ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል አንድ “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን?

ቀውስና ቀውሶቹ  ክፍል አንድ  “ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን?

ኢትዮጵያ በቅርቡ ከተከሰተውን የለውጥ ጉዞ ተከትሎ ሊታመኑ የማይችሉ ፈተናዎችን አሳልፋለች። እየተጋፈጠችም ትገኛለች። ከፊታችን ካሉት ፈተናዎች መካከልም፤ “የህገ መንግስት ቀውስ ተፈጠረ” በሚል ሽፋን እየተዘጋጀ ያለው ሴራ ጉልሁን ድርሻ ይይዛል።

ኢትዮጵያ በቅርቡ ከተከሰተውን የለውጥ ጉዞ ተከትሎ ሊታመኑ የማይችሉ ፈተናዎችን አሳልፋለች። እየተጋፈጠችም ትገኛለች። ከፊታችን ካሉት ፈተናዎች መካከልም፤ “የህገ መንግስት ቀውስ ተፈጠረ” በሚል ሽፋን እየተዘጋጀ ያለው ሴራ ጉልሁን ድርሻ ይይዛል። እጅግ ብልጠት፤ ቅንጅትና መስዋእትነት በታከለበት መንገድ ካልተመለከተ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። ይህ አጭር ሰነድ የዚህን ፈተና ጥያቄዎችና መልሶቻቸውን በጨረፍታ ለመዳሰስ ይሞክራል።

“ሀገራዊ ቀውስ” ሲሉን? ክፍል አንድ

ትርጉም አልሰጡትም። ግን ከግምታችንና ከልምዳቸው ተነስተን፤ “ሀገራዊ ቀውስ” የሚሉት፤ ብጥብጥን  ሁከትና ትርምስን  ወዘተ መሆኑን መገመት አያዳግትም። የሚፈጥሩትም ራሳቸው ናቸው። ይህንን ሊያደርጉ የሚችሉባቸውን አጋጣሚዎችና እድሎች ለደህንነት በማያሰጋ ደረጃ እንደሚከተለው ዝርዝርዝር ሁኔታዎችን ባላካተተ መልኩ ለማቅረብ ተሞክሯ። 

ጸጥታ የማደፍረስ፤ የአለማረጋጋት ዘመቻዎች

እነዚህን ጉዳዮች በክልሎችና በቀጣናዎች ከፋፍለን ማየት ብንችል መልካም ይሆናል።

 ኦሮሚያ

ከፍተኛ የተቃውሞ እና የአመጽ ፖለቲካ የማራመድ ግብ ይዘው ይንቀሳቀሳሉ። የትግሉ መሪዎች በግል በዘረጉዋቸው መረቦች፤ ከመንግስት አመራሮች ጋር በዘሩት ኔትዎርክ እየታገዙ ፤ እንዲሁም የሃይማኖትን ካባ ለብሰው፤ ተገፍተናል የሚሉ የቀድሞ የኦዴፓ  አመራሮችን  በማስተባበር ዘመቻቸውን ይዘውሩታል።

“የራሳችን ሜዳ “ የሚሉዋቸው አካባቢዎች አሉ። አዳማ፤ አርሲ፤ ባሌ፤ ምስራቅና ምእራብ ሀረርጌ፤ ድሬደዋ፤ ሻሸመኔ …… ዋና መንቀሳቀሻ ይሆናሉ።

ድሬደዋና ሀረር የተለመዱት አይነት ቄሮና ሄጎ መር የጋጥ ወጥ ወጣቶች ረብሻ ዳግም የሚከሰትበት እድል ሰፊ ነው፤ ምናልባትም፤

የኬንያና የኦሮሚያ ድንበሮች ላይ የሚገኙትን አመራሮች በጥብቅ ክትትል ስር ማድረጉ አይከፋም። ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር  ያለባትን ቀጠናውን የመምራት የእልቅና ፖለቲካ ለማሸነፍ ስትል፤ ኢትዮጵያን ሳይበትንም ሳይሰበስብም አጉል አድርጎ ከሚያኖር ማንኛውም አካል ጋር ትሰራለች። የዐቢይ መንግስት ከቻይና ጋር፤ ኬኒያ ደግሞ ከአሜሪካ ጋር የተሻለ ቅርበት ስላላቸው፤ የሁለቱ ሀያላን ፉክክር ሰላባ የሚሆኑበት እድል ሰፊ ነው። አሜሪካንን ተከልልላ ካይሮ ናይሮቢን የማታቅፍበት ምክንያት የለም።

