ሶች እንደ ውጫሌ፣ ግብጽ እንደ ጣሊያን?

ሶች እንደ ውጫሌ፣ ግብጽ እንደ ጣሊያን?

ደሴታማዋ የመዝናኛ ከተማ ሶች፣የኢትዮጵያንና የግብጽን መሪዎች አገናኝታለች፡፡ 45 ደቂቃ የፈጀው ውይይት ግብጽ ባለችው መንገድ ተጠናቅቋል፡፡እነሆ የስምንት ተከታታይ ዓመታት ጥያቄዋ መልስ አገኘ፡፡አንድ ጊዜ የዓለም ባንክ ያደራድረን፣ ሌላ ጊዜ አሜሪካ ታሸማግለን ሲል የነበረው የካይሮው መንግሥት ተሳክቶለታል፡፡ አሁን ሁለቱም በአንድ ጊዜ በአንድ ቀን በአንድ አዳራሽ ውስጥ ያለውን ሊፈጽሙ ቀን ቆርጠዋል፡፡ የአዲስ አበባ አቻው ይህ ይሆን ዘንድ ከስምንት ክረምቶች በኋላ በሶስተኛው ጠቅላይሚኒስትር ተስማምቷል፡፡‹‹ከማንም ጋር ብንደራደር ችግር የለውም›› ሲልም እሺታውን ገልፁዋል፡፡

(ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን አንጀት አርስ ነው አቦ! ከማንም ጋር ብንደራደር ችግር የለውም! ከማንም ጋር ብትደራደር አቁዋምህን ካወቅክ ምን ይመጣል?)

ለአፍሪቃ-ሩሲያ ጉባኤ ሶች የተገናኙት የግብጽና የኢትዮጵያ መሪዎች በሕዳሴው ግድብ ላይ የተቋረጠውን ውይይት/ድርድር ለማስቀጠል ተስማምተዋል፡፡

ነገርን ከስሩ

የሕዳሴ ግድብ እንደ አንድ ተራ ፕሮጀክት የሚወሰድ አይደለም፡፡ጉዳዩ ከኃይል ማመንጨትም በላይ ነው፡፡ይህ በተለይ በኢትዮጵያ ላይ ሁለት ነገር አምጥቷል፡፡አንደኛው ይህንን ግድብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ አድርጎ እንዲያስበው በማድረግ፣ ለብሔራዊ መግባባት ግብዓት ሆኖ ነበር (ነበር? እና ዐቢይ አበላሸው አይደል? ለብሔራዊ ኢ መግባባት አዋለው አይደል?) በዚህም ግብጽ ለዓመታት የተወሰኑ ልሂቃን የሚከራከሩለት ወንዝ ብቻ አድርጋ የምታስበውን አባይን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚቆረቆሩለት እንደሆነ እንድትገነዘብ አድርጓል፡፡ (ይሄ ነው ባለልከኝ ተራ ፕሮጀክት ላለመሆኑ ማሳያው? ‘የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው’ የሚለው ተረት ከህዳሴ ግድቡ በሁዋላ ነዋ የተተረተው? የግድቡ መሰረት ሲጣል ነዋ ለጂጂ ግጥምና ዜማውን የሰጣችሁዋት? አባይ አባይ የሚለው የቁጭትና የመብሰክሰክ መዝሙር መቼ እንደተሰራ አዋቂ ሰው ጠይቅ። ይሄንን መቆርቀር ግብጽ ዛሬ አይደለም የምታውቀው!)

ሁለተኛው በዲፕሎማሲ የሚገለጽ ነው፡፡ለዘመናት ‹ታሪካዊ መብቴ ነው› በምትለው የአባይ ወንዝ ላይ ለውይይት መቀመጥ የማትፈልገውንና ስለወንዙ በተለይ ከኢትዮጵያ ጋር መነጋገርን እንደ ግዴታ የማታየውን ግብጽን ለፍትሐዊ ድርድር ወደ ጠረጴዛው አምጥቷል፡፡ (ውሸት! ከግድቡ በፊት ሌላ ብዙ መወያያ መድረኮች ነበሩ! የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ የተመሰረተው በ1999 ነው። ዋና ግቡም የተፋሰሱን ሀገራት ለጋራና ለዘላቂ ጥቅም በአንድ ማዕድ ዙሪያ ማስቀመጥ ነው። ግብጾቹ ከህዳሴ ግድቡ መጀመር ይልቅ የኪንሻሳው ስምምነት (የትብብር ማዕቀፉ) የበለጠ ለሽንፈታቸው አስተዋጽኦ አድርጎአል። Unstable power structure, regional disagreement : Water politics along the Nile የሚለውን የ Nizar Manek ጽሁፍ አንብበው። ግድቡ የኪንሻሳው ስምምነት ውጤት ነው የሚሉም ብዙ አሉ። ካንተ ይሻሉኛል። የተፋሰሱ ሀገራት በኢኒሼቲቩ እንቅስቃሴ ውስጥ የግብጽን አይን አውጣነት በደንብ ለመታዘብ ጊዜ አግኝተዋል። ያ ነው ወደ ጋራ አቁዋም የመራቸው። ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ በ 2011፤ Negotiations for a Nile-Cooperative Framework Agreement ሲሉ ISS ላይ ያስነበቡትን ጽሁፍ አየት አድርገው። ከግድቡ በፊት ስለነበሩ ግብጽን ወደ ትበብር ውይይት ለማምጣት ስለሞከሩ ኢኒሼቲቮች ጥሩ ገንዛቤ ይሰጥሃል። ፌክ እና እኛን አግላይ ቢሆኑም፤ Hydromet (1967)፤ Undugu in (1983፤) እና Tecconile (1992) የተሰኙ የትብበር ማዕቀፎች ከተወሰኑ የተፋሰሱ ሀገራት ጋር . ልታካሂድ ሞክራ ነበር። ‘በትብብር’ መንፈስ ወደጠረጴዛ ዙሪያ በማምጣት ከ1999–2010 የዘለቀውንና በናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ አማካይነት የተካሄደው ድርድር ቀድሞ ይጠቀሳል። በአጭሩ የሲኤፍኤው ደርድር ልንለው አንችላለን። ነገርዬው፤ Cooperative Framework Agreement ይባላል። የትብብር ማእቀፍ ስምምነት ልንለው አንችላለን። የተፋሰሱን ሀገራት በ1997ቱ በተባበሩት መንግስታት የውሃ ህግ መሰረት የሚያስተዳድር ማእቀፍ ነው። የተፈጥሮ ሀብታቸውን በእኩል እና በምክንያታዊ መርሆች እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ ድንጋጌ ነው። የናይል ተፋሰስ ሀገራትም የዚህ አለማቀፋዊ ድንጋጌ ተገዥ ናቸው። በትብብርና፤ ጉልህ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ ሀብታቸውን የሚጠቀሙበተን መንገድ ለመዘርጋት የደከሙበት ጉዞ ነበር። ‘በተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሚኒስቴሮች ካውንስል አማካይነት ለ10 ዓመታት የተደረገው ውይይት በልዩነት ነበር የተጠናቀቀው። ልዩነቱን የፈጠረው በሰነዱ አንቀጽ 14(b) ላይ ያለው ሀሳብ በሱዳንና ግብጽ በኩል ተቀባይነት በማጣቱ ነው። ‘በተፋሰሱ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ ” የሚለውን፤ ግብጽና ሱዳን ‘ ‘…አሁን ባለው የውሃ ተጠቃሚነት እና መብት ላይ ጉዳት የማያደርስ’ በሚለው ይስተካከልልን ብለው ጥለው ወጡ። ግንቦት 2009 ኪንሻሳ ላይ በተካሄደው ጉባኤ፤ ሰባት ለአንድ በሆነ ድምጽ ማዕቀፉ ተቀባይነት አገኘ። ግብጽና ሱዳንን ለማካተት የተደረገው እልህ አስጨራሽ ሙከራም ሳይሳካ ቀረ።’ ይላል የዶክተሩ ሰነድ። ይህን ሰነድ ጥለው በመውጣታቸው ብቻ የአለማቀፉን የውሃ ህግ መሰረታዊ መርሆች ጥሰዋል። ‘አሁንም በአግላዮቹና ለእኛ ብቻ በሚሉት የቅኝ ግዛት ዉሎች እንቀጥል’ ማለታቸውን ያረጋግጥልናል። ይሄ እነሱን እንጂ እኛን የሚጎዳበት ምንም መንገድ የለም። ለዚያ ነው ግድቡን ሳናማክራቸው በራሳችን ውሳኔ ብቻ የጀመርነው። የእኛ ድርሻ ጉልህ ጉዳት አለማድረስና በፍትሃዊ አጠቃቃም ላይ መመርኮዝ ብቻ ነው። ለአለም አቀፉ ህግ ተገዢ ቢሆኑ ኖሮ፤ ዲዛይኑንም አብረን ልንሰራው በቻልን (ህጉ ይላል አላልኩም፤ ፍቅራቸው ይሉኝታ ካሲያዘን ብዬ ነው)። ግብጽ ህዳሴ ግድቡን ከመጀመር ያላገደችው አመክንዮአዊም ህጋዊም ሞራላዊም መሰረት ስሌላት ነው።

