ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል ሁለት “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን? ኢኮኖሚያዊ ጥቃት

ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል ሁለት “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን?  ኢኮኖሚያዊ ጥቃት

ትርጉም አልሰጡትም። ግን ከግምታችንና ከልምዳቸው ተነስተን፤ “ሀገራዊ ቀውስ” የሚሉት፤ ብጥብጥን  ሁከትና ትርምስን  ወዘተ መሆኑን መገመት አያዳግትም። የሚፈጥሩትም ራሳቸው ናቸው። ይህንን ሊያደርጉ የሚችሉባቸውን አጋጣሚዎችና እድሎች ለደህንነት በማያሰጋ ደረጃ እንደሚከተለው ዝርዝርዝር ሁኔታዎችን ባላካተተ መልኩ ለማቅረብ ተሞክሯ። 

“ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን? ክፍል ሁለት

ኢኮኖሚያዊ ጥቃት

የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ምርቶች የሚገኙባቸውን አካባቢዎች ማመስ መምታት መዝረፍ ከባድ ጉዳት ማድረስ። ቡናና ሰሊጥ ዋና ናቸው። የቅባት እህሎችና ጥራጥሬም አብሮ ይመታል። ስንዴና መሰል አንገብጋቢ ምርቶችን ከምርት አስከገበያቸው ያለን ሰንሰለት በማዳከም፤ ለውጪ ምንዛሬ ጫና መንግስትን መዳረግም የቆየ የቤት ስራቸው ነው።

ከመስከረም 30 በኋላ በጌዲኦና በምእራብ ጉጂ ዞኖች የአምናውን አይነት ግጭቶች መቀሰቀስ።  በእነዚህ የቡና መስመሮች ላይ የተቀናጀ የኢኮኖሚ ጦርነት ይከፈትባቸዋል።  የዚህ አካባቢው ቡና መራሹ ጥቃት እጆቹን ወደ ሀዋሳ ሊዘረጋጋ ይችላል። በምእራብና ምስራቅ ወለጋ፤ እንዲሁም በቄለም ቡና አምራች ወረዳዎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ይኖራሉ።

 

ሀረርጌ ባቢሌና ጭናቅሰን እንዲሁም የምስራቅና የምእራብ ሀረርጌ  ድንቅ የቡና መሬቶችም የፈንቃይ ተፈንቃይ ታሪኮችን ያስተናግዳሉ።

የባሌና የአርሲ አካባቢዎች ሀይማኖትን መሰረት በማድረግ ተመሳሳይ የኢኮኖሚ ጥቃቶች ይፈጸማሉ።  ጎለልቻ፤ ባሌ ብሄራዊ ፓርክ የሀረና የጫካ ቡና የመቃጠል አደጋ ይደርስበታል። ይሄ አካባቢ በስንዴ ምርቱ ስለሚታወቅ ጥቃቱ እሱንም ያማከለ ሊሆን የሚችልበት እድል ሰፊ ነው።

ጅማን አጋሮና ቦን፤ ሚዛን ቴፒ ወዘተ

በዚህ መስመር የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን የክልልነት ጥያቄዎችን እንዲሁም የሀይማኖት ጉዳዮችን ምክንያት በማድረግ  ግጭቶችን ይቀሰቅሳሉ። ውጥረት ይፈጥራሉ። ቴፒ  የቤንች ማጂ ዞን የጉራ ፈርዳ ወዘተ እዚህ ውሰጥ ይጠቃለላሉ። ቡና፤ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ዋና ኢላማ ናቸው። ሀይማኖትና ኢኮኖሚ ተኮር የሆነ የዲሞግራፊ ፖለቲካም እንደተለመደው ብቅ ይላል።

የአማራና የኦሮሚያ ሰሊጥ አምራች አካባቢዎቸም በተመሳሳይ የኢኮኖሚ  ጥቃት ውስጥ የሚወድቁበት እድል ሰፊ ነው።

 