ለዚህ ጨዋታ ደግሞ ከኬኒያ የሚዋሰኑት የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ወረዳዎች ምቹ ምሽጎች ይሆናሉ። የአሜሪካ ግዙህ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅቶች እንዲሁም አጋሮቻቸው የተንሰራፉበት ቀጣና በመሆኑ ለኬንያ የተሻለ እድል ይሰጣል። ሁሉንም በንቃት መከታተል ነው።

ይህ በተለመዱ ክልሎችና  መስመሮች ላይ የሚተገበር ነው። Melka MERI Camp, Mandera የእህል፤ የጣውላ፤ ስንዴ ብረት እጽዋትና ተክሎች ሲሚንቶ በአፋርና ሶማሊ የጦር መሳሪያ ንግድና የሰው ዝውውር ከኢትዮጵያ ወደ ሶማሊያ ወደ የመን ወደ ጅቡቲ ይካሄዳል።  

 አፋር

በአፋር ወጣት ፖለቲከኞች (የጃዋር ምልምሎች) በማህበራዊ ሚዲያ የተደራጀ የተቃውሞና የቅሬታ ድምጾች ያስተጋባሉ። ከሶማሌ ጋር የድንበር ግጭቶች በተለመዱት ቦታዎች ሊፈጥሩ ይንቀሳቀሳሉ። ይህንንም ጅቡቲ ካሉ የውጪ ሃይሎችና ከትግራይ ክልል በሚነሱ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ይፈጽሙታል። የደፈጣ ጥቃቶችና የንግድ መስመሮችን መረበሽ ወዘተ ሊስተዋሉ ይችላል፤ በአዋሽና በሀላይ ደጌ ፓርኮች ላይ ጥቃት የሚፈጸምበት እድል አለ፤ የተፈጥሮ ሀብት ክፍፍልን፤ የጎሳ ግጭቶችን፤ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ወዘተ  እንደዋና ማቀጣጠያዎች ይጠቀማሉ። የክልልን መሪ ፓርቲ አቅም የማሳጣት ግብ ይኖራቸዋል። ጅቡቲ ከወደብ ፖለቲካው ጋር በተያያዘ፤ የገልፍ ሀገራትም የህገወጥ የእህል ንግዳቸውን መስመር ለማስጠበቅ የሚፈልጉት ድራማ ይሆናል። በቅርቡ ከፓርክ ጋር በተያያዘ በአካባቢው “ዱባይ ተኮር” እንቅስቃሴ እንዳለ የሚናፈሰው ወሬ የራሱን ክፉ ንፋስ ይዞ መምጣቱ አይቀርም፤ እስከአሰቦት የሚዘረጋ ሀይማኖታዊ ውጥረትና ግጭት ለመቀስቀስ የሚያስችል እድል ያገኛሉ።

ወደ ትግራይ አልፎ ወደሱዳን የሚያቀና፤ የያሎ ጭፍራ የቁም አንስሳት ንግድ የካፒታል ምንጭ በመሆን ያገለግላል።

 

ሰሜን ሱዳን

የአማራ የትግራይንና የቤንሻንጉል ክልልን ግባቸው ያደረጉ የተለያዩ ጥቃቶችን ማስተናገጃ ሜዳ ነው። በርካታ የውጪ ሀይሎች ለእጅ አዙር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያቸው ከጥንት ጀምሮ የሚጠቀሙት አካባቢ ነው። በዋናነት በቅርቡ የተነሳውን “የእርሻ መሬቶች ይገባኛል” ጥያቄ ላይ በማትኮር ይንቀሳቀሳል። ህወሓትና ግብጽ በእንግሊዞች እርዳታ እየታገዙ የወረራ ሙከራዎችን ያደርጋሉ። በተለይም ገዳሪፍን እንደመቀመጫቸው በማድረግ የእርስ በርስ ግጭቶችን ድንበር ለማሻገር ይሰራሉ። ከመሃል ሀገር የተቃዋሚ ሀይሎች ጋር በሚደረግ የተናበበ የሚዲያ ዘመቻ እየታገዘ ይከወናል። የተወረርን ነጋሪት  ይጎሰማል።

የስደተኞች ሽሽት፤ የህገወጥ ነጋዴዎች ብጥብጥ፤ የገልፍ ሀገራትን ባሳተፈ ደረጃ ለም የቸአርሻ መሬቶችን ማእከል ያደረገ ግብግብ ይካሄዳል። ቤንሻንጉል ፤ አማራና ትግራይ ክልሎችን ያሸብራል። የፋኖን ታጣቂዎች ያስታጥቃል የመተማን መስመር በመከተል፤ ከፖርት ሱዳን የሚመጣውን ወሳኝ የንግድ አቅርቦት ያስተጉጓጉላሉ። የቀፍታ ሽራሮ፤ የአልጣሽና የጋምቤላ ፓርክ የመቃጠል አደጋ ይደርስባቸዋል። ግብጽ ይሄንን እድል በመፍጠርም በማስፋትም በመጠቀምም ስራዋን ትሰራለች።