‹‹ግብጽ በናይል ወንዝ ዙሪያ ምንም ዓይነት የትብብር መንፈስ ለማሳየት ፈቃደኛ ሳትሆን ለረዥም ዘመናት የቆየች አገር ነበረች፡፡የናይል ወንዝ ድንበር ዘለል ባሕርይ ያለው መሆኑን እስከመካድ የሚደርስ አካሄድን ስትከተል የቆየችም አገር ነበረች፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ መጋቢት 23-2015 (እ.ኤ.አ) ለዓለም አቀፍ ሕግ ተገዢ በመሆን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ስምምነት መምጣቷ ታላቅ እርምጃ ነው›› ይላሉ፡፡ (ሰውዬው እንዲህ ብለው ጽፈው ከሆነ፤ በእውነቱ መጽሃፉን ባለማንበቤ ደስታ ይሰማኛል። ጸሃፊው የህወሓት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ናቸው። ይሄንን ሰነድ የሚያጋንኑበት ምክንያትም ከሰነዱ ቅሽምና ጋር የተያያዘ ነው።ቀደም ሲል እንደገለጽኩት በዚህ ስምምነት ሳቢያም አይደለም ግብጽ ወደ ድርድር የመጣችው። ሰነዱ ምን ያህል ቀሽም እንደሆነም ወረድ ብዬ አመለስበታለሁ)

በዚህ መልኩ ብሔራዊ ሕብረትንና የዲፕሎማሲ ድልን ያጎናፀፈው የሕዳሴው ግድብ አሁን እነዚህን ሁለት ውጤቶቹንም እያጣ ይመስላል፡፡ በአንድ በኩል ግድቡን በተመለከተ የአሁኑ መንግሥትና መገናኛብዙሃን ካላቸው አተያይ ይመነጫል፡፡

ግድቡን ‹50 በመቶም ያላለቀ፤የተዘረፈ፤ለፕሮፓጋንዳ ሥራ ተብሎ የተጮኸለት፤ሕዝቡም 10 በመቶ እንኳን ያላዋጣለት፤ የጥራት ችግርም ያለበት› እንደሆነ በተለይ ጠቅላይሚኒስትሩ ደጋግመው መናገራቸው ግድቡ ፈጥሮት የነበረውን ብሔራዊ የልማት መነቃቃትና መግባባት ውሃ ቸለሰበት፡፡የአገሪቱ መገናኛብዙሃንም እንደ ግብፃዊያን ግድቡን ማራከስና ስም ማጥፋት ቀጠሉ፡፡ (ይህቺን በመጀመሪያው ጽሁፍ ውስጥ ተችቻታለሁ። እዚህች ጋ አዲስ ነገር የተጨመረችው፤ ሚዲያዎቹ ግድቡን አራከሱ ስም አጠፉ የምትለው ነገር ናት። ውሸት! ሚዲያዎቹ ግድቡን አራክሰውም አያውቁም፤ አዎ ሜቴክን ወቅጠውታል። ሲያንሰው ነው። ሜቴክን ማራከስ ደግሞ ግድቡን ማዋደድ ነው። ካንተ የማያንስ የሀገር ፍቅር ያላቸው ጋዜጠኞች ብዙ አሉ። ፌዴራሊዝሙንም ካንተ በተሻለ ደረጃ የሚረዱ (ደራን አላውቃትም ሳይሉ መቀሌን ጽቡቅ የሚሉ) ብዙ የሰሜን ሸዋ ልጆችም ይኖራሉ። ለቫራይቲ ከፈለግካቸው ብዬ ነው። ሌላውን ግርግር ተይው ያየሰው! ‘ብሄራዊ ስሜቱ ላይ ውሃ ቸለሰበት’ ምናምን የምትለውም ተራ ሴንሴሽናላይዜሽን ናት። ብሄራዊ ስሜት ሲኖር እኮ ነው የሚቸልስበት፤ ህወሓት ቀድሞ ቸላልሶ የጨረሰውን ዐቢይ ከየት አምጥቶ ነው የሚቸልስበት?) ከዚያም ስለዚህ ግድብ የሚጽፍ፣የሚናገርና የሚከራከር ልሂቅ አነሰ፡፡ በአንድ ጊዜ 1300 ሜጋ ዋት እንዲቀንስ ሲደረግ እንኳ የሚቆጭ ጠፋ፡፡ (አልተቀነሰም! የተርባይን ቁጥር እንጂ ሀይል አልተቀነሰም። ያየሰው ለሚፈልገው ሀሳብ ማጠናከሪያ ነው ሀቁን ያዛበው። ወረድ ብዬ አብራራለሁ ) መገናኛ ብዙሃንና መሪዎቻችን ከግብፃዊያን በበለጠ ስለዚህ ግድብ አፍራሽ ዘመቻ ከፈቱ፡፡

