የግብጽ ሜዳዎች

የግብጽ ሜዳዎች

“የግብጽ ሜዳዎች”

… ግብጽ ትለፋለች። የዋንጫ ጨዋታ ላይ ናት። ለብዙ ሺህ አመታት ግጥሚያ ላይ ነን። የግብጽ እና የእኛ ግጥሚያዎች የሚካሄዱባቸውን ሜዳዎች ከሞላ ጎደል በሚከተሉት ሶስት ምድቦች መከፋፈል እንችላለን።
 
ከላይ የጠቀስናቸውን አካባቢዎች ከመዳፉዋ ለማስገባት፤ አሊያም ለምታምነው አካል ለመስጠት አሊያም በሼር ይዞ ለማስተዳደር ወዘተ…… ግብጽ ትለፋለች። የዋንጫ ጨዋታ ላይ ናት። ለብዙ ሺህ አመታት ግጥሚያ ላይ ነን። የግብጽ እና የእኛ ግጥሚያዎች የሚካሄዱባቸውን ሜዳዎች ከሞላ ጎደል በሚከተሉት ሶስት ምድቦች መከፋፈል እንችላለን። እያንዳንዳቸው ከባህር የሰፉ ጉዳዮች ቢሆኑም በተቻለ መጠን አሳጥረን እንጨዋወታለን።
  1. ተራሮቹን መናድ
  2. “ያለጎረቤትሽ አይነድም እሳትሽ”
  3. ወዳጆቿ ከጠላቶቹዋ
ተራሮቹን መናድ
አራቱም ንዑስ ተፋሰሶች የተራሮቹ ውጤት ናቸው። ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች በሚገኘው ዝናብ ተሞልተው ነው ሶስቱም ተፋሰሶች የግብጽን ማጀት ይሚሞሉት። ”የአፍሪካ ጣሪያዋ“ መባል የማይበዛባት ለዚያ ነው። ጣሪያዎቹ ወሳኝ ናቸው። 
በጥልቅ ጂኦ ፖለቲካዊ ትንታኔዎቹ የሚታወቀው Stratfor የተሰኘው የመረጃ ምንጭ Understanding East Africa's  Politics, One Core at a Time በሚለው ጽሁፉ፤ የውስብስቡንና የሰፊውን የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ የሀይል ማእከል በሶስት ቦታዎች ይመሰርተዋል፡፡ በናይል ወንዝ ተፋሰስ፣ በኢትጵያ ከፍተኛ ቦታዎችና በኬንያ ከፍተኛ ቦታዎች፡፡ 
ሁለቱን በይደር አቆይተን “የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች”ን  እንመልከት፡፡  አስመራና አዲስ አበባን የሚያካትት፣ የታላቁ ናይል ምንጭ፣ ከአፍሪካ ተራሮች 80 ከመቶውን የሚይዝ፣ በጎንደሩ ራስ ዳሸንና በባሌው ቱሉ ዲምቱ ተራሮች ከፍታውን አርቆ የሰቀለ፣ ከአክሱም ገናናነት እስከ ላሊበላ ጥበብ  የተስተናገደበት፣ የትግራይ፣ የአማራና የኦሮሚያ ክልሎችን ያስተሳሰረ፣ የካፋን መስኮች የዘረጋ፣ የአድዋ ድል አሻራ የታተመበት፣ በሰማይ ጠቀስ ተራሮቹ አይበገሬነት የሀገሪቱን ነጻነት አስጠብቆ የዘለቀ፣…… ድንቅ፣ ውብ፣ ሀብታም ግን ደሀ የኢትዮጵያ ክፍል ነው፡፡
 ከኢትዮጵያም አልፎ የምስራቅ አፍሪካን ውሎ አዳር የመወሰን ጉልበት ታድሏል፡፡የናይል ወንዝ ተፋሰስን 85 ከመቶ ውሀ የሚያዋጡትን የናይል ገባሮች በማፍለቅ የሚታወቀው ይህ ቦታ፤ ከግብጽም አልፎ ሶማሊያን የሚያጠጡ ምንጮችን ይዟል። የአውሮፓ ላቦራቶሪዎችን የሞሉ እጽዋቶችን ያበቅላል። 100 ሚሊዮን ለሚደርሰው የግብጽ ህዝብ የህይወት ማእዘን የሆነው ይህ ቦታ፣ ለወላጁ ኢትዮጵያ ግን የልጅ ክፉ ከሆነባት ዘመናት ተቆጠሩ፡፡
”ጠባቂዎቿ“ የተባሉት ከፍተኛ ቦታዎቿ የችግሯ፣ የስጋቷ፣ የጥቃቷ መነሻዎች ሆነዋል፡፡ ብርቱ ክንዷ መጠቂያዋ ሆኗል፡፡ የማእከላዊ መንግስታትን ጥንካሬ ያዳከሙ፣ የተገንጣይነትን አስተሳሰብ ያፋፋሙ  የትጥቅ  ትግሎች እነዚህን ከፍተኛ ቦታዎች ማእከል ያደረጉ ነበሩ,፡፡ ናቸውም፡፡ ለነፍጥ አንጋች ቡድኖች መሸሸጊያ በመሆን የሀገሪቱን ሰላማዊ  የፖለቲካ ትግል ታሪክ ወደጋርዮሽ አለም ጎትተዋል፡፡ በወረራ ጦርነቶች ከፍተኛ የባህል የቅርስና የእሴት ውድመት የተስተናገደው በዚህ ቀጠና ነው፡፡ ከዚህም ቀጠና ነው። የመሰረተ ልማቱ ኋላ ቀርነት ለወሬም አይመች፡፡ የአባይ ዳር  ህጻናት በትራኮማ ብርሀናቸውን ያጣሉ፣ በንጹህ ውሀ እጦት ለበሽታና ሞት የዳረጋሉ፡፡ ወሎን ድርቅ ሲመታው፣ ትግራይን ረሀብ ሲያንገላታው፣ ወለጋ በማያቋርጥ አመጽ ውስጥ ስትዳክር፣ ……ቦታው የሰሀራ በረሀን እንጂ የአፍሪካን የውሀ ማማ አያሳታውስም፡፡  አፍሪካን ለመመገብ የማይሳሳ ሰፊ ለም መሬት ይዞ፣ “የአፍሪካ የውሀ ማማ“ እየተሰኘ እንደምን በአሰቃቂ የድህነት፣ የረሀብ፣ የበሽታ ተምሳሌትነቱ ሊጠቀስ በቃ?
ከመሰል ጥያቄዎች ጀርባ የግብጽ እጅ በግልጽም በእጅ አዙርም አለ፡፡ ይህ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚተልም ቀጠና እንዲዳከምና ትኩረቱ እንዲበታተን ሙሉ አቅሟን ትጠቀማለች፡፡ የኢትዮጵያን አንድነት በሚሸረሽሩ ድግሶች ላይ ሁሉ ሽክ ብላ ትገኛለች፡፡ የሰማይ  ጠቀሶቹን ተራሮች ጉልበት በተለያዩ መንገዶች በማዳከም የናይል ወንዝ እልቅናዋን ታስጠብቃለች፡፡

 “ያለጎረቤትሽ አይነድም እሳትሽ”
የግብጽ ሌላኛዎቹ ሜዳዎች ጎረቤቶቻችን ናቸው። የአንዳንድ ጎረቤቶች ታሪክ ከራስ ቤት ጋር ይመሳሰላል። ከወላጅ በላይ ተቆጪና አሳዳጊ ተጠሪ የሆኑ ጎረቤቶች እናውቃለን። በዚያው ልክ ኑሮን የሚያመሳቅሉ ጎረቤቶች ሞልተዋል። የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ከሁለተኛው ምድብ ውስጥ ይገኛሉ። ለጊዜው አምስት ጎረቤቶች አሉን። የነገውን ጊዜ ያውቃል። ቀጣናው መአት ያረገዘ በመሆኑ ምን ወልዶ እንደሚያድር ለመተንበይ ከፖለቲካል ሳይንስና ከመጻፍ ችሎታ የዘለለ እውቀት ይፈልጋል። ስለዚህ እስከአሁን አምስት  ናቸው ብለን እንለፈው። ኬኒያ፤ ሶማሊያ፤ ደቡብ ሱዳን፤ ጂቡቲ፤ ሱዳን እና ኤርትራ። ሁለቱ በቅርቡ በግንጠላ የተወለዱ ሀገራት ናቸው። ሶማሊላንድም 20 አመታት አልፎአታል፤ ከአንዳቸውም ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የፈጠርንበትን ጊዜ ማስታወስ ይከብዳል።
በሚገርም ሁኔታ በአራቱም ተፋሰሶች በኩል ሁለቱ ሱዳኖች ያዋስኑናል። ኤርትራንም አልረሳንም ። ከሶስቱም ጋር ያለን ግንኙነት ሰላማዊ አይደለም። ማለቂያ የሌለው የደቡብ ሱዳን ጉዳይ፤ በድንበር ጉዳይና በገንጣይ አስገንጣይ ክስ ከድፍን ምእተ አመት በላይ የምንወዛገባት ካርቱም፤ ከሁለት አመት በፊት በወይራ ዝንጣፊ የታረቅናት አስመራ!
ከሁሉም ጋር በጥርጣሬ የተሞላ፤ አንዱን ለአንዱ በማያስተኛ የፉክክርና የመጠፋፋት ስሜት የታጀለ፤ በበቀልና በቁርሾ የወረዛ የእርስ በርስ ታሪክ ነው ያለን። ይህ መራር ሀቅ ራሱ፤ በቀጥታ ከወንዙ ጋር የተያያዘ ለመሆኑ አያጠራጥርም። ከሁለቱ ሱዳኖችም ሆነ ከአስመራ ጋር ባለን ድፍርስርስ ታሪክ ውስጥ የግብጽ እጆች በረዥሙ ነበሩበት። ወደፊትም መኖራቸው ይቀጥላል።
 