 ትግራይ

 ከላይ የሚጠቀሱትንም ሆነ፤ ከታች የሚዘረዘሩትን የቀውስ ቀጣናዎችና እድሎች የሚጠቀመው የህወሓት የነጋዴዎች ቡድን ነው። ለቀውሱ በጀት መደጎሚያውም  የማይሰማራበት የህገ ወጥ ንግድ አይነት አይኖርም። ድሮም የተካነበት በመሆኑ የልምድ እጥረት ይገጥመዋል ተብሎ አይገመትም። የወርቅ፤ የሬር ሜታልስ ምርቶች ላይ በትኩረት ቁጥጥር ማድረግ።  ቡና፤ አህያ፤ የሶላር ቁሳቁስ፤ የቻይናን ፍላጎት ተከትለው በሚዘረጉት የንግድ መስሞሮች ላይ በትጋት ይሰለፋል። ቢራ፤ ጨርቃጨርቅ፤ የእሽግ ውሀ ንግድ፤ ከሰል፤ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በደንብ ይሰራሉ፤ የምንዛሬ ሽሽት ወዘተ …… እየተባለ ቀይ ባህርን የሚሻገር ሸቀጥ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል።

ይህ ቡድን የሱዳን በሮች በሚሰጩት እድል እየታገዘ ወደታችም ይወርዳል።   በጋምቤላ በመተማ ቋራ በቤኒሻንጉል ጉምዝ በሚደረጉ ድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴዎች የደቡብ ሱዳንን መስመርና ከሱዳን እንዲሁም ከኬኒያ አለፍ ሲልም (በተለይም) በሶማሊያ በኩል ስርአት አልበኝነትን የማስፋፋት እንቅስቃሴዎች ሊታዩ ይችላሉ።

 አማራ

ከላይ የጠቀስነውን ከሱዳን የሚነሳ ችግር በመጨመርም ይሁን ራሱን ችሎ በጎንደርና በሱዳን ተዋሳኝ ዞኖችና ወረዳዎች፤ ወልቃይት አካባቢ አሁንም በፋኖ የሚመሩ ሽፍታ አንጋሽ ውንብድናዎች ይስተናገዳሉ፤ አሁንም የቅማንትን ጉዳይ በመቀስቀስ፤ የሚከወን እንቅስቃሴም አይጠፋም። የውጭ ምንዛሬ ዋልታ የሆነውን የሰሊጥ ኘመስመር የመምታት አላማም ይኖረዋል። በተለይም በጠገዴ ክንፍ ያለውን የምርት ሰንሰለት የሚበጣጥሱ ከማእከላዊ ጎንደር እንዲሁም ከትግራይ  እየተነሱ የሚሰነዘሩ ሁለንተናዊ ጥቃቶች ሽብር ፈጠራዎች ይኖራሉ።

ወደትግራይ የሚደረጉ የንግድ ልውውጦችን የማገድና ከማእከላዊ መንግስቱ ጋር ቁርሾውን የማፋፋም፤ የአዴፓን ጉልበትና ሀይል የማናናቅ፤ የማእከላዊ መንግስቱን ተጽእኖ አሳዳሪነት የመቀነስ ግብ ይኖረዋል።

“የወልቃይትና የራያን ጉዳይ አሁኑኑ” የሚሉ እንቅስቃሴዎች ይስተዋላሉ።

“ጎጃም ተበላ ተገፋ” የሚሉ ድምጾች ጎልተው ይወጣሉ። ህገወጥ የመሳሪያ ንግድ በጣና በኩል ከሱዳን በጎንደር አድርጎ ይጧጧፋል።  እንደሰሜን ጎንደሩ ሁሉ የሽፍትንት እንቅስቃሴዎች በጎጃም ዞኖች ላይ ተስፋፍቶ ይታያል፤ ወደ ቤኒንሻንጉል የሚሻገሩ ሴራዎችም አይጠፉም። በተለመደው መልክ የተለመዱት የተለመዱት አይነትጥቃቶች ይፈጸማሉ።

 ሶማሌ

ሶማሌ ውስጥ የሙስጠፌን ኔትዎርክ በተለያየ መልኩ አደጋ ላይ ለመጣል የሚፈጸሙ ድርጊቶች ይኖራሉ፤ ከቦረና እና ከአፋር እንዲሁም ከማንዴራ ትሬያንግል የሚነሱ የጎሳና የእርስ በርስ ጥቃቶች በሙሉ የጂግጂጋን ሰላም የማወክ አላማ የያዙ ይሆናሉ፤ የኦኤንኤልኤፍን የቅርብ ጊዜ የእርስ በርስ ክፍፍል ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ አለመረጋጋቶች በጊዜ መዳኘት ይኖርባቸዋል።