እዚህ ጋር ግልጽ መደረግ ያለበት ነገር አለ፡፡

(በነገራችን ላይ፤ በ2014 ማርች ላይ፤ አስር አባላት ያሉትና በሶሰቱ ሀገራት አማካይነት የተደራጀው የሶስትዮሽ የቴክኒክ ኮሚቴ ባወጣው ሪፖርት ዙሪያ ከባድ ወዝግብ ነበር። ሪፖርቱ ላይ ኢትዮጵያም ማስተካከል ያሉባትን ነገሮች ተቀብላ ስራዋን ቀጥላለች። ግድቡ መቆም አለበት እስከሚለው የከከረረ ውዝግብና ፤ ተሰርቆ ቀድሞ ስለወጣው ሪፖርትም በሀገር ደረጃ መግለጫ የተሰጠበት በጭቅጭቅ የተሞላ አመት ነበር። ሰውዬው የመጡት መስከረም 21 2014 ነበር። ጎብኝተው ሲመለሱ ለአልሞኒተር የሰጡትን ቃለምልልስ የተወሰነውን ቃል በቃል ማንበብ ነው። አንዳችም ቦታ ስለ ግድቡ ጥራት ጠብቆ መገንባት የተናገሩት ነገር የለም። እንዲያውም በተቃራኒው ነው ያወሩት። በግንባታው ፍጥነት ገን ረክቻለሁ ብለዋል። እንግዲህ በእሳቸው ዘንድ እርካታ ከፈጠረ እንደተንታኝ መጠርጠር ነበር አንጂ፤ ለራስ ፍጆታ ግብጻዊን ማስዋሸት ትንሽ አስቂኝ ነው። የእስከዛሬውንም ውሸታቸውን አልቻልነው። ስለቴክንክ ችግሩ ነው ያግድቡን መጎብኘቴ በግድቡ መስማማቴን አያመላክትም። የሚል ቃላቸውንም ሰጥተዋል። የውሃ ድርሻችን እንደማይነካ ማረጋገጫ አግኝቼ ነው የተመለስኩት ሁላ ብለዋል። ያው ከዜናው መካከል የቀነጨብኩት። ሙሉውን ዜና ለማንበብ ደግሞ፤ Egyptian visit to Ethiopian dam raises hopes for resolution በሚል ርእስ EECCA ላይ ያገኙታል። 15 October 2014 ነው የወጣው።

 In an interview with Al-Monitor, Moghazy said, “We have assurances from the Ethiopian side that there will be no prejudice to the amount of water flowing to Egypt from the Ethiopian plateau through the eastern Nile. My visit with Ethiopia’s water minister is strong evidence that there are good intentions.”

After Moghazy returned from Addis Ababa, he said the visit did not and would not necessarily mean that Egypt has agreed to the building of the dam based on the current specifications. This visit proved controversial in some decision-making circles, with a fear that the visit would be misinterpreted as Egypt’s implicit approval for the construction of the dam without conditions.

Moghazy said, “We have not yet agreed upon the dam’s stated specifications and our final decision will depend on the results of studies to be conducted by an international consultancy bureau, in collaboration with the national committee of experts.”

Moghazy affirmed that, “My visit to the dam’s site was not political, but rather technical.” But the minister expressed satisfaction at the pace of construction. “I have found that construction works at the dam’s site are preliminary, ranging between 15-20%,” he said.

 “Technically, the storage of water and generation of electricity are not possible in the first stage, as Ethiopia says, in September 2015.” He also said, “The topographic nature in the dam’s area does not allow the water stored behind the dam to be exploited in agriculture.”

 Nevertheless, in an interview with Al-Monitor, Mahmoud Abu Zeid, head of the Arab Water Council and expert in water management, said it is not technically feasible to judge the dam’s details from one quick visit by a minister.

  “It would have been better to put off the minister's visit to Ethiopia and the dam’s site until the national committee completed its work and until we made sure that Ethiopia will be committed to the results of the studies on the dam’s impact on Egypt’s water interests,” he said.

“የእኛ መሪዎች ግን ከግብፃዊያንም በላይ ግድቡን ስም ማጥፋት የጀመሩት ሥልጣኑን በያዙት ማግስት ነበር፡፡ በግድቡ ላይ ገንዘብ አባክኗል ተብሎ ዶክመንተሪ የተሠራበት ሜቴክ ነው፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ በዚህ ጥፋት የተከሰሰ አንድም የኮርፖሬሽኑ አመራር አለመኖሩን ስንመለከት፣ይህ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ኩራት የሆነ ግድብ ስሙ እንዲጠፋ የተደረገው በየትኛው አገር ትዕዛዝ ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ (አለመከሰሳቸው ብቻውን ነጻ ስለመሆናቸው ማስረጃ ሆኖታል ማለት ነው? በግብጽ ትዕዛዝ ሜቴክ ለመመታቱም ማስረጃ ሆኖታል የሰዎቹ አለመከሰስ፤ ያው የእነ ክንፈን አናካትተውም፤ ከመታሰሩ በፊት ነው የጻፈው። የሜቴክ ባለስልጣናት አብዛኞቹ ያልተቀፈደዱትን ምክንያት ሀገር ያወቀዋል። ቆይቶም የተፈረደባቸወ አሉ!)