የአማራ የቤኒሻንጉል፤ የትግራይና የኦሮሚያ ክለሎችን በቀጥታ ይነካሉ። ‘ብሉ ናይል’ በተሰኘች ግዛታቸው ብቻ የአለም ሁሉ ችግር የሚወዳደር ፈተና ማስተናገድ ከጀመርን ቆይተናል። አራቱም የግብጽ ከተሞች ናቸው ያልናቸውን ተፋሰሶች በሙሉ ያገኙዋቸዋል።
የሁለቱን ሱዳኖች ሁለንተናዊ አቅም ማዳከም፤ ለግብጽ የመጀመሪያው ስኬት ነው። አራቱም ሰብ ቤዚኖች አጥለቅልቀው ከሚያልፉዋቸው መስመሮች አንዱ ምስራቃዊው የሱዳን ክፍል ነው። የፍሬሽ ውሃ ማጀት፤ የለም አፈር ኪስ፤ የወርቅ ማማ ነው። የክብት ሀብቱ አይነገርም። 72 ከመቶ የሱዳን የቁም ከብት ኤክስፖርት የሚደረገው በዚህ መስመር ነው። ግን ድርቅ፤ በሰፋፊ እርሻዎች ምክንያት ወረራና መፈናቀል፤ የተፈጥሮ ሀብት መበዝበዝ መራቆት፤ የታጣቂ ቡድኖች የሀብት ሽኩቻ፤ የድንብር ግጭቶች ወዘተ በጣሙን ያዳከሙት አሳዛኝ አካባቢ ነው።
የደቡብ ሱዳንም አይወራም። ይሄም ለግብጽ አለሟ ነው። ብትችል ጥንቅቅ አድርጋ የምትቆጣጠርበትን እድል እስክታገኝና ልቧ እስኪረጋጋ በዚሁ ቢቀጥልላት ደስተኛ ናት። ‘የጥንቱ የግብጽ ኮንዶሚኒየም’ የሚባለው የእንግሊዝ ሽንሸና ተመልሶ ቢመጣላት ደስተኛ ናት። ግድቦች አስከመስራት የደረሱ ወዳጅነቶች፤ የጦር ካምፕ እንመስርት እስከሚሉ ዝምድናዎች ከጁባ ጋር መጣመር ትሻለች። ትሞክራለች። ይሄ ያላረጀና የማያረጅ አላማዋ ነው። “በእርግጥ እሷ ናት እንዲህ ያደረገችው” ብዬ የትግራይ ኦንላይን አይነት ትንተና ለመስጠት አይቃጣኝም። የቻለችውን በመተባበር የማትችለውን በማጨብጭብ አግዛለች። አብዛኛው ግን በእሷ እና ለእሷ በተሰሉ ዋጋዋች የመጣ ኪሳራ ነው፤ ሱዳንን እያማቀቀ የሚገኘው።
የብሉናይልን ግዛት “microcosm of Sudan” ይሉዋታል። ትንሽዬዋ ሱዳን አምሳያ እንደማለት ነው። የትልቁ ሱዳን ማሳያ። ጨዋታው ሁሉ ከያቡስ፤ ወንዝ ጋር የተያያዘ ነው። የብሉ ናይልን ውሃ ለመቀራመትም ሁነኛ ቦታ ናት። የኢትየጵያን ለም መሬቶች ለመያዝም፤ በአራም አቅጣጫ ለማመስም የሚያህላት የለም።  የሸርቆሌ ካምፕና ወንዝ እንዲሁም ተከታታይ ጥቃቶችን ማስታወሱ አይከፋም። ‘መጤ’ ፣ ‘አረብ’ እና ‘ባላገር ‘ እየተባባሉ በሶስት ቡድን ይጠዛጠዛሉ። በደቡብ ሱዳንና በኢትዮጵያ ብቻ ከዚህች ግዛት የተገፉ 150ሺህ ስደተኞች ይኖራሉ። እዚያው ደግሞ 200ሺ ያህሉ ተፈናቅለዋል።
የብሉ ናይልና የደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ጣጣ ሚስጥሩን በደንብ እየመለሰልን ይሄዳል።  አካባቢዎቹ በካርቱምና በጁባ ሀብታም ፖለቲከኞችና ነጋዴ ወዳጆቻቸው የተፈጥሮ ሀብቱን የተቀማ አካበቢ ነው። በተለይም ብሉ ናይል ለእኛ ከጎረቤትም በላይ ናት። ሁለቱ ሱዳኖች ለሁለት ከፍለው መከራ ያበሏታል። በአፍሪካ ዩኒየን እና በመለስ ዜናዊ አማካይነት የቀረበውን የስምምነት ማእቀፍ ጁን 26 2011  አልበሺር አልቀበልም ያሉላት አደገኛ ስፍራ ናት። የብሉ ናይልን ብጥብጥ ዋና ምክንያት ከ1960 ጀምሮ አካባቢው ላይ የግብጽንና የገልፍ ሀገራት ሀብታሞች በእርሻ ስም መስፈራቸው እንደሆነ ሀገር ያውቃል። የሰፋሪዎቹም ግብ ወንዞቹ ናቸው!! የማይመጣባቸው የለም፤ ለካርቱም አበጋዞች የማእድን ብዝዛውን ወጥረው ይዘውላቸዋል። ከቻይና እስከ ፈለታ ያልሰፈረ የለም። የበሺር ፕሮክሲ ቡድኖችም ይዞታቸውን አይለቁም። የእኛዋ ህወሓትም ተወካዮች አታጣም።
የክሮማይት ማእድን ከብሉ ናይል እስከ አሶሳ ደረስ ይዘረጋል። ኦሮሚያ ዩብዶ፤ ብር ብር ወንዝ ድረስ፤ ጊምቢን ይጠቀልላል። ቱሜት ወንዝ፤ የኬንቲቻ ኮረብቶች ያቡስ ወንዝና የአሶሳ ፖለቲካ መገኛቸው እዚህ ነው። ኮሌራ፤ መፈናቀል፤ ጎርፍ፤ ረሃብ፤ ስደተኛ ካምፕ፤ ጸጸ ፍላይ ወዘተ የዚህ ቀጠና መለያዎች ናቸው። እርዳታ ሰጪ ይርመሰመስበታል። ሪሰርች፤ ዳታ፤ እርዳታ እያለ የያዘውን ይዞ ይተራመሳል። ከኖርዲኮቹ እስከ አልቤርታዎቹ፤ ከቦሮቹ እስከ አቦርጂኖቹ ሁሉም አሉ።
ጥቃቶች ግድያዎች እንደአየር ሰፍነዋል። ከኩርሙክና ጌይሳን ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ የሚሰነዘሩትን ጥቃቶችና ግባቸውን መመርመር ለማንም ከባድ አልነበረም። ይፈለጋሉ።  Sudan’s Spreading Conflict (II) War in Blue Nile የሚለው የቻታም ሀውስ ሰነድ በዝርዝር ያብራራዋል።  ያው የራሳቸው ፊልም ስለሆነ ይሆናል!
SPILLING OVER Conflict Dynamics in and around Sudan’s Blue Nile State, 2015–19 ይሄም በጣም የተደራጀ ጥናት ነው። Khalid Ammar Hassan ጽፎታል።
የብሉናይል ግዛት ጉዳይ፤ ከቤንሻንጉልና ከኦሮሚያ ክልሎች ጋር በቀጥታ የሚያያዙ ጉዳዮች ይኖሩታል። ከላይ የተገለጹትን ችግሮች ተንተርሶ፤ መፍትሄዎቹን ማሰሱ አይከፋም።
 አስመሪኖ
ኤርትራ ከህወሓት ክፉ ቀንበር የምትላቀቅበትን አሰልቺና አታካች ጉዞ ስታደርግ ያለተጠቀመችው የስንቅ አይነት አልነበረም። በሰሜን ምስራቃዊው የሱዳን በረሃ አስታጥቃ ጂኦ ፖለቲካሊ ረብሻዎችን ያካሄደችባቸው ቡድኖች ተመልሰው ሊነሱባት የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው። አሁን በፍጹም የማታልፈው እድል ላይ ናት። ይሄ መስመር የሞት ሽረት ትግል ማካሄጃ ይሆናል። ከጉልበተኛ እስከ አጃቢ በዚህ  መስመር ፍላጎት የሌለው አካል ማግኘት ይከብዳል። ዘላለማዊ ጠላቶቹ ቻይና እና ህንድ የወርቅና የነዳጅ ድራማቸውን ይተውናሉ።
የቤጃ ታጣቂዎች ጥቃት እየፈጸሙ ወደ ኤርትራ ይሸሹ ነበር።  እንደሙጃሃዲን ምልምሎች አሳዳጊያቸው ላይ ዞረው፤ “ዘንድሮ የምስራቃዊ ሱዳን የነዳጅ መስመሮችን ራንሰም ሊይዙ ይችላሉ፤ አዲስ የሺአ ታጣቂ ተነስቶ ሊያተራምሰው ይችላል” የሚሉም አይጠፉም።
 ”ከባህር መነጠያዎች“
ከማስታጠቅና ከማሰልጠን በተጨማሪ፤ የሬዲዮ ጣቢያ ማሰራጫ እስከመሆን በደረሰ አጋርነት የኤርትራ ተገንጣይ ቡድኖችን የደገፈችው ግብጽ፤ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ የማድረግ ግቧን አሳክታለች፡፡ ግብጽ በቀጥታ ከፈጸመቻቸው ጥቃቶች ባሻገር በቀይ ባህር ፖለቲካ የበላይነቷ በመጠቀም በሀያላኑ ሀገራት እየተከለለች ፍላጎቶቿን አሳክታለች፡፡ እንግሊዝ፣ ጣሊያንና ፈረንሳይ የሌሉበት የኢትዮጵያ ችግር የለምና የግብጽን ፍላጎት ማሳካት እጅግ በጣም ቀላሉ ስራ ነው፡፡  
”ጅቡቲ የጥገኝነታችን መስፈሪያ“ የአቶ በለጠ በላቸው መጽሀፍ ውስጥ፤ ግብጽ በጂቡቲ ያሳየቻቸውን ጸረ
 ኢትዮጵያ አቋሞች አብራርተዋል፡፡ የጅቡቲ ጉዳይ ምን ያህል የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ላይ እንደጣለና፣ ሀገራችንን ለማገገም በሚያስቸግር ደረጃ እንዳዳከመ በስፋት ተተንትኖ ይገኛል።
አንዋር ሳዳት፤ ሶማሊያ ጦር አዝምተናል የሚለውን ሀቅ ካለአደባባይ አያወሩትም ነበር። ይሄም ከህንድ ውቅያኖስ የመነጠል ድራማዋን በደማቁ ያሳያል።
 
ወዳጆቿ ከጠላቶቿ

 ከአውሮፓም፤ ከአሜሪካም፤ ከመካከለኛው ምስራቅም ወዳጆች አሉዋት። ጠላቶቹም ከዚያው አይርቁም። ተዋውቀዋል፤ ተስማምተዋል። ከእኛ እሱዋ ትበልጥባቸዋለች፤ ለእሱዋ እኛ እንበልጣለን። ስለዚህ፤ በእነሱ ሚዛን እኛ ከእሷ እናንሳለን (ይሄ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የነበረው ፕሪቴክስት ነው። በቅርቡ አንዳንድ ማስተካከያዎች የተደረጉ ይመስላሉ። እንመለስባቸዋለን) ነገርዬዎቹን በአምስት እንክፈላቸውና ነካ ነካ እናድርጋቸው። እስካሁን ከምናወራቸው ጉዳዮች ጋር የሚተሳሰሩ ነጥቦች ይባዛቸዋል።
 
     1) የሚጣሉባት (ፈረንሳይ እና እንግሊዝ)፤
     2) የሚጣሉባትም የሚያጣሉዋትም (ገልፎቹ)፤
     3) ያመለጠቻቸው (እነቱርክ)
     4) የማያውቋት (ሎካል ወዳጆች)
     5) ጃንሆዮቿ (አሜሪካና ቻይና)
 
 ፈረንሳይና እንግሊዝ
 
The European Struggle for the Nile Valley and the Motives and Factors Behind the British Decision to Invade the Sudan ይላል ርዕሱ፤ Korean Minjok Leadership Academy  አሳትሞታል።  የLee Jaehyun ጽሁፍ ነው። 2011 ለንባብ በቅቷል። በናይል ጉዳይ፤ በርካታ ድርሳናትን ያገላበጡም በሆኑ በዚህ ጽሁፍ ካልተገረሙ፤ ይገርመኛል።
የፈረንሳይና የእንግሊዝን የናይል ተፋሰስ የ150 አመታት ግብግብ ዛሬ ላይ አምጥቶ የሚያሳይ ድንቅ መስታዎት ነው። ግልጽ ከመሆኑ የተነሳ ሊያደናግር ሁላ ይችላል። አንዳንዴ ግልጹም ይደበቅ የለ? የዛሬን ታሪክ እየነገረን ይመስላል። ከተወሰኑ ለውጦች ውጪ የኢትዮጵያ የዛሬ ፖለቲካ ከመቶ አመታት በፊት የነበረውን እየደገመ ለመሆኑ በእግረ መንገዱ ያጫውተናል። የዋና ዋና ተዋናዮቹ ተሳትፎም ዛሬ ከሚኖሩት የሀይል አሰላለፍ ለውጦች ጋር ተዳምሮ ታሪክ ራሱን እየደገመ ለመሆኑ ማሳያ መሆን ይችላል።
“በላይኛው ተፋሰስ ላይ የነቃና የሰለጠነ ሀይል ከኖረ ግብጽ አለቀላት፤ በቁጥጥሩ ስር ያውላታል” የሚለው አስተሳሰብ የእንግሊዞቹ እንደሆነ ቃል በቃል ይነግረናል። “ስለዚህ ይሄ ሀይል በተለያዩ ስልቶች ይዳከማል፤ በጉልበት ይንበረከካል፤ በእጅ አዙር በቁጥጥር ሰር ይውላል። ዘላለሙን ለማኝ፤ ሁዋላ ቀር፤ ያልሰለጠነ እንደሆነ ይኖራታል። ግብጽ ሙሉ በሙሉ ምንጩን ከእጇ አስገብታ እፎይ እስክትል ድረስ በዚሁ መልኩ ይቀጥላል” የሚል አይነት ነው፤ የአስገራሚው ጽሁፍ መልእክት። የትግራይ የዛሬ ኩርፊያ፤ የኤርትራን የዛሬ መነጠል፤ የፋሾዳን የትላንት ፍልሚያ፤ ወዲህ እያመጣ ወዲያ እየመለሰ ያስቃኛል። ከማክረንና ከዐቢይ ስም በስተቀር የጎደለው ነገር የለም። አዲሱ ነገር፤  ድል ለፈረንሳይ ያደላች መምሰሉዋ ነው።
The Belgian Campaign in Ethiopia A trek of 2,500 miles through jungle swamps and desert wastes የሚለው ደግሞ የGeorge Weller ጽሁፍ ነው። ይሄም ተመሳሳይ ትርክቶች አሉት። ሁለት መቶ አመታ ት ለመድፈን ትንሽ ስለቀረው ታሪክ ነው የሚያትተው። ነገር ግን ሰሞኑን፤ የብራሰልሱ መንግስት ለዐቢይ ስለጻፈው ደብዳቤ የሚያወራንም ይመስላል። በዚህ ሁለት ምእት አመት ሊደፍን ትንሽ ከቀረው ድርሳን ውስጥ የዛሬውን የናይል ተፋሰስ ውሎ አዳር መፈለግ አይከብድም። የምእራብ ኢትዮጵያ፤ የወለጋ፤ የሰዮ ተራራ፤ የአሶሳ ገጾች ላይ የራስን ታሪክ ለመጻፍ የተደረጉ ተጋድሎዎችን ያትታል። ቤልጂየም አሶሳ ላይ ባንዲራዋን ለመትከል መጋደሉዋን በኩራት ጽፈውታል። የአውሮፓ ህብረት ዛሬ የገባበትን ቅርቃር፤ በእነጀርመን የተገለበጠውን የእነ እንግሊዝ ኔት ዎርክ ወደሁዋላ መልሶ ያስቃኘናል። ነጠብጣቡን እየቀጣጠሉ መተርጎም የእኛ ድርሻ ይሆናል።
ስንቋጨው፤ የፈረንሳይ ወዳጆች ነንና፤ ግብጽና እንግሊዝ ደስ አይላቸውም። ፈረንሳይን መምረጣችን የህወሓት ሳይንቲስት ተንታኞች እንደሚሉት ‘አላዋቂነት’ አይደለም። ማሳያው ደግሞ፤ እንግሊዝን የመረጡት የት እንደደረሱ እያየን ነው። የሉም! እነ ስብሃት ነጋ የእንግሊዝ እቁባቶች ነበሩ። 

