበት አካባቢ ነው። 40,000ሄክታር ይሸፍናል ተብሎ የሚገመተውን የወልቃይት፤ እንዲሁም ባለ 43ሺህ ሄክታሩን የሁመራ የመስኖ ፕሮጀክቶች የያዘ ከባድ ቀጠና ነው።የወልቃይት መስኖ የዛሪማ ወንዝ ገባር ከሆነው ዱቆቆ በተሰኘው ወንዝ ላይ ነው። ትግሬ ነው አማራ ነው ሲባባሉ አትስማቸው ይህቺው ናት ጨዋታዋ። ሳትበላ ማንነት የለም። ዋናው የእህሉ ዘር ነው።

የባድመ ፖለቲካም የመስኖና የወንዝ ጉዳይ ላይ በዋናነት ያጠነጠነ ነው። የጋሽ መረብና የሰቲት ተፋሰስ ባድመን ውድ ያደርጋታል። ሲቶና ቶምሳና መአተብ የሚባሉ ወንዞችም አድራሻቸው እዚያው ነው። ሁሉም በተፋሰሱ ጥላ ስር ናቸው። ለስንዴና ማሽላ መመቸቱዋ፤ በጦርነቱ ውስጥ እነ ሳውዲ አረቢያና አይኤምኤፍ የነበራቸውን ሚና ያስታውሰናል።  የደርግ ሰራዊት ያለቀባቸው እነ ተሰነይና እነ አቆርዳት፤ ከሰላ ላይ የሚደረገው የንግድና የሀይማኖት ትንቅንቅ በሙሉ ግባቸው ይሄንን የውሃ ጥላ ለመማረክ ነው። የአሲምባን ጅረቶች ከአሲምባ ፍቅር ላይ፤ የሙናና በለሳን ትርክት ከያሬድ ጀቤሳ አንደበት ይስሙ፤ የበለሳን ትዝታዎች ከቹቹ አለባቸው ድርሳን ይመርምሩ ያኔ ቁልፉን በቀላሉ ያገኙታል። አክሱም፣ ደብረታቦር፣ ጎንደር፣ ሀገረ ሰላም፣ ሃውዜን፣ ኮረም፣ ላሊበላ፣ ማይጨው፣ መቀሌ፣ ነፋስ መውጫ፣ ውቅሮ ወዘተ በእዚህ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ናቸው። “ጎንደር ለህወሓት የህልውና ጉዳይ ናት” ይሉ ነበር አሉ ታጋዮቹ።  ሰብ ቤዚን

በኢዮጵያ ያለው ክፍል ባሮ አኮቦ ይባላል። ብቸኛው ወደ ነጩ ናይል የሚፈሰሰው ወንዛችን ነው። ደቡብ ሱዳን   ሲደርስ ከፒቦር ጋር ይቀላቀልና ሶባት ይባላል። ከዚያም ወደ ነጩ ናይል ይገባል። ባሮ አኮቦ ጂሎ አልዌሮ ጂካዎ ብርብር ገባ የተባሉ ትልልቅ ገባሮች አሉት። ከዩብዶ፤ ከላይኛው ዲዴሳ፤ ከኢሊባቦሯ ሱጴ፤ ከእጉመሮና በኮ የሰበሰባቸውን ይዞ ባሮን ያወፍረዋል። ከታችም እነ ጂሎ አልዌሮ ይመጣሉ፤ ጋምቤላ ላይ ተቀራርበው ይፈስሳሉ። አኮቦ ደግሞ የእነ ዲማን ገባር ሰብስቦ በደቡብ ሱዳን ድንበር ከኡጋንዳና ከደቡብ ሱዳን ተሰባስቦ የሚመጣውን ፒቦርን ተቀላቅሎ በእኛና በጁባ ድንበር ፈስሶ ወደ ማላካል ያቀናል። ሶባት ተብሎ እስከ ማላካል ይዘልቃል። ጋምቤላ የባሮ አኮቦ ሰገነት ናት። መቱ፣ ቤንች ማጂ፣ አቦቦ፣ ኢታንግ የሚያልፍባቸው ታዋቂ ከተሞች ናቸው::

የነጩ ናይል ሰብ ቤዚን

የባሮ አኮቦ ሶባት ተፋሰስ ከሚያበቃባት ማላካል ትንሽ አለፍ ብሎ ባህር አልጀበል ከተባለው ወንዝ ጋር ይጋጠማል። ይህ የሁለቱ ወንዞች መጋጠሚያ የማላክል ትሬአንግል ይባላል። የነጩ ናይል ንዑስ ተፋሰስ መነሻ ነው። ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ይጋሩታል።ከዚያ ወደ እንቅፋቱ ወይም ሱድ ይፈስሳል፤ ወደ ረግረጋማው ሰፊ ቦታ። እዚያ በርካታ ወንዞች ይቀላቀሉታል።

ይህ ሰብ ቤዚን ከኢትዮጵያ ጋር ባለው ዝምድና የሶስቱን አካባቢዎች ያህል ስሙ አይነሳም። ነገር ግን የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ካርታና ገለጻ እንደሚያሳየው ከሆነ ኢትዮያም የዚህ ክልል አካል ናት። አካል ብቻም አይደለም፤ የሱዳንና የደቡብ ሱዳንን የእርስ በእርስ ግጭት ከምታሾረው የብሉናይል ግዛት ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት አለው። ከባሮ አኮቦ ተፋሰስ ከፍ ብሎ ያለውን አካባቢ ያካትታል። የዝናብ መጠን መለኪያ ጣቢያዎቹን በቤንሻንጉል ጉምዝ አሶሳና ኩርሙክ፤ እንዲሁም በምእራብ ወለጋዋ ቤጊ ላይ ተክሏል። የማኦኮሞንና የጊዳሚን ደጃፎችም በጥላዎቹ ይነካቸዋል። ይረግጣል።

የተፋሰሶቹ መጨረሻ

መጨረሻቸው በግብጽና በእኛ እጅ ነው ያለው። የእኛም መጨረሻ በሀብታችን በሌሎች ላይ የጎላ ጉዳት ሳናደርስ መጠቀም ነው። የግብጽ መጨረሻ ኮታዬ የምትለውን ውሃ አለማስነካት ነው። ከተቻለም ሌላ መጨመር ነው። አሁንም ከተቻለ ምንጩን በቀጥታ አሊያም በእጅ አዙር መቆጣጠር ነው። እነዚህን ለማድረግ፤ የታወቁትንና የተሰለቹትን መስመሮች ጨምሮ፤ የማይገመቱ አካሄዶችንም አልፎ አልፎ ከመተግበር ወደሁዋላ አትልም። የተወሰኑትን ‘የግብጽ ሜዳዎች’ በሚለው ክፍል እንመለከታለን።