ሁለተኛውና ኢትዮጵያ በዚህ ግድብ ያሳካችው ዲፕሎማሲያዊ ድልም፣ አሁን እየተቀለበሰ ነው፡፡ ግብጽን ከታሪካዊ ባለቤትነት ወደጋራ ልማት ስሜት ያመጣው ይህ ፕሮጀክት፣ለውይይትም አስቀምጧታል፡፡

በአንድ በኩል፣በሌሎች ግድች ላይ የነበረው (ለምሳሌ ጊቤ) ዓለማቀፋዊ መንጫጫት በሕዳሴ ግድብ ላይ አልነበረም፡፡ ከግብጽ በስተቀር ይህንን ግድብ የተቃወመ፣የተቸ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ አለው ያለ አገር፣ድርጅት፣አለያም መሪ የለም፡፡ (በ2017 አረብ ሊግ በከረረ ተቃውሞ አውግዞታል፤ ዐቢይ ያኔ ስልጣን ላይ አልነበረም። Arab League “extreme concern” over Ethiopia’s Nile dam 27 November 2017 ላይ የወጣ ነው። ኤርትራም ዛሬ ነው የደገፈችው፤ ያኔ ሀገር አልነበረችም አይደል? ድሮስ ኤርትራና አረብ ሊግ ግድቡን ሊደግፉ ነበር ወይ? የሚለውን ጥያቄ፤ በሌላ ጥያቄ እመልሰዋለሁ፤ ድሮስ ያየሰው እና ህወሓት የዐቢይ አህመድን መንግሰት ሊደግፉ ነበር? የተቃወመ ድርጅት የለም የሚለውን እንተወው።)

ይህም ግብጽን ብቻዋን ያስቀረና ኢትዮጵያም ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ሥራ መሥራቷን ያሳያል፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ግብጽ ሳትወድ ወደ ድርድር እንድትመጣ አድርጓል፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታትም ሄድ መጣ እያለች ስትደራደር ከረመች፡፡

ግድቡ ቆሞ እንነጋገር ብትልም፣ በኢትዮጵያ በኩል አወንታዊ ምላሽ አላገኘችም፡፡ የግድቡ ቁመት ይነስ፣የማመንጨት አቅሙም ይቀንስ፤ የሚይዘው ውሃ አነስተኛ ይሁን፤ ተርባይኖች ይቀነሱ ወዘተ የሚል ጥያቄ ስታቀርብም፣ከኢትዮጵያ በኩል በዚህ ላይ ድርድር የለኝም ስትባል ከረመች፡፡

በመጨረሻም መጋቢት 23፣2015 (እ.ኤ.አ) ኢትዮጵያ ጥቅሟን ያስከበረችበትን ድንቅ ስምምነት ተፈራረመች፡፡ (ምንም የተከበረ ጥቅም የለም። የተደፈረ እንጂ። የተከበራችሁ አንባቢዎች፤ ያየሰውና አለቆቹ በ2015 ከግብጽና ከሱዳን ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ (Declarations of Princeples) አለ። እሱን ነው፤ ድንቅ አያለ የሚያሞካሸው። አለቆቹም ይኩራሩበታል። ግብጽን ያንበረከክንበት ነው ይሉታል። አዋቂዎች ገን ይስቃሉ። ምክንያቱም ሰነዱ በብዙ ነገሩ የግብጽን ወገብ ያጠና ነው። በዚህ ሰነድ ውስጥ ዛሬ ዐቢይ አህመድ አደረጋቸው እየተባሉ ለወቀሳ መዋያ የተደረጉ ነጥቦች በሙሉ ተካትተውበታል።

Declaration of Principles on the Grand Ethiopian Renaissance Dam: Some Issues of Concern  የሚለው የደረጄ መኮንን ጥናት የእነያየሰውን ድንቅ ስምምነት በጥልቀት ይተቸዋል። እንግዲህ የኪንሻሳውን የትብብር ማእቀፍ አንቀበልም ካሉት ሀገራት ጋር ነው፤ በ2015 ሌላ ሰነድ የተፈራረምነው። ዋናው ችግር ከዚህ ይነሳል። ለአለም አቀፍ ስምምነት ተገዥ አለመሆናቸውን የCFAውን ሰነድ ባለመፈረም ካረጋገጡልን አካላት ጋር ምን አይነት የትብብር ውል ነው የምናስረው? የሚለው ጥናቱ፤ 2015ቱን ስምምነት የአለም አቀፍ የውሃ ድንጋጌዎችንና የኢትዮጰያን ጥቅም አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ያብራራል። ‘የግድቡን ውሃ ለሀይል ማመንጫ ብቻ ነው የምንጠቀምበት’ ብለን በመፈረም፤ የግብጽን የቅኝ ግዛት ኮታ በእጅ አዙር እንደማንነካ ማስተማመኛ ሰጥተናል። ይሄንን አለማቀፋዊ ህግም የማይደግፈውና፤ ዛሬም ቦይነታችንን በፊርማ ያረጋገጥንበት፤ ዛሬም በተፈጥሮ ሀብታችን ለመጠቀም የሌሎች ፈቃድና ይሁንታ እንደሚያስፈልገን የተስማማንበት ሰነድ ነው። ይሄም ብቻ አይደለም በሲኤፍኤው ላይ ያልተስማሙባቸውን የቃላት ጉዳዮችም ‘በአሻሚ መልኩ ክፍት አድርገው እንዲተዋቸው እድል ከፍቶላቸዋል። የአቶ ደረጀ ጥናት፤ ሌሎች የስምምነቱን ከባባድ ድክመቶችም ቃኝዋቸዋል። ተመልከተው!