ገልፎቹን መገልፈፍ  (የሀብታም ደሃዎች)
እነዚህ ሀብታሞች ናቸው። ‘የእነሱ ፔትሮ ዶላር ስንት ጉድ ያመጣል’ ሲል ሃይሌ ፊዳ እንደተነተነው፤ የማይቆጠር ጉድ ከማይቆጠር ካዝና  ሲግተለተልበን ስንት መስከረም ሄደ። እነሱ እህል እና ውሃ ከቸገራቸው ቆየ። ነዳጅ ደሞ ተርፎአቸዋል። እነኢትዮጵያ ደሞ ውሃው አላቸው አፈሩ አላቸው። አውሮፓውያኑንና አሜሪካውያኑን ደግሞ ነዳጁ እምቢ አላቸው። አሜሪካ በቅርቡ ተገላግላለች። ስለዚህ ለአረብ ነዳጅ ሲባል፤ የእኛ አፈርና ውሃ ፎር ግራንትድ ተሰላ። አውሮፓውያኑ ቀድመው ሀይጃክ አድርገውታል። ገልፎቹም እንዳቂሚቲ የራሳቸው ለማድረግ ደፋ ቀና ይላሉ። ግብጽ ቱቦ ናት፤ የመርከብ ወደብ የእነሳውዲን ነዳጅ ለአውሮፓ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረቢያ ተመራጭ መስመር ናት። እሱዋም ትሸጣለች እንደአቅሚቲ። በነዳጅ ሀብቱዋ ከእነ ዱባይ ባትጠጋም በውሃ ችግሯ ግን ተመሳሳይ ናት። የእሷ የሚለየው ናይል የሚባለውን ውድ ስጦታ ሄሮደተስ በጥቅስ አጽድቆልኛል ማለቱዋ ብቻ ነው። ኢትዮጵያም አለመካዱዋ ሌላው ስጦታ ነበር። እሱዋ ማመናችንን ካደች እንጂ።
ይሄንን ውሃ ለመቀራመት ነው ገልፎቹ ካይሮን ገዝተው አሌክሳንደርያ ላይ የከተሙት። የእነሱን ውሃ ለመያዝ ነው አውሮፓውያኑ ናይል ላይ ጦርና ተንኮል የሚሰብቁት። በእርግጥ መያዝ ብቻም አይደለም፤ ለራሳቸውም ያመርቱበታል፤ ጥጡ ልዩ ነው (የደቡብ ሱዳንን አፈር የጥጥ ነው ይሉታል)። ከራሳቸው ጥጥ ሲተርፍ ደግሞ የገልፍ የነዳጅ ሻጭ የሸቀጥ ገዥ ደንበኞቻቸውን አልፋአልፋ ያመርቱበታል። የከብት መኖ ነው። ስንዴና ሩዝ ይተክሉበታል። ይሸጡላቸዋል። ከእዚህ ሁሉ ሲተርፍ ነው የሚተውላቸው።
የአስዋን ግድብን የከበቡት ትላልቅ የእርሻ ማሳዎች የእነዱባይ ናቸው፤ የእነሳውዲ ናቸው። በጋምቤላ ውሃ የሚቀልዱት የሳውዲ፤ የህንድ፤ የዱባይ፤ የፓኪስታን ኢንቨስተሮች በሙሉ  የሚያርሱት ለእነ አቡዳቢ ነው።
አስዋን ትንሹም ፤ የሴናር ግድብ በግብጽ የአባይ ጥገኝነት ምክንያት የተፈጠሩ ናቸው። ሱዳንን እንግሊዝ አምጣ የወለደቻትም በዚሁ የግብጽ ጥገኝነት ምክንያት ለብላክ ሜይሊንግ ፈልጋት ነበር።  ናይል ወንዝ ላይ የተንተራሱ የፕሮጀክቶች በሙሉ የሱዳን ሀገራዊ አድገት መወሰኛ ተደርገው እንዲወሰዱ ያስገደደው ይሄው ድርማ ነበር። ለግብጽም የህልውና ጉዳይ ስለሆነ፤ በዚህም ሳቢያ በሱዳን ግድቦችን መገንባት በእነሱ መስኖ ማልማትና ሀይል ማመንጨት የእድገት ብቸኛው ቁልፍ ተደርጎ ሲወሰድ ቆይቶአል።  ይህ በብሉ ናይልና በደቡባዊ ኮርዶፋን ግዛት በጃፋር ኒሜሪ የተመራው የግብርና አቢዮት፤ ሳውዲ አረቢያንና የገልፍ ሀገራትን አስከትሎ ነበር። በብሪታኒያ ፊት አውራሪነት ተዘውሮአል።  በዝናብ እርሻ ፋሽን በርካቶችን አፈናቅሎ፤ አካባቢውን ለዛሬ ጣጣው ዳርጎት አርፎአል። እኛም ዘንድ ከንጉሱ ጀርባ የነበሩት የበኪንግሃም ሰዎች፤ ከሱዳን የምንዋሰንባቸውን ድንበሮች፤ ‘እረሱ አሳርሱ’ እያሉ ለግብግብ ዳርገውናል።
እነዚህ አካባቢዎች እኮ ቢንላደን መሬት ገዝቶ ሊያርስ ሲሞክር የታዘብንባቸው የጉድ ገጾች ናቸው። በእርግጥ ከእነሱ አይብስም። ነገሩ ግን ምን ያህል ፖለቲካዊ ትርጉምና አለምአቀፍ መልክ እንዳለው ማሳያ ይሁነን።
ዛሬም የእነዚህን አካባቢዎች ለም የእርሻ መሬቶች ከእነሱ ውጪ የሚዋጋበት የለም። የሰሞኑን የሱዳን ድንበር ሴራም ከእነሱ ሌላ ማንም አይነካው።  የእነ ቻይና አዳዲስ ጉልበት ተጨምሮበት፤ የዋሺንግተን እልህና የመልስ ምት ተደምሮበት ገና ፍዳችንን እንቀምሳለን። ሰሜናዊ ሱዳን፤ ካርቱም  ወ ጁባ የትንቅንቁ ገበያዎች መሆናቸው ይቀጥላል። ይሄ ሁሉ ለግብጽ ድል ነው። ለአውሮፓውያኑና ለገልፎቹ ሌላ ሸክም ነው።  ከለም መሬት ፍልሚያው በስተጀርባ የህገወጥ ንግዱ አይነት ይስተናገዳል። ከከብት እስለ ሰው፤ ከሽጉጥ እስከ ቪያግራ፤ ከቡና እስከ ማር  የማይገባ የማይወጣ የለም። ከፖርት ሱዳን እስከ ላሙ ቀዳዳዎች ይዘረጋሉ።
 