በኬኒያ ፤ በሶማሊያና በኢትዮጵያ ማፍያ በነጋዴዎች የሚታገዙ ጥቃቶች የቁም ከብት ንግድን ማእከል ያደረጉ ረብሻዎች ይስተናገዳሉ። የሸበሌና የዋቤን ተፋሰስ አማክለው ይፈጸማሉ።

ከስደተኞች ጋር በተያያዘም አደገኛ የነውጥ እንቅስቃሴዎች የሚከሰቱበትን እድል በንቃት ማየቱ አይከፋም። ይህ ቀጣና፤ በጎሳ እና በቤተሰብ የተተበተበ የቁም ከብትን ንግድን፤ የከሰልና፤ የመሳሪያ እንዲሁም የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወዘተ የተንሰራፋበት ነው። ይህንን የንግድ መስመር ለመያዝና ለማስጠበቅ በአዳዲስና በነባር ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ትንቅንቅ ይካሄዳል።

ከአዋኪው ሀይሎች ጋር በስውር የሚሰሩ አካላት የሚርመሰመሱበት እንደሆነ ግልጽ ነው። እስከመፈንቅለ መንግስት የሚያደርስ ሙከራ ሊያደርጉም ይችላሉ። በቱርክና በዶሃ እየታገዘ ከሞቃዲሾ የሚነሳው ሃይልም የአካባቢውን የሃይል ሚዛን የሚቀያይሩ እርምጃዎች ሊወስድ ይችላል።

የእርዳታ ድርጅቶችን በንቃት መከታተሉ ይመከራል።

 

ደቡብ ክልል

“የሲዳማ ጥያቄ አልተቋጨም” የሚል ጥያቄ የሚያገረሽበት እድል ሰፊ ነው።የኤጀቶ መሪዎች ከጃዋር ቤት የማይጠፉበትን ምስጢር ማጠየቅ ነው፤ በሌሎች የደቡብ ዞኖች የክልልነት ጥያቄ እንዲቀሰቀስ የሚሰሩ ሚዲያዎችን ማን ነው የሚደግፋቸው? የሃዲያ የወላይታና የካፋን በዋናነት ማንሳት ይቻላል፤

ደቡብ ክልል ከብልጽግና እና ከኢዜማ ጋር ከሌሎቹ የተሻለ ትስሰር እንዳለው ይታወቃል። ይሄንን ለማዳከመም በኦሮሚያና በደቡብ ክልል ተዋሳኝ ወረዳዎችና ዞኖች ላይ ያሉ አመራሮች ከእነጃዋር ጋር በጥምረት ሊሰሩ ይችላሉ። መረበሽ የመሪ ፓርቲውን ቅቡልነት ማሳጣት ይሆናል የፕሮጀክቱ አላማ። አማሮ ቡርጂ ሰገን ሃመር ስልጢ ሲዳማ፤ የም ሀዲያ ከፋ ሸካ ወዘተ ከኦሮሚያ ክልል በሚነሱ ጥቃቶች (በተለይም ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያላቸው) ሊፈጸምባቸው ይችላል። በቅንጅት አመራሮቹ ሊመሩዋቸውም ይችላሉ።

ቤኒሻንጉል

በዋናነት ከአማራና ከኦሮሚያ በሚሻገሩ ጥቃቶች ስር ይወድቃል። ከሁለቱ ክልሎች ጋር የሚዋሰንባቸው ወረዳዎችም ሆኑ ዞኖች በሙሉ ማለት ይቻላል ለግጭት የተጋለጡ መሆናቸው ይታወቃል። በባለሃብቶችና በኢንሸስትመንት ስም አሁንም ሰፋፊ መሬቶችን ይዘው የሚገኙ የህወሓት ኢንቨስተሮችና ሰንሰለቶቻቸው ከሁለቱም ሱዳኖች የሚገቡ ረብሻዎች መናገሻ ይሆናል። በከማሺና በሌሎችም አምራች የቤንሻንጉል ጉምዝ ዞኖችና ወረዳዎች የግብርን መሰረተ ልማቶችና ማሳዎች እንዲሁም ምርቶች ጥቃት ይፈጸምባቸዋል።

ኤርትራ

ከኤረትራ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲደፈርስ በተለይም በሶሻል ሚዲያው ተንኩዋሽ መረጃዎችን በማቀበል የሚሰሩ ሰራዎች አሉ፤ ህወሓትም የጸረ ኢሳያስ እንቅስቃሴዋን አጠናክራ ትቀጥላለች፤

ቀውስና ቀውሶቹ ክፍል ሁለት ኢኮኖሚያዊ ጥቃት