ይልቅ እኔ ሰነዱን ሳነብበው፤ የታዩኝን አንድ ሁለት ነጥቦች ልጨምርና ያየሰው አንደሚለው ‘ድንቅ’ አለመሆኑን አመላክቼ ልለፍ። በሰነዱ አንቀጽ 4 ላይ የግድቡን ውሃ አሞላልና ፤ አጠቃቀም በተመለከተም መጀመሪያ ሶሰቱ ሀገራት መስማማት እንዳለባቸው በግልጽ ተቀምጧል። ወረድ ይልና ደግሞ፤ ‘ከሚመረተው ሀይል ግብጽና ሱዳን ቅድሚያ  የመግዛት መብት ይሰጣቸዋል’ ይላል፤ በቶሽካና በሜሮኢ መስኖዎች ከሚያመርቱት ሽንኩርት አቅምሰውን ከማያውቁ ና ባስ ሲልም የሽንኩርት ፖለቲካ ሲጫወቱብን ለኖሩ ሀገራት እንዲህ አይነት ችሮታ የሆነ አዝናኝ ነገር አለው።

የመጨረሻዋን ትዝብቴን ልጨምር፤ በአጋጣሚ ይሄንን ስምምነት ከሁለት ምንጮች ወስጄ ነበር ያነበብኩት።  ከHorn affairs ላይOfficial Text: Egypt, Ethiopia, Sudan – Declaration of Principles  የሚለውንና ከAhram Online ላይ ደግሞ  Full text of 'Declaration of Principles' signed by Egypt, Sudan and Ethiopia በሚል ርእስ አግኝቼ ነው። በሁለቱ ሰነዶች ላይ አንዲት አስገራሚ ልዩነት አጋጥማኛለች። ሙሉ በሙሉ አሰፍራታለሁ፤ ክፍል 4(b) እና 5(b) ላይ ያገኙታል።

  1. Agree on guidelines and rules for the annual operation of GERD, which the owner of the dam may adjust from time to time.
  2. An agreement on the guidelines and annual operation policies of the Renaissance Dam, which the owners can adjust from time to time

ባለቤት እና ባለቤቶች የሚል ወግ እንዳይመጣ ስጉልኝ ብቻ!! የያየሰውን ርእስም ከ’ሶች እንደውጫሌ’ ወደ ‘ካርቱም እንደ ውጫሌ’ ማስተካከያ እንዳያደርግ……..በአርግጥ ጋዜጣው በፈለገው መነገድ ተርጉሞት ሊሆን አንደሚችል ይገመታል።

ቢሆንም…

ይሁን እንጂ ግብጽ በዚህ የምታቆም አልሆነችም፡፡ ሶስተኛ ወገን ያደራድረን ብላ የዓለም ባንክን አማራጭ አቀረበች፡፡ ኢትዮጵያ በአንፃሩ እራሳችን መነጋገር እንችላለን ብላ ተቃወመች፡፡

አድካሚው ድርድር ከተካሄደ ከዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ የአስተዳደር ለውጥ ተደረገ፡፡ የተቀየረው መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ግድቡን በተመለከተ ከላይ የተዘረዘረውን ጉዳት በኢትዮጵያ ላይ አድርሶ፣ (የተለወጠው መንግስት ግድቡ ላይ ምንም ያደረሰው ጉዳት እንደሌለ አይተናል።) የግብጽን ጥያቄዎች አንድ በአንድ መመለስ ጀመረ፡፡ በአንድ ጊዜ ሶስት ተርባይኖች ቀነሰ፡፡ (ምንም የተመለሰ ጥያቄ እንደሌለም አይተናል) የግድቡን የማመንጨት አቅም በ1300 ሜጋ ዋት እንዲቀንስ አደረገ፡፡ በዚህም ከ6450 ወደ 5150 ሜጋ ዋት ወረደ፡፡ (ይህንን የተናገሩት የውሃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ናቸው)፡፡ (በዚህ የያየሰው መረጃ ውስጥ አስገራሚ ስህተትና ጥፋት እንዲሁም ውሸት ተካትቷል።

ሲጀመር 6450 የሚለው ወደ 6350ሜጋ ዋት መስተካከል ይኖርበታል። ዶክተሩ ከተናገሩት ውስጥ ለራስ በሚመች መልኩ ቆርጦ በማውጣት የተሰራ የመረጃ ሸፍጥ አለ። ሰውዬው እንዲህ ነው ያሉት፤  ግድቡ ቀደም ሲል ተደረገለት በተባለው የዲዛይን ማሻሻያ 6 350 ሜጋ ዋት ኃይልን እንደሚያመነጭ ታስቦ ነበር፡፡ ይህ ኃይል የሚመነጨውም በወቅቱ ይተከላሉ በተባሉ አስራ ስድስት ተርባይኖች በኩል ነው፡፡ ከአስራ ስድስቱ ተርባይኖች መካከል አስራ አራቱ እያንዳንዳቸው 4 መቶ ሜጋ ዋት ሁለቱ ደግሞ እያንዳንዳቸው 3 መቶ 75 ሜጋ ዋት አመንጭተው ነው በድምሩ 6 350 ሜጋ ዋት ኃይልን የሚያስገኙት፡፡ ተርባይኖቹ በሰዓት 15 692 ጊጋ ዋት ኃይልንም ያመነጫሉ፡፡ ሆኖም ይህን ሀይል ለማግኘት ተርባይኖቹ ከዓመቱ ቀናት ውስጥ 28 ነጥብ 2 በመቶ ያህሉን ወይም በዓመት ውስጥ 2 471 ሰዓታትን አለበለዚያም በዓመት ውስጥ 103 ቀናትን መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የተርባይኖቹ ቁጥር ወደ 13 ዝቅ ሲል ግድቡ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫል ፡፡ ይህን ለማግኘትም 11 ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 4 መቶ ሜጋ ዋት ቀሪዎቹ ሁለት ተርባይኖች ደግሞ እያንዳንዳቸው 3 መቶ 75 ሜጋ ዋት ኃይልን ማመንጨት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚመነጨው የኃይል መጠን ግን ቀደም ሲል ታቅዶ ከነበረው (6 350) 1 2 መቶ ሜጋ ዋት ያነሰ ነው፡፡ይህ የተርባይኖቹ የማመንጨት ዐቅም እና የስራ ሰዓት ባለበት ሆኖ ነው፡፡  ሆኖም የተርባይኖቹን የስራ ሰዓት ከዓመቱ ቀናት ውስጥ 34 ነጥብ 8 በመቶ ወይም በዓመት ውስጥ 3 66 ሰዓት አለበለዚያም በዓመት ውስጥ 128 ቀናት በማድረግ ተርባይኖቹ በሰዓት እንዲያመነጩ ታስቦ የነበረውን 15 692 ጊጋ ዋት ኢነርጂን ማግኘት ይቻላል። የተርባይኖች ቁጥር ቢቀንስም ግድቡ ተመሳሳይ የሀይል መጠንን ያመነጫልበዚህም እስከ 210 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለመቆጠብ የሚያስችል  ነው።


Image

ከላይ የሚታየው ፎቶ በማብራሪያው ወቅት ከቀረበው ሰነድ ላይ የተወሰደ ነው። ፎቶውንም ሆነ ንግግሩን (ለራሳችን በሚመች መልኩ የቀናነስነው አለ) የወሰድነው፤ አል ዐይን ከተባለው የመረጃ ምንጭ ነው።

ሰውዬው እንዲህ በቀላሉና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ያብራሩትን ነው፤ ያየሰው ተንታኙ በራሱ መንገድ ተርጉሞ ያቀረበው።)

የሶስተኛ ወገን አደራዳሪነትን ተቀበለ፡፡ ግብጽ የውሃ ሙሌቱ በ7 ዓመት ይሁንልኝ ስትልም ተስማማ፡፡ (በነገርህ ላይ፤ የ2015ቱ ስምምነት፤ እርስ በርስ ካልተስማሙ በየሀገራቸው መሪዎች ምክር ሀሳብና አደራዳሪነት ይመራሉ ይላል። ይሄንን ተከትለው ሁለቱ መሪዎች ገብተውበት ይሆናል። ይሄም ለሶስተኛ ወገን አደራዳሪነት መግባት ዋናው በር ከፋች ተደርጎ መወሰድ አይችልምን?። ያን ያህል አናሊቲካል እይታ አይፈልግም። ግብጽ በሰባት አመት ብላ የምታወቀው መቼ ይሆን? )

የግድቡን የቁመት መጠንም አስቀድሞ ከ80 በመቶ በላይ ስለተገነባ ነው እንጂ፣እዚህም ጋር የግብጽ ጥያቄ ሊመለስ የሚችልበት እድል አይኖርም ብሎ መናገር አይቻልም፡፡ አሁን የቀረበው ጥያቄ ‹አስዋን በተራበ ቁጥር ከሕዳሴ ግድብ ውሃ ልቀቁለት› የሚልና መሠል ሉዓላዊነትን የሚጋፋ ዕቅዷ ነው፡፡ በሩሲያ ሶች የነበረው፣የዐቢይ አሕመድና የኤል ሲሲ ውይይት ይህንንም ፈር አስይዞት ሊሆን ይችላል፡፡

እስካሁን ባለው ሁኔታ ግን ሌላው ቀርቶ ግብጽ ከኢንቴቤው ስምምነትም ሆነ ከናይል ቤዚን ኢኒሽዬቲቭ የወጣችባቸውን ስምምነቶች እኛ በጓሮ በር ተቀብለናል፡፡ (ለምን ከናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ እንደወጣች ተናግሬያለሁ። ሱዳንም አብራ መውጣቱዋን እንዳትረሱ። በጓሮ በር ማን እንደተቀበለም በመረጃ አስነብቤያለሁ። ያየሰው ማለት ይህቺ ናት። ውሸታም፤ ከመረጃ ሩቅ! ከእውቀት ጽዱ!)

የሶች ስምምነት

ግብጽ የሕዳሴ ግድብን ዓለማቀፋዊ ገጽታ በማላበስ እንዴት እየሠራች እንደሆነ ከወር በፊት የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ መነሻ በማድረግ ከአሁን በፊት በዚሁ መጽሔት ላይ በስፋት አንብበናል፡፡ በወቅቱ ኤል ሲሲ በጉባኤው ላይ ከተናገሩ በኋላ አሜሪካ እንድታደራድራቸው በይፋ ጠይቀው ነበር፡፡

ትንሽ ቆይታም እኔ ላደራድራችሁ አለች፡፡ግብጽም አስቀድማ የሠራችው ሥራ ስለነበር ከብርሃን ፈጥና ‹አዎ!አደራድሪን› አለች፡፡ በዚህ መሀል የጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ የኖቤል ሎሬትነት ይፋ ሲደረግ ኤል ሲሲ ተሸቀዳድመው ደውለው ‹እንኳን ደስ አለህ› አሉ፡፡የግብፁ ፕሬዚዳንት የዲፕሎማሲ ረቂቅነት የሚመጣው እዚህ ጋር ነው፡፡‹የሠላም ሎሬት ሆነህማ በግድብ ምክንያት የምጠይቅህን እምቢ ብትል እንደ ሠላም ጠልና ጦረኛ ትቆጠራለህ› የምትል ይዘት ያላት ‹የደስታ መግለጫ› ነች፡፡ከዚያም ሩሲያ ለመገናኘት እንደተስማሙ ተዘገበ፡፡ ከሳምንት በኋላ ጠቅላይሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ ቀርበው፣‹ፕሬዚዳንት ሲሲን አውርቻቸዋለሁ፤በቅርቡም እንገናኛለን፤እንወያይበታለን›› አሉ፡፡እንዳሉትም በማግስቱ በሩሲያ ሶች ተገናኙ፡፡

አሁን ጥያቄው በሩሲያ ተገናኝተው ምን ተስማሙ የሚለው ነው፡፡ተከትለዋቸው ለሄዱት የመንግሥት መገናኛብዙሃን ጠቅላይሚኒስትሩ ሲናገሩ ‹ግብፃዊያን በኢትዮጵያ መጥተው ችግኝ እንዲተክሉ ያቀረብሁትን ጥያቄ ፕሬዚዳንቱ በአወንታ ተቀበሉኝ› በማለት ነው፡፡ይህ መልካም ነው፡፡

ሶስተኛ ወገን ያደራድረን የሚለውን የግብጽን የዘወትር ጥያቄ እንዴት እንዳስተናገዱት ሲጠየቁ ደግሞ ‹‹ግብጽና ኢትዮጵያ በጣም ትላለቅ አገራት ስለሆኑ በእነርሱ መካከል የሚፈጠር ችግር አፍሪቃ ላይ አደጋ ያመጣል የሚል ፍራቻ ስላላቸው፣ራሺያን ጨምሮ በርካታ አገራት ጣልቃ መግባት ማወያየት ይፈልጋሉ፡፡ ፖለቲካዊ ውይይቱን ከማንም ጋር ብናደርገው ችግር የለውም››አሉ፡፡

እዚህ ጋር አስገራሚ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ጠቅላይሚኒስትሩ  ‹‹ከማንም ጋር ብናደርገው ችግር የለውም› ያሉት በውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ መሪነት እየተደራደረ ያለው የኢትዮጵያን ቡድን የሶስተኛ ወገን አደራዳሪነት አስፈላጊ እንዳልሆነና ኢትዮጵያም እንደማትቀበለው በይፋ ከገለፀ ከአንድ ሳምንት በኋላ መሆኑ ነው፡፡ ከዚያ ቀጥሎ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን አሜሪካ ልታደራድር መወሰኗንና የዓለም ባንክም በአደራዳሪነት እንደሚሰየም ዘገቡ፡፡