ቱርክ
ቱርክ ከፖርት ሱዳን ሆና፤ በትዝታና እልህ ግብጽን ትገረምማለች። በታሪክና በገናናነት ግብግብ እነሳውዲን ትገላምጣለች። የኑቢያን፤ የሃላይብ ትሬይአንግልን፤ የቀይባህርን የምፅዋን  ቁስሎች  እያከከች ታደማለች፤ እንዳይጠግጉ ነቅታ ታድራለች። የጨዋታው ህግ ነው። እሱዋም ያልተሰማ በደል አላት፤ ከገፊዎቹዋ እኩል ያልተጮኸለት ጠባሳ አላት፤ ከሜዲትራኒያን ዳርቻዎች ያሳድዷታል። ዛሬም አላበቁም። በፋዚል ኪዛኩሬክ ግጥሞች ብሄረተኝነቱን የቃኘው ኤርዶሃን እስከመቃብሩ ጫፍ እጅ የሚሰጥ አይነት አይደለም። ብዙዎች ‘ሁሉንም እያጣ ነው’ ቢሉትም፤  እሱ ግን አይመስልም።  ሶፍት ዲፕሎማሲ ብሎ ሲመጣ ነገርዬው ከሀርድም የባሰ ይሆናል። ‘ዩ ካንት ጎ ባክ ቱ ኮንስታቲኖፖል’ እያሉ ለሚያሾፉት የሃሊውድ አላጋጮች አልተሸነፈም።  “ኢስታንቡል ኢዝ ናት ኮንስታቲኖፖል” እያሉ ቧልታይ ዜማ የሚሰሩባት አንካራ አንቀላፍታ አታውቅም። ለአውሮፓ ማርና ሰሟን፤ ለምስራቅ አፍሪካ ሽጉጥ ላይ ስሟን ጽፋ ትልካለች። በሽጉጦቹዋ ለሚወድቁት ሆስፒታል ትሰራለች፤ ጋደም ብለው እንዲዝናኑም ፊልም ትጋብዛቸዋለች። ተርኪይ አሜሪካን ሀገር ዶሮ ነው። እዚህ አፍሪካ ቀንድ ገደማ ደግሞ ተርንኪይ ናት። ክሮስ ከቲንግ ሶሉሽን ናት።
 
አሜሪካና ቻይና
“ዘንድሮ ሰላምም ሆነ ጦርነት ከአራት ዋና ዋና ነገሮች ይሰራሉ፡፡ ከአሜሪካ ከሩሲያ ከቻይና እና ከአውሮፓ ህብረት”፡፡ የራሴ ጥቅስ ነው።
በዛሬይቱ አለም እነሱ የሌሉበት ጦርነትና ሰላም የለም፡፡ አሜሪካና ቻይናን የቡድን አባት አድርጋቸውና አራቱን በሁለት ምድብ ክፈላቸው፡፡ አውሮፓ ህብረትን ለሁለቱም አካፍላቸው (ቦሪስ ጆንሰንን ወፈፌው ሲሉት ትዝ ብሎኝ ነው) ፤ ሩሲያን ለቻይና ስጣት፡፡ ሁለቱን ምድቦች እየተከተሉ መአት ጀሌዎች ይግተለተላሉ፡፡ ኢራን ቱርክ ሰኡዲ አረቢያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኳታር የቡድን አባቶቻቸውን ቅኝት እየተከተሉ በሁለተኛ ደረጃ ተወዛዋዥነት ይሰለፋሉ፡፡ ለእኛዋ ጉድና ለመሰሎቿ ቅኝት ለማሲያዝ እንዳትሞክር፡፡ ደሀ ምን ቅኝት አለው? የሀብታም ኪስ እያየ ጎንበስ ቀና ከማለት ውጪ፡፡   ይል ነበር መለስ ዜናዊ። ዐቢይ አህመድ ሲል ብቻ ለሰሙት ማስታወሴ ነው።
ሁለቱ የቡድን አባቶች እዚህም ባይኖሩ ይገርም ነበር። በታሪፍ ግብግብ እየተቃኘ፤ በኮሮና ጦዞ፤ አሳማና አኩሪ አተር ላይ ሳይቀር ጥይት ለሚያርከፈክፈው  የሁለቱ ሀገራት ሽኩቻ፤ ሰፊውና ረዥሙ የናይል ተፋሰስ ምቹ አለም ይሆናል። ከክሮማይት አሰከ ወርቅ፤ ከማሽላ እስከ ነዳጅ የማይሳል ቀስት አይኖርም። በሰላም ማስከበር ጦስ ሬንጀራቸውን ለብሰው ከገቡ ቆይተዋል።
 
ሎካል ወዳጆች
በነገራችን ላይ የተፋሰሱን 10 ሀገራት ‘በግብጽ እየተበዘበዙ እንደሆነ፣ መብታቸው እየተገፋ እንደሆነ ለማሳመን’ እና የትብብር ማእቀፍ ወደተሰኘው ሰነድ ፊርማቸውን ለማምጣት ከ10አመት በላይ ፈጅቶ ነበር ። ይሄ ነው አንዱ ሎካል ወዳጅ። ሳያውቁዋት ግብጽን ይፈሩዋታል፤ ወይም ራሳቸውን አያውቁትም፤ ህዝባቸውን አያውቁትም። ከወንዝ ሀይል እንደሚመነጭ ላያውቁም ይችከላሉ (አያፍሩም መቼም) ። ሙባረክን ከኦባማ ጋር ፎቶ ሲነሳ አራት ኪሎ ደውለው ሊሳደቡ ሁላ ይችላሉ። ከእነዚህ ጋር ሆኖ ግብጽን መታገል በራስ አንደመቀለድ ሆኖ ቆይቶአል። አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወቅት ከሚያወሩትና ምርጫ ሲደርስ የሚያወሩት እንደተለያየ ነው። ሙሴቬኒ ግድቡን እፈልገዋለሁ ቢልም፤ የደቡብ ሱዳንን ሸቀጥ ማራገፊያነት ማንም እንዲነካበት አይፈልግም። ኬኒያም የግድቡን ሪፖርት በሰማች ቁጥር ከግብጽ ጋር ላሙን ስለማልማት ያወራችውን ለመከለስ መደዋወሊዋ አይቀርም። ለግብጽ ይሄም አለሟ ነው።
የራሳችን ነጋዴዎቹ ደሞ አሉ፤ ፖለቲከኛም ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሀይማኖተኞችም ሊሆኑ ይችላሉ፤  አስመጪና ላኪም ሊሆኑ ይችላሉ። ወናው ቢዝነሱ አትራፊ መሆኑ ላይ ነው፤ ህዳሴ ግድቡን ተቃውሞ ካይሮ ላይ ሰልፍ ሊያካሂድ ዝግጁ ነው። የማይሰራ ተርባይን ሊገጥም ዝግጁ ነው። በፌክ ኒውስ ግድቡን ሲተገትግ ለመኖር ዝግጁ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩን መምቻ ለማድረግ ዝግጁ ነው። ታጥቆ ለመታገልም ዝግጁ ነው። በቀፍታ ሁመራ በኩል ካይሮ ቅርብ ሆናለች አሉ!!
 
ህወሓት
ሰፊዋ የግብጽና የወዳጆቹዋ ሜዳ። በቅርቡ እንዳስተዋልነው፤ “ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ መሳሪያ ገዝታ ለግድቡ ልትተክል እንደሆነ ፤ ከህወሓት አመራሮች ሰማሁ” እያሉ የሚጽፉ የግብጽ ሚዲያዎችን እየተዋወቅን ነው። መቼም ዘንድሮ ተገርማችሁ ሙቱ ብሎናል።
እነዚህ ከሀገር ጉዳይ ጋር የሚተሳሰር ሽራፊ ልቦና የሌላቸው፤ የነጋዴ ማህበርተኞች፤ ምንም ለማድረግ ዝግጁ ናቸው። “ወደስልጣናችን መልሺንና ግድቡን በጋራ እናስተዳድረዋለን የሚል ፕሮፖዛል ይዘው ሄደዋል” እያሉ የአስመራ ጆሮ ጠቢዎች ይሳለቁባቸዋል።
የተከዘ አጥባራን ፖለቲካ ይዞ ለመጫወት የሚደረገው ሙከራ፤ ብዙዎቸን ዋጋ ሳያስከፍል አይገባደደም።  ግቡ ያወ ውጥረት መፍጠር፤ ማዳከም ነው። በተዋሳኞቹ ከበሽሎ ተፋሰስ እስከ አንገረብ ጉራንጉር፤ አሰከ ሰቲት መውጫ፤ ወደከሰላና ካርቱም የሚዘልቅ የነውጥ ምእራፍ ለመግለጥ ይሞከራል። 
 
የእጅ አዙር ጥቃቶች፤
ግብጽን በእግረመንገድ የሚያግዙ ከበርቴዎችም አይጠፉም ለማለት ያህል ነው። ከወዳጆቹዋ ስራዎች ጥቂቶቹን እንያቸው እሰቲ፤

“በርታ እያሉ ማዳከም”
በተለያዩ መንገዶች ይተገበራል። ለምሳሌ፤ የአባይ ተፋሰስ ባለስልጣን የሚባል ተቁዋም አለ። እድሜውም በጀቱም የሚናቅ አልነበረም። ባህር ዳር ላይ ዋና መቀመጫውን አድርጎአል። ዝርዝርዝ ስራዎቹን ከመንገሬ በፊት፤ ጣና ላይ የደረሰውን የእንቦጭ ወረራ መከላከል እንዳልቻለ ልጥቀስ። ስለዚህ ሌላ ነገር እናወራ አይደል?
ይሄ ከጨዋታው ጠባዮች አንዱ ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። ለትዝብት ቅርብ የሆኑ፤ ከስራቸው ይልቅ ነገረ ስራቸው ጎልቶ የሚወጣ፤ ስማቸው ብቻ የተሽሞነሞነ ፕሮጀክቶች ይቀረጻሉ። ቢሮች፣ ጽቤቶች፣ ኮሚሽንና፣ ካውንስሎች፣ ሴክሬታሪያቶች ይዋቀራሉ። ታስክ ፎርሶች ይደራጃሉ። ኢኒሼቲቮች ይቀረጻሉ። ሳይንቲስቶች ይሰባሰባሉ። በሰአት የአንድ መምህር ደሞዝ እየበሉ፤ በአበል፤ በስብሰባ በሴሚናር፤ በጥናትና ምርምር፤ በፓይለት ስተዲ፤ ወዘተ በጀቱ ያልቃል። ዋናው ጉዳይ የለም። ስልጠና እየሰጡ፤ እያጠኑ፤ እየተሰበሰቡ፤ እየተመራመሩ ቫይረሱ ስራውን ይጨርሳል፤ ሲያሰኘው ባክቴሪያ ሆኖ አዲስ ስራ ይጀምራል። ‘ጣና ፎረም’ ተባብለው የምስራቅ አፍሪካን ጂኦፖለቲክስ ሲተነትኑ ጣናን እንቦጭ ይበላዋል። እምቦጭ ጂኦፖለቲካሊ፤ ሀይድሮሎጂካሊ፤ ጂኦግራፊካሊ፤ ኢኮኖሚካሊ ምናምን እንዴት እንደማይታይ የሚያሰረዳኝ ተአምር አፈልጋለሁ። ግሪን ሪቮሉሽን እየተካሄደ ነው አለማለታቸውም ያስመሰግናቸዋል። ከባድ ኢንቴሌክቹዋል ዲኬደንስ ሀገሪቱን ገዝግዞ ጥሎአል። Intellectual Decadence!  የዚህች ስድብ ባለቤት ዲግቢ አንደርሰን ይባላል። አንዲት ደስ የምትል ጥያቄ አለችው፤ “በሀብታሟና በጤናማዋ አሜሪካ የሚገኙ አዋቂ ሰዎች፤ ለምንድነው የራሳቸው የሆነውን፤ ጥሩውን ማህበረሰብ ይሄንን ያህል የሚጠሉት?” ይላል።  ዋይት ኮላሪዝም መንችኳል። ድህነትን ለማጥፋት ተሰማርተው ሀብታም ሆነው በሚመለሱ ኤሊቶች ተከብበናል። እናንተ ሪሰርቸርስ፤ ሪች-ሰርቸርስ፣ ሪግሰርቸርስ፣ ታውቃላችሁ፤ ግን አትኖሩትም። ለምን?
ይሄ ለግብጽ አለሟ ነው። አቅዳ ባተሰራውም አቅደው የሚሰሩላት አጋሮች ግን አሉዋት። በድረሲንግ ኮድ ሲያዳክሙላት ይውላሉ። በፕሮፖዛል አጻጻፍ ወጥረው እንደያዙላት መአት ክረምቶች ይመላለሳሉ። ዝናቡን ማንም አያቆመው፤ የእሷን ሀጃ ማንም አይነካት።
 
“አረንጉዋዴው ቅርምት”
 ‘Green Grabbing’? ይሉታል።  የጋርዲያኑ ጋዜጠኛ John Vidal ነው ይህንን ስያሜ በስራ ላይ ያዋለው። “መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን በአካባቢ ጥበቃ ስም መቀማት፤ መከለል መያዝ” እንደማለት ነው። በደን ልማት፤ በካርቦን ልቀት ቅነሳ፤ በእርጥበታማ መሬቶች ጥበቃ ወዘተ የፈሃ ሀገራት መሬቶችንና የተፈጥሮ ሀብቶችን በእጅ አዙር የመያዝ ጨዋታ ነው። ባለቤቶቹ እንዳይጠቀሙበት ለማድረግ ነው፤ በሚመች ጊዜም ይሁን አሁን ለራስ ጥቅም ለማዋል የሚጻፍ የድራማ ስክሪፕት ነው።
በዚህ በእኛ ተፋሰስ ውስጥ በስፋት ተተግብሯል። እየተተገበረም ይገኛል። ከአራቱ ዩኔስኮ ከመዘገባቸው የብዝሃ ህይወት ቅርሶች ሶስቱ የሚገኙትበባሮ አኮቦ በሚነሳባቸውና ገባሮቹ በሚፈሱባቸው አካባቢዎች ላይ ነው። የያዩ ጥብቅ የጫካ ቡና ፤ የሸካና የካፋ ባዮስፌር ጥብቅ ደኖችን ካርታው ላይ ይፈልጉ። በጋምቤላም የሚያስደነግጥ ስፋትያላቸው ሶስት ጥብቅ የአደን ስፍራዎች፤ አንድ ፓርክ ተከልለዋል። የጎብኚውን ቁጥር መተው ነው። በአለም ድንቅ ከሚባሉ ዌት ላንገዶች አንዱ የሆነውን የማቻር እርጥበታማ መሬት በውስጣቸው ይዘዋል። ጥብቅ ስፍራዎቹ የቱጋ እንዳሉ በካርታ ላይተመልክቶ መፍረድ ቀላል ነው። በላዩ ላይ የደቡብ ሱዳኑን ቦማ ፓርክ መደመር ነው፤ ማን እንደሚያስተዳድረውና ከምን ጋር የተያያዘ እንደሆነ ስናስብ ደግሞ የበከለጠ ስእሉ ይገለጥልናል። የእኛዎቹንም አሜሪካውያኑ ገብተውባቸዋል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ነው።  የአልጣሽ፤ የሰሜን ተራሮች፤ የሽሬ ፓርኮችም መገኛቸው እዚሁ ተፋሰስ ላይ ነው። የዳቡስና የአሰበ ተፈሪ ጥብቅ የአደን ስፍራዎችም ይጨመራሉ። ሁሉም በባሮ አኮቦ፤ እና በብሉ ናይል የተፋሰስ ክልል ውስጥ ይገኛሉ።
 
እነዚህ ስፍራዎች በከርሰ ምድር ውሃ ክምችታቸው የታወቁ ናቸው። ከታች ከእነ ጂሎ መፍሰሻ እስከ ተከዜ መውጫ ድረስ በሆዳቸው ንጹሁንና ውዱን ውሃ ይዘዋል፤ ሰማያዊውን ወርቅ። የደቡብ ሱዳንማ አይነገርም፤ ውሃ ናት!! ውሃ የበላት!!  ቅርመታውን ሰማያዊ ብንለውም የበለጠ ያስኬዳል። ውሃ ነው ግባቸው። ወንዙንና ስሩን መቆጣጠር የመጨረሻው ግብ ነው። ወንዙንና ስሩን መቆጣጠር የመጨረሻው ግብ ነው። የከርሰ ምድር ውሃ ፖለቲካ

(AQUIFER POLITICS) ይሉታል ይሄን ደግሞ።  
ብቻ በጥቅሉ፣ ለኢንደስትሪ ፓርክ፤ ለተቀናጀ፤ መንገድ፤ በህንጻና በዩኒቨርሲቲዎች የተያዙ፥ ስደተኛ የተያዙ፤ በወታደር ካምፕ፤ በቢሮ፤ የሜቲዎሮሎጂ ስቴሽኖች፤ የቴሌና የፖስታ ቤት፤ የመብራት ሃይል፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የመንገድ ዳርቻዎች፤ ለእንትን እየተባሉ የታጠሩ ቦታዎች፤ ለአንደኛና ለሁለተኛ ደራጃ ትምህርት ቤቶች ተብለው የታጠሩ  ወዘተ ግን ምንም አገልግሎት የማይሰጡ መሬቶችን መቁጠር የሚያደክምም ልብ የሚፈትንም ስራ ነው። ይሄ ሁሉ የአረምጉዋዴው ወረራም፤ የአረንጉዋዴው ረሀብም ማጠናከሪያዎች ናቸው። 
 