 

የሚዳከመውን ቱሪዝም ማዳከም

ብዙዎች በኮቪድ 19 ምክንያት የቱሪዝም መስኩ ከባድ ችግር እንደሚገጥመው ያምናሉ። በተቃራኒው ደግሞ በወረሺኙ ሳቢያ በሚፈጠረው አረንጉዋዴ መነቃቃት ተፈጥሮን ፍለጋ የሚመጡም ቁጥራቸው ይጨምራል የሚሉም አሉ። ክርክሩን ለጊዜ ትተነው ኮቪድ 19 ባይኖርም ቢኖርም ላይቀርልን ስለሚችለው ችግር እናውራ። የእኛ ብቻ ስለሆነው ችግር።  የቀፍታ ሽራሮና የአልጣሽ እንዲሁም የጋምቤላ ፓርኮች ላይ የቃጠሎ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል፤ ይሄ ከፖርት ሱዳን የሚመጣውንና የሚሄደውን የንግድ እንቅስቃሴ ከማወክና ከመቆጣጠር ጋር የተያያዘ እንቅስቃሴ ሊኖረው አንደሚችልም ይገመታል፤

እንዲህ ያለ ኢኮሎጂካል ዎር፤ በባሌና በአርሲ ፓርኮች ላይም በስፋት ሊፈጸም እንደሚችል መጠርጠሩ አይከፋም።

የተፈጥሮ ሀብቶችንና ምንጮቻቸውን መቆጣጠር

ሁከትና ብጥብጦቹን የሚመሩዋቸውም ሆነ በተለያየ መንገድ የሚያግዙ፤ እንዲሁም የሚያደራጁ የሚያሰለጥኑ አካላት የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀበቶች በእጅ አዙርና በቀጥታ የመቆጣጠር አላማን ያነገቡ ሆነው እናገኛቸዋለን። ስለሆነም፤ ጥያቄው “መንግስትን አንቀበልም ወይም ስልጣን አጋሩን” ከሚለው የወጣ ሆኖ ይገኛል። አጋጣሚውን በመጠቀም የስልጣንም ሆነ ቀጥተኛ የፖለቲካ ጥያቄን ያላነገቡ ቡድበጨኖች ለኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎቻቸው መለስ ያደርጉታል። የተፈጥሮ ሀብት መገኛ ቦታዎችን ይቆጣጠራሉ። ቻይናና አሜሪካ መሩ የሪሶርስ ትንቅንቅ የሚወልዳቸው በተለይም የሬር አርዝ ሜታልስ ፍልሚያ ማሳለጫ ይሆናል።  ወርቅ፤ ታንታለምና መሰል ውድ ማእድናት በሚገኙባቸው አካባቢዎች ላይ ስውር ሽኩቻዎች ይካሄዳሉ። ወንዞችና ተፋሰሶቻቸውን የመቆጣጠር፤ የናይልን ትናንሽ ገባሮችን ሳይቀር ከሰው ንክኪ የማራቅ ዘመቻውን አጠናክሮ ለመቀጠልም አካላዊ ውክልና ግዴታ ስለሚያስፈልግ፤ ይህንን እድል ተከልለው ስራቸውን  የሚሰሩ ብዙ ሃይሎች ይኖራሉ። ትርምሱን ለዚሁ ሲሉ የሚፈጥሩና የሚያግዙም አይጠፉም።  ለወንዞቹ፤ ለርጥበት አዘል መሬቶችና በከርሰ ምድር ውሃ ክምችታቸው የሚታወቁ ቦታዎችን፤ ወይም የናይልን ወተር ሼዶች ይይዛሉ። ከተያዘም ያስለቅቃሉ። ሀይማኖታዊ የዲሞግራፊ ለውጦችን ለማካሄድ የመሞከር ነገርም ይስተዋላል።

ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል ሦስት “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን? ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞ

ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል አንድ “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን?