ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል ሦስት “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን? ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞ

ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል ሦስት “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን? ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞ

ትርጉም አልሰጡትም። ግን ከግምታችንና ከልምዳቸው ተነስተን፤ “ሀገራዊ ቀውስ” የሚሉት፤ ብጥብጥን  ሁከትና ትርምስን  ወዘተ መሆኑን መገመት አያዳግትም። የሚፈጥሩትም ራሳቸው ናቸው። ይህንን ሊያደርጉ የሚችሉባቸውን አጋጣሚዎችና እድሎች ለደህንነት በማያሰጋ ደረጃ እንደሚከተለው ዝርዝርዝር ሁኔታዎችን ባላካተተ መልኩ ለማቅረብ ተሞክሯ። 

“ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን? ክፍል ሦስት

ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞ

በከረምት ውሃ ሙሌት የመጀመሩ እና ከግብጽ ጋር ዳግም ድርድር የመጀመሩ ነገር እውን የሚሆንበት እድል ሰፊ ስለሚሆን፤ ለታቀዱት አወዛጋቢና ቀጣፊ ፕሮፓጋንዳዎችን ለማምረት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ፤ ከአሜሪካ ጋር ተመሳጥሮ ደባ እየፈጠመ እንደሆነ ብሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ አየሰጠ እንደሆነ የሚወራበት አድል በጣም ሰፊ ነው።

እያንዳንዱን ነገር በጥንቃቄ ማስኬዱ ይበጃል፤ ጠንካራ የሚዲያ ቲም አዋቅሮ የተደራጀ ምላሽ መስጠት፤ አስደገዳጅ የሚዲያ አዘጋገብ ህግ ማውጣት፤ እንዲሁም የህግ ክፍሉን በማጠናከር፤ ያለአግባብ ፕሮጀክቱን በተመለከተ ዘገባዎችን የሚያስተላልፉ አካላት የሚጠየቁበትን አሰራር መዘርጋት፤

 

ደቡብ ሱዳን

በደቡብ ሱዳን ያለውን አለመረጋጋት ተከትሎ በጋምቤላና በአሶሳ ላይ ነውጥ ለመፍጠር ምቹ የህወሓት ሜዳዎች ሆነው የሚቀጥሉ የጁባ ግዛቶች ቤት ይቁጠራቸው።  የግብጽና አጋሮቹዋ  በነልማት ሰበብ የወረሩት ቀጣና በመሆኑ፤ በቅርቡም አዳዲስ ጥምረቶችን በመመስረታቸው (በማደሳቸው) ። ግብጽ አካባቢውን በተለያየ ፎርም ይዛዋለች። የውሃ ቁፋሮና የነዳጅ ማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩትን የማሌየማሌዢያና መሰል ሀገሀራት ድርጅቶችን ተገን አድርጋ መንቀሳቀሱን ታውቅበታለች።

 

የስደተኛ ካምፖች

የካምፖቹ ቦታ አያያዝ የተጠና ነው የሚመስለው። ውስጡ ገብቶ ለመረመረው ደግሞ ብዙ ጉድ ያገኛል።  ከስደት ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶችን ስፓንሰር የሚያደርጉ፤ ፈንድ የሚያደርጉ፤ በአጋርነት አብረው የሚሰሩ፤ በማማመከር በጥናት በጨረታ በበ ፈቃድ የመንግስት የግል እንዲሁም የውጪ ሀገራት አካላት ተጠያቂነትና ግልጽነትን እንዲያዳብሩ የሚያደርግ ሀገር አቀፍ ፕሮጀክት ነድፎ መከታተል ነው። ሁሉም ለቀውስ ታለንቱ ምቹ ሁናቴ የሚፈጥር ግብአት አላቸው።  

 

የውጪ እርዳታ ድርጅቶች

እነዚህ የምእራባውያን ድርጅቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ካርታ ላይ ወሳኝ የጂኦፖለቲካል ስፍራዎችን በመያዝ ይታወቃሉ። ከዋና ዋና ከተሞች ይልቅ በገጠርና በክልል እንዲሁም በድንበር አካባቢዎች ተከማችተው ይገኛሉ። ስራዎቻቸው በውጢ የፖለቲካ ፍላጎቶች የሚጠለፉም ብቻ ሳይሆኑ በብዛት ፍላጎቶቹን አማክለው የሚቀረጹ ናቸው።

ግብጽ ላይ ላላቸው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሲሉ ለብላክሜይሊንግ የመጡ እንዳሉ ግልጽ ነው። በተለይም በውሃ ቁፋሮና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ተሰማርተናል የሚሉና ረዠም እድሜ ያስቆጠሩ የእርዳታ ድርጅቶች ሞልተዋል። እነዚህን በንቃት መከታተል። የነውጥ ሀይሉን በተለያዩ አማራጮች ሊደግፉ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው። የየራሳቸው የንግድና የኢኮኖሚ ሰንሰለትም ዘርግተዋል፤ ይህንን ህገወጥ አለም ለማቆንጀት ከሁከትና አለመረጋጋት በላይ  ምርጥ አማራጭ አይኖርም። “ቅማል መቼም ቢሆን ጸጉርህ ቆሸሸ አትልህም” የሚል አባባል አለ።

የተቃውሞ ሰልፍ መጥራት

በቅርቡ ተጀምራ የነበረችውን አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ይቀጥላሉ። ከዚህ ቀደም በሰልፍ ፎቶዎች ውጤታማ በሆኑባቸው የኦሮሚያ ክልሎች ላይ ድጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠሩ ይችላሉ። “ብልጽግና የጋራ መንግስት እንመስርት ስንለው እምቢ አለን፤ በህገመንግስቱ መሰረት ከመስከረም ጀምሮ መንግስት ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ የተቃውሞ ሰልፍ እናካሂዳለን” ይላሉ። በማህበራዊ ደረገጽ ሰልፍ ይጠራሉ። ይሄንንም ለተለያዩ ነገሮች ይጠቀሙበታል። መንግስት የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት ሲሞክርም፤ እንደ አፈናና ጭቆና በመውሰድ  ህዝቡ መንግስት ላይ ጥላቻ እንዲያነብር ያደርጋሉ። ይሄ ሙከራ በተለይም በኦሮሚያና አማራ ውጤታማ መሆን የሚችልባቸው አደሎች ሰፊ ናቸው።

 

ዐቢይን ከህዝቡ ማቃቃር፤

ከእነዚህ ሰልፎች  ጎን ለጎን፤ በእርስ በእርስ ግንኙነቶችና በዲጂታል ሰራዊቶቻቸው በኩል፤ “ዐቢይ ጸረ ኦሮሞ ነው” የሚለውን እሳት የመጫር ስራ ይሰራሉ። በቅርቡ እንደታየው የእነኤርሚያስ አይነቶቹን ከፋፋይ ሴራዎች በስፋት ስራ ላይ ያውላሉ። እንደማቀጣጠያ ከሚጠቀሙባቸው ተጨማሪ መንገዶች  ውስጥም፤

“ቁልፍ የሚባሉ የስልጣን ቦታዎችን ለአማራ ተወላጆች ሰጥቷል፤ ( የጦር ሃይሎች ፤ ውጪ ጉዳይ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር፤ ንግድና ኢንዱሰትሪ፤ ገቢዎች፤ በዋናነት ይጠቀሳሉ በአምባሳደርነት ለመያዝ ከሚፈለጉ ትልልቅ ሀገራትና ከተሞች ውስጥ የኦሮዎች አለመመደብም አንዲሁ ይነሳል፤ የእነዳንኤል ክብረት የቤተመንግስት ሚና ወዘተ)፤ “ቲም ለማ ተገፍቷል”  የሚለውም ይመጣል ፤ “የንግድ እንቅስቃሴውን በርካታ የአማራ ተወላጆች ይዘውታል” የሚለውም ደግሞ በኢኮኖሚው በኩል የሚነሳ ነው። የአንዳንድ ኦሮሞ ባለሃብቶች መገፋትም እንደማስረጃ ይቀርባል፤

 

ይሄንኑ አይነት የሰብእና ገደላ (ካራክተር አሳሲኔሽን) በተቃራኒው ያለው የተቃዋሚ ጎራም ይደግመዋል። የአማራው ልሂቅና ተቃዋሚ “አማራው ተገፋ፤ ታከለ አዲስ አበባን አስወረረ፤ ቁልፍ ቦታዎች በኦሮሞ ተያዙ” ወዘተ  የሚሉ ወቀሳዎች እየሰነዘረ አየሩን ለመያዝ ይሞክራል። የተለመደው በሀገር ሉአላዊነት የመደራር፤ ሀገርን የመሸጥ ሴራ የእነ አይኤምፍና የአእነአለም ባንክ ስም እየተናሳ ይተነተናል፤ (እስከዛሬ የተደረጉት የማይሰይጠን የማሳነስ በጥቅሉ የተለመዱት የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ ተጠናቅሮ ይቀጥላል፤)

 

የአዲስአበባን  የፖለቲካ ካርድ መምዘዝ

የልዩ ጥቅም ጥያቄና፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከሰም አጠራር ጀምሮ ያሉ ንትርኮች የታሪካዊ ቦታዎች ውዝግብ ወዘተ እንደ አዲስ ይቀሰቀሳል። ቤተመንግስቱ ውስጥ ሀውልት ይሰራልን  የሚለውን ጨምሮ ተራ የሚመስሉ ግን ግባቸው የታለመ ጸረ መንግስት በተለይም  ዐቢይን ከኦሮሞ ባስ ሲልም ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ጋር የሚያላትሙ አደገኛ ጉዳዮችን ያራግባሉ።

የተቀናጁ የሶሻል ሚዲያ ጥቃቶች፤

በዘመነ ሶሻል ሚዲያ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የሚስተዋሉ ዘመን አመጣሽ የፕሮፓጋንዳ ታክቲኮችን በሙሉ በመጠቀም  የብልጽግና ፓርቲን ሁለንተናዊ  ገጽታ የማበላሸት እንቅስቃሴዎች የበለጠ ተጠናክረው ይቀጥላሉ’።

2019 battle: How fake news was used as a weapon of mass deception የሚለውን ፅሁፍ ያንብቡ። Fact Check Bureau New Delhi ያሳተመው ነው። (እዚህ ጋ የአታሚውን መጠሪያ ልብ ይበሉ። ሀቅ አጣሪ በቢሮ ደረጃ ይቋቋማል) የፓርቲው አባላት ነን የሚሉ ግለሰቦችን አስገዳጅ፤ አስነዋሪ፤ (በተለይም በኦሮሚያና አማራ ክልል ላይ) የሆኑ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የሚያሳዩ የውሸት ቪዲዮዎች በራሳቸው ሰዎች እየተሰሩ በሶሻል ሚዲያው ላይ ይለቀቃሉ፤

ታሪኮችን በማገጣጠም፤ በማዛባት (Twisting) ተምሳሌቶቸን ማራከስ ማስመሰል፤ ማጋነን፤ ማቆንጀት (Window dressing)፤ ውጥረት በመፍጠር፤ ተቀናቃኝን ማሳጣት፤ ማዋረድ፤ የካሜራ አንግል እየለዋወጡ ሰልፈኛን በማብዛትና በማሳነስ ወዘተ……. የተለመዱ የሶሻል ሚዲያ ታክቲኮች ላይ ይሰማራሉ። 

ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል አንድ “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን?

ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል ሁለት ኢኮኖሚያዊ ጥቃት