ችግርን ማድለብ
ድልብ  የሆነ ጊዜ ስድብ ሆኖ ነበር። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለተቃራኒው አውሎ ከሞት አንስቷታል። ቃል ማዳን ከባድ ነው። (አድናቆቴ አሰቆኛል መሰለኝ) ህወሓት ብቻ ከቃል አነሰ፤ አልድንም አለ። ቃል ለካ እውነትም ከባድ ነው። ለማንኛውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ‘ድልብ ሀብት አለን’ ሲሉ ሰምቼ ገለጻውን ወድጄዋለሁ። ወደ ግብጽ ጉዋደኞች እንመለስ፤ ችግር እንደሰንጋ ያደልባሉ። አንድን ቦታ ጎርፍ ለ50 አመታት ያህል በየአመቱ ይመታል። ሰውም ይሞታል፤ ቤትም በየአመቱ ይፈርሳል ። መፈናቀል በየአመቱ አለ፤ በመሬት መደርመስ መሞት በየአመቱ አለ፤ በእርስ በርስ ግጭት መሰደድ ሰብልን ለእሳት መገበር በየአመቱ አለ፤ ስደተኛን መቀበል በየአመቱ የሚበዛ ሰራ ነው፤ የማያልቁ ፕሮጀክቶች ብዛት በየአመቱ ይጨምራል፤ ይሄ ሁሉ ሰንጠረዡ ውስጥ በጻፍኩዋቸው ወረዳዎች ውስጥ የእለት ተእለት ተግባር ነው። በእርግጥ የሌሎቹም አካባቢዎቻችን መለያዎች መሆናቸውን አልክድም። እሱኝ በሌሎች አጫዋቾችና ተጫዋቾች የሚተገበር ጌም ሊሆን ስለሚችል ሌላ ጊዜ እንጫወተው ይሆናል። ለመተማ ወረዳ አስተዳዳሪነት፤ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ያልጨረሰ ካድሬ አስቀምጠን፤ ችግርን ከማድለብ ሌላ ምን ትርፍ ሊኖረን?
ጎበዝ! መተማ በምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ ስትራቴጂክ ከሚባሉ ገጾች አንዱዋ ናት። የሸቀጥ፤ የውሃ፤የጦር መሳሪያ፤ የድንበር፤ የታሪክ፤ የብዝሃ ህይወት ወዘተ ፖለቲክስ ማዳወሪያ የሆነ ቀጠና እኮ ነው። የሱዳንን የግብጽን ፍላጎት፤ ከአውሮፓውያን ወዳጅ ጠላቶቻቸው ጋር እያዋሃድን፤ በፖርት ሱዳን በሚገባው የሩቅ ምስራቅ ንፋስ እያበጠርን የምንፈትሽበትን  መነጽር እንዲህ ከሆነ የምንይዝው፤ ችግርን ከማክበር ሌላ ምን ስያሜ ሊሰጠው?

 

የእኛ ምላሽ ምን መሆን ይኖርበታል? የእኛ ድርሻዎች በሚለው ንዑስ ርዕስ ቀጥሎ እናየዋለን።

የእኛ ድርሻዎች
ይህ ክፍል፤ እንደመነሻ የሚሆኑ ጥቂት የመፍትሄ ሀሳቦችን ቀለል አድርጎ ለመጠቆም ይሞክራል። ስማቸውም ሆነ፤ አሰያየማቸው ለመንገድ መጠቆሚያ ያህል በመሆኑ አንዳነድ የስፔሊንግ ጨዋታዎችን ሲያዩ አይደናገጡ።

”አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ ጉርብትና”

(GREEN or Blue NEIBOURHOOD)

የአረንጓዴ አሻራ አንዱ አካል ተደርጎ ይወሰዳል። ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰኑ ክልሎቻችን ላይ (በተዋሳኝ ወረዳዎችና ዞኖች፤ እንዲሁም ቀበሌዎች ውስጥ) ፤ ድንበር በሚጋሩን ሀገራት ውስጥና የተፈጥሮ ሀብቶችን በተዘዋዋሪም ቢሆን ከሚጋሩን ሀገራት ጋር የሚሰራ ፕሮጀክት ነው። በእርግጥም ከቀሪ ተዋሳኝ ሀገራት ጋርም መስራት ይቻላል። ይገባልም።

እንደሚታወቀው፤ ከግማሽ ምእተ አመት በላይ በውዝግብ ከኖረው የሱዳን ድንበራችን በተጨማሪ፤ ከሶማሊያ ጋር ከምንዋሰንበት ድንበር ውስጥ ስምንት ያህል ወረዳዎች ‘Undetermined Boundary’ በሚለው ስም የሚገለጹ ናቸው። ይህ እንዳለ ሆኖ፤ እነዚህ የድንበር አካባቢዎች እጅግ ከልማት የራቁ፤ መሰረተ ልማት ያልተማላላቸው፤ ነገር ግን የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ በሚጥሉ የህገወጥ ንግድና መሰል አንቅስቃሴዎች የታወቁ ናቸው። ከአጎራባች ሀገራት ገሃር ያለውን ግንኙነትም ከዚህ የበለጠ የሚገልጸው ማሳያ አይኖርም። 

ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ፤ ድንበሮቻችንን በግሪን ግንብ መርሆች እንድናጥር ያደርገናል። ለምሳሌ የሱዳንና የደቡብ ሱዳንን ብንወስድ፤ ቀፍታ ሁመራ፣ በምራብ አርማጭሆ፣ መተማ፣ ቋራ፣ ጉባ፣ ሲርባ አባያ፣ ሸርቆሌ፣ ኩርሙክ፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ በተባሉት ወረዳዎች ላይ፤

በጥምረት፣ በግልና በመሰል ግንኙነቶች በሚዋቀሩ ቡድኖች አማካይነት የእርሻና የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መትከል ቢቻል ይመከራል። በሶፍት ቦርደር ፖለቲክስ ውስጥ ሃርዱንም ማቀናጀት ነው። የማንዴራ ትሬያንግልን ወሎ አዳር ለሚያውቅ ሰው ይህቺ መላ አትከብደውም። ለኬኒያ ተዋሳኝ መንደሮች ትምህርት ቤት መስራትና እዚያ እየሄዱ የሚማሩ ዜጎችህን ማግኘት አንደማለት ነው። ከዚያ እዘጨነዚያ መጥተው እዚህ ይሰራሉ። ድንበር ላይ ዛፍ ተክለህ ገናሌና ዳዋን መሸኘት ማለት ነው። ቀጭንም ብትሆን ወንዚቱ ያላትን ዋጋ በመገንዘብ በታንክ መጠበቅ ማለት ነው። ድንበሮቹ የእኛ አይመስሉንም፤ በእነሱ በኩል መሰስ ብሎ በሚገባ ጥይት ልጆቻችን ሲቀጠፉ መባነኑ ምንም አይጠቅምም።

60 ለማይሞሉ ወረዳዎች፤ የተቀናጀ አልሚ አንቂና አደራጅ የወታደሮች ቲም ማዋቀር እውነት ከባድ ስራ ነውን? አካፋና ጠብመንጃ ይዞ የሚንቀሳቀስ አረንጉዋዴ ወታደር ማፍራት ያን ያህል ከባድ ነውን?

አረንጉዋዴው ሰራዊት፤ ህገወጥ የሰው ዘውውርን ጨምሮ እነዚህ አካባቢዎች የሚታወቁባቸውን ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ይቆጣጠራል። የመሬት ወረራና ስርአት አልበኝነትን ይከላከላል። ‘በየአመቱ 300ሚሊዮን ዶላር በህገ ወጥ የቁም ከብት ንግድ እያጣሁ ነው!” ብሎ ሪፖርት ከሚያደርግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በዚህ መንገድ ካልሆን መዳን አይቻልም።

ለእነዚህ ስፍራዎች ብቻ የጥናትና ምርምር፤ የዶክመንቴሽን ስራ የሚሰራ መዋቅር ማደራጀት። በተለይም ከሁለቱ ሱዳኖች ጋር በአፋጣኝና በጥልቀት ቢገባበት ይመከራል። ሶማሊያንም በንቃት እያዩ። ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያሉንን ግንኙነቶች የሚወስኑዋቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ታሪካዊና ሚናቸውስ? የየአካባቢዎቹ እንቅስቃሴ ከሀገራችን ሰላምና ብልጽግና ጋርስ ምን አይነት ተያያዥነት አላቸው? ቦታዎቹ በታሪክ በኢኮኖሚ በስነህዝብ በሰላም በጦርነት ወዘተ ያላቸው ድርሻ ምን ይመስላል?  ስለ ጠላቶቻችንና ወዳጆቻችን ፍላጎቶች አሰላለፎች ስለእኛ አሰላለፍ ስለታሪካዊው ስለ አሁኑ ስለ ሀገራችን ፖለቲካ ስለ አለም አቀፉ ሚዛን ወዘተ ያጠናል።’  

ዌንጂኦስ (WENGos)

የአፍሪካ ህብረትም ሲያበረታታ ሰምተነዋል። ኢንተርናሽናል የእርዳታ ድርጅቶቹ የሚሰሩትን ስራ ለሀገር በቀል የእርዳታ ድርጅቶችም ማካፈል ያስፈልጋል። ደግነት፤ በጎ ፈቃደኝነት እምግሊዝኛ በመቻል፤ ፕሮፖዛል በመጻፍ ብቻ አይሰራም። ለብዙዎች የተሰጠ ጸጋ ነው። መንግስት የራሱን ሀገር በቀል ድርጅቶች ያደራጅ፤ በሚፈልገው ቅርጽ ይስራቸውና ይቅጠር። ዌንጂኦስ ይበላቸው። የእኛ ኤንጂኦዎች ማለት ነው። ስለ ውሀ ሀብታችን በተዋሳኝ ወረዳዎች ላይ የሚንቀሳቀሱ፤ ከውጪዎቹ በጎ አድራጊዎች ጋር፤ ከጎረቤት ተዋሳኞች ጋር አብረው የሚሰሩ፤ አካባቢውን የሚያለሙ፤ ብዙ ደረጅቶችን መመስረት ይችላል። ፈንድ እየፈለገ ይከፍላቸዋል።  

ETHIO SYNONYMS

ቻይና ለዘላለም በጥንቃቄ ትኑር። የአለም ባንክ ከግብጽ ጋር ሆኖ ፈንድ በማስከልከልም ሆነ በመከልከል፤ በህወሓት መራሹ መንግስት ይብጠለጠል ነበር። ህወሓት ዞር ትልና ደግሞ ናይል ቤዚን ኢኒሼትቭን አቋቁማ የትብብርና የልማት ስራዎችን እየሰራሁ ነው ትላለች። የናይል በዚን ዋና ፈንድ አድራጊ ማን ነው?አለም ባንክ። ለምሳሌ፤ ኢኒሼቲቩ Nile Basin Trust Fund (NBTF), የተባለ ፕሮግራም አለው፤ የውሃ ልማት ስራዎችን ለማከናወን ለሚፈልጉ አባል ሀገራት  ፈንድ ያቀርባል፤ አስተዳዳሪው የአለም ባንክ ነው። ይሄ ያኔም ነበር ወደፊትም የትም አይሄድም ለማለት ያሀል ነው።

አሁን መንከባከብ ቻይናን ነው። ከጠገበው የራበው ይሻላል። ለዚህ ግድብ እዚህ መድረስ የቻይና ውለታ በቃላት አይገለጽም። ለእኛ አይነቱ ሀገርም እንደሱዋ ያለ አጋር ማግኘት የማይታሰብ ነውና ፤ ቻይናን እናጥብቅ። በቴክኒክም በእውቀትም በልቦናም በጥንቃቄ ከያዙዋቸው ከግብ ያደርሳሉ። እንዳቀራረባችን ነው።

                           Portable initiative

የወደብ አገልግሎት ከሚሰጡንና እንዲሰጡን ከምናስባቸው ሀገራት ጋር ፤ እንዲሁም በአዳዲስ የወደብ ማስፋፊያዎቻቸው የወደብ ፖለቲካንና የቀጠናውን የበላይነት ለመያዝ ግብግብ ከሚገጥሙን ሀገራት ጋር የሚሰሩ ይትብብር እና የልማት እንዲሁም የመረጃና ደህንነት ስራዎችን ያጠቃልላል። እንዲሁም የሀገር ውስጥ ደረቅ ወደቦችንም ያካትታል።

በበርበራ፤ በቦሳሶ፤ በጅቡቲ፤ በፓርት ሱዳን ቢሮ ይኖራቸዋል፤ በደረቅ ወደቦች፤ በአማካይ ስፍራዎች በዋና ዋና ከተሞች፤ የመጋዘን አገልግሎችን የሚሰጡ መዋቅሮች ይዘረጉለታል። Djibouti ኬር፣ በርበራ ኬር፣ ቦሳሶ ኬር፣ ወዘተ

   ‘ETHIO RED SEE’ or ‘READ SEA INITIATIVE’

በአፋር ወረዳዎችና፤ ከኤርትራ ተዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የተለያዩ ስራዎችን የሚሰራ፤ አንዲሁም በቀይ ባህር ጠቅላላ ቀጠና ወስጥ የሚደረጉ አንቅስቃሴዎችን የሚከታተል ኢኒሼቲቭ።

                           ኬር ዘ ሪቨርስ ኢኒሼቲቭ
በጥቅሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሰራዎችን የሚያግዝ ይሆናል። ይሄ የሚለየው ሚኒስቴሩ የማይሰራቸወን ሌሎች የልማት ስራዎች የውሃ ሀብቶቻችንን በመንተራስ ይሰራል። የመረጃ ምነጭ በመሆንም ያገለግላል። በወንዞችና ተፋሰሶች፤ በሀይቆች፤ በሰውሰራሽ ግድቦችና በረግረጋማ ቦታዎች፤ በከርሰ ምድር ውሃ ሀብቶቻቸን ላይ የተለያዩ የልማት ፕጀክቶችን ቀርጾ የሚሰራ  ይሆናል። የአፍሪካ የውሀ ማማዎች፣ የኢትዮጵያ የዝናብ ማማዎች፤ የድንበር ተሻጋሪ ተፋሰሶችና፣ የከርሰምድርና የገጸ ምድር የውሀ ሀብቶቻችን፤ ካርታ እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ የከርሰምድር ውሀ ሀብቶቻቸን ላይ ምን እየተካሄደ ነው? የሚለውን ይከታተላል። ከእነዚህ ጉዳዮች ጋር ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ግንኙነቶች ያላቸው ሀገራት (በተፋሰስ ተጋሪነት፤ አስተዋጽኦ) ውስጥ ምን አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ ነው?  ከማን ጋር ምን ይሰራሉ?

በተለይም በአራቱ ንኡስ ተፋሰሶች ላይ፤ በእያንዳንዱ ወንዞች ከሰዎች ንክኪ ለማራቅ ይተጋል

  • የተደራጀ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ይሰራል
  • በወንዞቹ ላይ እየደረሱ ያሉ ጉዳቶችን ያሳውቃል ጥፋተኞቹን ያጋልጣል፤ እርምት ያስወስዳል
  • ተማሪዎች ለወንዞች ያላቸውን ግንዛቤ ያሳድጋል
  • ሚዲያ ላይ ወንዞችን በተመለከተ ሰፋፊ ስራዎችን ይሰራል

ፔትሮ ዶላሩን መከታተል

የገልፎቹን ዱካ መከታተል ለነገ የማይባል የቤት ስራ ነው። ኳታር፤ ቱርክና ኢራን፤ በሀገራችንና በጎረቤቶቻችን ውስጥ ምን እየሰሩ እንደሆነ በልዩነት መከታተል ያስፈልጋል። ከአውሮፓ ሀገራት (እንግሊዝ፤ ኖርዌይ፤ ስዊድን፤ ዴንማርክ) ከቻይናና ከአሜሪካ ድርጅቶችና መንግስታት ጋር ያላቸውን የእርስ በርስ ግንኙነት፤ እንደሀገር ያሉባቸውን ችግሮች፤ ጂኦፖለቲካዊ፤ ሀይማኖታዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ወዘተ በተደራጀ ሁናቴ መከታተል።

Riyal Politik The political economy of Gulf investments in the Horn of Africa Jos Meester Willem van den Berg Harry Verhoeven CRU Report April 2018

April 2018 © Netherlands Institute of International Relations ‘Clingendael’ ይሄንን ሰነድ ብዙዎች ያዘወትሩታል። እንደመነሻ መውሰዱ አይከፋም።

 አስመራ ፍቅሬ

ከአስመራ ጋር ያሉነን የግንኙነት መስመሮች የበለጠ ማጠናከርና ማስፋት።

ኢትዮ Sahel Alliance

ከፈረንሳይ ጋር ልንሰራቸወ የምንችላቸውን ቀጠናዊ ፕሮጀክቶች ያካትታል።  በላኩዊላው L’Aquila Food Security Initiative የእሷን አቅሞች በሚገባ መጠቀም። የጂ7 መሪነቷን በመጠቀም 

ከህንድ ጋር

ከጥራጥሬ ኢምፓርት ፍላጎት ጋር ከቻይና ጋር ያላትን ቁርሾ በቻይና ትልቁ ፕሮጀክት የሚደርስባት መገላለል ከአሜሪካ ጋር የሚኖራት ግንኙነት፤ ከገልፎቹ ጋር ያላት ጥብቅ ትስስር፤ እኛ ጋ ያላቸው የእርሻ መሬት የአግሮ ፕሮሰሲንግ መሰረተ ልማቶች ከገልፎቹ ጋር ያለውን ቁርኝት መመርመር፤ በጠቅላላው የኢንዶ ፓስፊክ ጉዳይ ከእኛ ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት መተንተን፤ አቅጣጫ ማስቀመጥ።