በተለይ አሜሪካና የዓለም ባንክ ከግብጽ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው ናቸው፡፡ የካይሮው መንግሥት በየዓመቱ ከዋሽንግተን እስከ ስድስት ቢሊዮን ዶላር የሚሠጠው (ለጦሩ) እና በመንግሥታት መቀያየር ውስጥ ያልዋዠቀ ወዳጅነት ያለው ነው።
 
ግብጽ ለዓመታት በሠራችው ሥራ የግድቡ ፋይናንስ ከውጭ እንዳይገኝ አድርጋለች፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ ኃላፊነት ይዛ ተነስታለች፡፡ከሳምንት በፊት Forum for Social Studies ባዘጋጀው መድረክ ላይ ሕሩይ አማኒኤል (ጡረተኛ አምባሳደር)
 
ጠቅላይሚኒስትሩ በእነዚህ አማካኝነት ለመደራደር ነው እንግዲህ፣ካቢኔያቸውንም ሆነ በጉዳዩ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ሳያማክሩ ተስማምተው የመጡት፡፡ይህም ለዘመናት በግብጽ በኩል ሲጠየቅ የነበረ በመሆኑ ለካይሮ ትልቅ ድል ነው፡፡ኢትዮጵያን ግን ዋጋ የሚያስከፍላት በብዙ መልኩ ነው፡፡በአንድ በኩል፣ ‹ሕዳሴ ግድብን በጋራ እናስተዳድረው› የሚለው የግብጽ ሉዓላዊነትን የሚጋፋ እቅድ፣አደራዳሪ ትሆናለች በተባለችው በአሜሪካ በኩል አስቀድሞ አቋም ተይዞበታል፡፡
 

ከሳምንታት በፊት የወጣው የዋይታውስ መግለጫ ‹በግድቡ አስተዳደር ላይ ተስማሙ› (ከላይ ገልጬዋለሁ) በማለት ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቷ ውስጥ የሚሠራን ግድብ ግብፃዊያን መጥተው እንዲያስተዳድሩ (Operation) ትፈቅድ ዘንድ አዟል/ጠይቋል፡፡ይህ በኢትዮጵያ ባለሙያች በኩል ውድቅ ቢደረግም፣

ከሕዳሴ ግድብ ጅማሮ ማግስት የኢትዮጵያን አቋም ደግፋ የፀናችው ሱዳን፣በእያንዳንዱ ውሳኔና እንቅስቃሴ ላይ የጋራ የአቋም ስትይዝ ከርማለች፡፡ (ሱዳን በየጊዜው እንደምትቀያየር በመጀመሪያው ትችቴ ውስጥ ጠቅሻለሁ) የሶስተኛ ወገን አደራዳሪን አላስፈላጊነትም ውድቅ ያደረገችው ከኢትዮጵያ ጋር ሆና ነው፡፡ (አድርጋ አታውቅም)

አሁን ግን የኢትዮጵያ ጠቅላይሚኒስትር ሱዳንን ትተው ምዕራባዊያን ያቀረቡላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ተመልሰዋል፡፡ ይህ በቀጥታ ሱዳንን ቅር የሚያሰኝ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃን ችግር በአፍሪቃዊያን እንፈታለን ከሚለው የአፍሪቃ ሕብረት አጀንዳም ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው፡፡ ጠቅላይሚኒስትሩ ‹ፖለቲካዊ ውይይቱን ከማንም ጋር ብናደርገው ችግር የለውም› ያሉት ነገር ትልቅ ስህተት የሚሆነውም ለዚህ ነው፡፡

በአንድ በኩል ግብጽ በወንዙ ላይ ከዚህ በኋላ ሌላ ምንም ዓይነት የልማት ሥራ እንዳይሠራ የሚያደርግ ፕሮፖዛል ይዛ ልትቀርብ ትችላለች፤ እስካሁን ያላነሳቻቸውን አጀንዳዎችም ልትመዝ ትችላለች፡፡ (አቤት ጉድ! በ2015 ላይ ከመብራት ሌላ ምንም አልሰራበት ብሎ በድንቁ ሰነድ ያሰፈረውን ረስቶት ነው። ከዚህ ውጪ ዐቢይን ምን አይነት የልማት ስራ እንዳትሰራ ልትከለክለው ይሆን? እንዳትዋኙበት እንዳትለን ይሆን )

ለዚህ ደግሞ ባንኩና አሜሪካ ያግዟት ዘንድ ለዓመታት ስትሰራ ቆይታለች፡፡እናም ይህ ድርድር በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምኑችን ቢሮ በመጪው ረቡዕ ይካሄዳል፡፡ የማይመጣጠኑ ኃይሎች የሚያደርጉት ድርድር መሆኑ ውጤቱን ከወዲሁ ተገማች ያደርገዋል፡፡

ከሶች በፊት፣በፓርላማው ፊት

ጠቅላይሚኒስትሩ ወደ ሩሲያ ተጉዘው ኤል ሲሲን ከማግኘታቸው በፊት፣በፓርላማ ቆይታ ነበራቸው፡፡ስለ ግድቡ ተጠይቀው የመለሱት መልስ፣በዲፕሎማሲያዊ ስህተቶች የተሞላ ነበር፡፡‹‹ያው ኢትዮጵያውያን በውስጥም በውጭም በታላቅ ትህትና እንድትገነዘቡ የምጠይቀው፣ 1/4ኘኛው የአገሪቱ ሕዝብ ድሃ ነው፡፡እና ወጣት ነው፡፡ስለዚህ ከአፍሪቃ ጋር እንዋጋ ከተባለ ብዙ ሚሊዮን ማሰለፍ ይቻላል ማለት ነው፡፡አንዳንዱ ሚሳኤል መተኮስ የሚችል ከሆነ አንዳንዱ ደግሞ ቦንብ ታጥቆ፣ለኢትዮጵያ (ለባንዲራ) ከሆነ፣…ካይሮ ላይ ያፈነዳል ማለት ነው፡፡ግን በማፈንዳት በጦርነት ጥቅም አይገኝም››፡፡

እንዲህ ያለውን ነገር በ21ኛው ክፍለዘመን የአገር መሪ ሲናገረው ያስደነግጣል፡፡


 

በአንድ በኩል 1/4ኛው ድሃ ስለሆነ ይዋጋል ማለት ‹ኮሎኔልነት› ማዕረግ ላይ ከደረሰ መሪ የማይጠበቅና ውትድርና የድሃ ሥራ አድርጎ ማየቱ ትልቅ ችግር ነው፡፡ (ሃሃሃ! ማቀሳሰር ይልሃል እንዲህ ነው! ያየሰው እንዲህ አይነቱን ተራ ማቃጠር ትተህ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስህተት በግልጽ ነግረህ ብታልፍ ደስ ይለኝ ነበር። እኔ ልንገርልህ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ነግግር አላስፈላጊ ነበር!!!!)

ሁለተኛው ግን ‹ካይሮ ላይ ቦንብ እናፈነዳለን› ማለት ፍፁም ኢ-ዲፕሎማሲያዊና አቅምን አለማወቅ ነው፡፡ጉዳዩ ወዲያው ነበር ያንጫጫው፡፡አሶሽዬትድ ፕሬሰ ‹የኖቤል ተሸላሚው ጠቅላይሚኒስትር ግብጽን አስጠነቀቁ› ብሎ ዘገበው፡፡አልጄዚራ ‹የሠላም ሎሬቱ ከግብጽ ጋር እስከ ጦርነት ከደረሱ ሚሊዮኖችን አዘምታለሁ አሉ›› አለ፡፡ የካይሮ መገናኛ ብዙሃን ይህንን የዘገቡት በሰበር ዜናነት ነው፡፡ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚያኑ ዕለት ማታ ባወጣው መግለጫ ‹ደንግጫለሁ› አለ፡፡

‹“የግብጽ አረባዊ ሪፐብሊክ የጠቅላይሚኒስትር ዐቢይን የፓርላማ ንግግር ስትሰማ ደንግጣለች፤ጠቅላይሚኒስትሩ ያሰሙት ንገግር ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን በሕዳሴ ግድብ አጀንዳዎች ላይ አሉታዊ ግብዓት የሚሆን ነው››ነበር ያለው-የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡በርግጥም ይህ በድርድሩ ላይ የበዛ አሉታዊ ሚና አለው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ‹ግን ጦርነት አይጠቅምም› ያሉት ነገር አያዎ ነው፡፡ የጦርነት አላስፈላጊነት ገና ድሮ የታመነበትና ተትትኖ የሚታወቅ ነው፡፡ወሳኙ ነጥብ ግጭት ቀስቃሽ ንግግርን መተው ነው፡፡ለዚያም ነው፣ግብጽና መገናኛብዙሃኖቿ ስለ ማፈንዳትና መዋጋት ብቻ የተናገሯትን ያራገቧት፡፡


 

ያየሰውን ስናጠቃልለው

በሁለቱ ጽሁፎቹ ውስጥ፤ መአት ትዝብቶችን መውሰድ ይቻላል። ውሸት፤ ማስመሰል፤ ስም ማጥፋት፤ ማለባበስ፤ የራስን ስህተት መሸፈን፤ ማወናበድ፤ የእውቅትና የመረጃ እጥረት፤ ጭፍን ጥላቻ ወዘተ ……….በዚህ ሁኔታ ነው ያየሰው በርካታ ጽሁፎችን ያስነበበን። ሌሎቹንም አይቶ መፍረድ ይቻላል። ተመሳሳይ ናቸው።  በተለይም ዛሬ ላይ ሆኖ ለሚያየው ሰው ከትዝብት በላይ ለሆነ ምላሽ ይዳረጋል። የእነ ህወሓትን መሰል እንቅስቃሴ ስንመለከትም እርስ በርሱ እየተናበበ ተራ ጥላቻውን የሚዘራ የሚዲያ ማፍያ እንዳለ እንረዳለን። ብዙ አሉ! ግድቡን ለተመሳሳይ አላማቸው የሚጠቀሙበት። በርካታ የፕሮጀክቱን ሰራተኞች፤ የተደራዳሪዎቻችንን ሞራልና ሰብእና የሚነኩዐ የለውጡን መንፈስ ለመጎዳት የታቀዱ  አደገኛ የፕሮፓጋንዳ ስራዎች ተሰርተዋል፤ እየተሰሩም ነው።

ከሁሉም በላይ አስገራሚው ግን ይሄንን አይነት ስህተት ሲፈጸም ምላሽ የሚሰጥ አካል መጥፋቱ ነው። አንድ ሁለት ጊዜ በመጽሄቱ ላይ ምላሽ ለመስጠት አንደተሞከረ አይቻለሁ። እነሱን አመሰግናለሁ። ጉዳዩ ግን ከዚህም የባሰ ምላሽ እንደሚያስፈልገው መማሪያው ጊዜ አሁን ነው።

ይሄንን ውድ እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክት ከሚሰነዘርበት የሚዲያ ጥቃት የሚከላከል ቡድን ማደራጀት፤ በፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ስር ማዋቀር ይቻላል። ለብቻው እንደ ቲንክ ታነክም ሊደራጅ ይችላል። ጉዳዩ ይሄንን መስራት ይሆናል። ወደራሱ የሚዲያ ፕሮጀክቶች የሚያድግበትም መንገድ ይመቻቻል። ብቻ፤  ከተለመደው የህዝብ ግንኙነት ስራ ከሚሰራው አካል የተለየ መሆን ይኖርበታል። ለእያንዳንዱዋ ሚዲያ ላይ ለምትወጣ ስህተት ማጣሪያ የሚሰጥ አካል ይሆናል። በመረጃ የበለጸገ፤ ፎርማል አካል መሆን አለበት። ተመጣጣኝ የሚዲያ ምላሽ መስጠት ህጋዊ እርማት ለሚያስፈልጋቸውም አቻውን መስጠት።

ይህ ፀሀፊ የህወሓት ዋነኛዉ የፕሮፖጋንዳ ማሽን በመሆኑ፣ በዚህ መልኩ የያየሰውን ጽሁፎች በተከታታይ እትማችን እንሄድባቸዋለን። በዛዉም የአለቆቹን ዓላማና ማንነት እንዲሁም አቅም ያሳይልናል ብለን እናምናለን፡፡
ትዝብታችንን ከታዘባችሁትም ጻፉልን፤ አንደወረደ ይነበባል